Get Mystery Box with random crypto!

#ሰበር_ዜና ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይ | ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿

#ሰበር_ዜና
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ አቀረቡ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት የተስጠ አስቸኳይ ሰበር መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች ፵፰ ሰዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፣ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያዬት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ጥሪ ማስተላለፏ ይታወሳል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሆኖም ግን ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሊሆን የሚገባ ነው በሚል በተነሳው ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የደህንነት ተሽከርካሪዎች እና የጸጥታ አካላት ብዛት ሲታይ ምእመናንን ስጋት ላይ እንዳይወድቁ እና ላልተጋባ ጉዳት እንዳይዳረጉ በማሰብ የሰላም ጥሪውን መንግሥት ከተቀበለ እና በቤተ መንግሥት መገኘቱ ሰሕዝባችን የሚያመጣው መፍትሒ የሚኖር እንደሆነ በማሰብ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችንን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት የሚገኝ መሆኑን እያሣወቅን ሕዝበ ክርስቲያኑም አባቶች የደረሱበትን ውጤት እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት ትጠባበቁ ዘንድ እናሳስባለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
=======
ማህበረ ቅዱሳን
https://t.me/mahbere_kidusan