Get Mystery Box with random crypto!

'በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል፤ እግዚአብሔር ሰምቶና | ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿

"በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል፤ እግዚአብሔር ሰምቶናል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ለጥያቄዎቻችን መልስ ተሰጥቶናል::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ትናንት በሰጠነው መግለጫ “በአስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርተን ጥያቄያችንን አቅርበናል፡፡ ጥያቄያችንም አንድ ነው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር፤ በሀገሪቱ ያለው ኦርቶዶክሳውያን መብት ይጠበቅ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ንብረቷ ይጠበቅ፤ እነዚህ ካልሆኑ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ እንሄዳለን ማለታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረን ቆይታ በደንብ ተወያይተንበት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ተሰጥቶናል ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡ እንዲሁም ዝርዝር መግለጫውን ነገ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

@zemaryan