Get Mystery Box with random crypto!

እስከ ሰኔ 30 ድረስ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት አይቻልም ተብሏል በመዲናዋ አዲ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

እስከ ሰኔ 30 ድረስ የቤት ኪራይ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት አይቻልም ተብሏል
በመዲናዋ አዲስ አበባ “ከጣሪያ እና ግድግዳ ግብር ጋር በተያያዘ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑን” ደርሼበታለሁ ሲል የከተማዋ አስተዳደር አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የካቲት 30/2015 ባደረገው ውይይት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 /2015 ድረስ መጨመር የማይቻል መሆኑን መወሰኑ ይታወሳል።

በመሆኑም በውሳኔው መሰረት ማንኛውም አከራይ የቤት ኪራይ እስከ ሰኔ 30 /2015 ድረስ መጨመርም ሆነ ተከራይ ማስወጣት የማይቻል መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አሳስቧል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja