Get Mystery Box with random crypto!

ሐሙስ ጠዋት! ሰኔ 15/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች 1፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካር | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሐሙስ ጠዋት! ሰኔ 15/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ሎጅስቲክስ ክፍል "ወደ ሌላ አገር በሽያጭ ሊተላለፍ" ወይም "ለብድር መያዣነት ሊውል" እንደኾነ ተደርጎ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጨው መረጃ "ከእውነት የራቀ" እና "መሠረተ ቢስ" መኾኑን አስታውቋል። "ይህ ከእውነት የራቀ ወሬ የብሔራዊ አየር መንገዳችን ስም እና ገጽታ" ይጎዳል ያለው አየር መንገዱ፣ ወሬውን የሚያሰራጩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጠይቋል።

2፤ ኦብነግ አንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል ማክሰኞ'ለት ቀብሪደሃር ከተማ ውስጥ በከፈተው ድንገተኛ ተኩስ ከተገደሉት ግለሰቦች መካከል ሦስቱ አባላቱ እንደኾኑ አስታውቋል። የሠራዊቱ አባል በተኩሱ አንድ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ አመራር አባልን ጨምሮ አራት ሰዎችን ገድሎ ሌሎች ሁለት ሰዎችን ማቁሰሉን ግንባሩ ገልጧል። የሱማሌ ክልልና ፌደራል መንግሥታት ድርጊቱን አጣርተው ርምጃ እንዲወስዱ የጠየቀው ኦብነግ፣ በክልሉ በተደጋጋሚ የሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች "አጠቃላይ አመጽ" ሊቀሰቅሱ ይችላሉ በማለት አስጠንቅቋል።

3፤ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሶሳ በቀጣዩ ወር ከሃላፊነት እንደሚለቁ የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ አስታውቋል። አንዋር ሶሳ፣ ከሃላፊነታቸው የሚሰናበቱት በኢትዮጵያ የተመደቡበትን ሥራ በማጠናቀቃቸው እንደኾነ ኩባንያው ገልጧል። አንዋር ሶሳ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት መሠረቱን ከጣለ ጀምሮ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት በማገልገል ላይ ናቸው።

4፤ የኤርትራ መንግሥት በኤርትራ የተመድ ልዩ ራፖርተር ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሪፖርት አጣጥሏል። ኤርትራ፣ የልዩ ራፖርተሩ ሪፖርት መሠረታዊ ችግር ያለበት፣ የኤርትራ ጠላት ከኾኑ አገራት መረጃ የሰበሰበና ብሄራዊ የውትድርና አገልግሎት የግዳጅ ሥራ እንደኾነ አድርጎ በሃሰት የሚያጠለሽ ነው በማለት ከሳለች። የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት "ተቀባይነት የሌለውን" ሪፖርት ውድቅ እንዲያደርግና በሰብዓዊ መብቶች አጠባበቅ ዙሪያ መነጋገርን እንዲመርጥ ኤርትራ ጥሪ አድርጋለች። ልዩ ራፖርተሩ፣ ሰሞኑን ስብሰባ ላይ ላለው የተመድ ሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ሪፖርቱን አቅርቧል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja