Get Mystery Box with random crypto!

መግቦተ እግዚአብሔር

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemariyannen — መግቦተ እግዚአብሔር
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemariyannen — መግቦተ እግዚአብሔር
የሰርጥ አድራሻ: @zemariyannen
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.62K
የሰርጥ መግለጫ

"ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እሱን ያፈርሰዋል ፤የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ"
1ኛ ቆሮ 3፥17
#የማህበሩ_አላማ
የኦርቶዶክስን ቀኖና፣ዶግማ እንዲሁም ትውፊት በጠበቀ መንገድ አስተማሪ የሆኑ መዝሙሮች፣አስተምሮቶች እንዲሁም ስብከቶች እናቀርባለን።
@zemariyannengp
@Zegebreal7
ሼር በማድረግ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታዎን ይወጡ!!

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-25 20:17:28
328 viewsLil slim shady, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 21:31:16
እንኳን ለ እናታችን እመቤታችን ድንግል በ፪ኤ ማርያም ወላዲተ አምላክ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!!
ኑ! ይህን ታላቅ በዓል በጥንታዊው እና ሰሚው አቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ያከብሩ የበረከቱ ተካፋይ ይሁልኑ ስንላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
437 viewsLil slim shady, 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 06:42:38 #ሰሙነ_ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

#ሰኞ
#መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል፦
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

#አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

#ማክሰኞ
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

#የትምህርት_ቀን_ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

#ረቡዕ
#ምክረ_አይሁድ_ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

#የእንባ_ቀን_ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

#ሐሙስ
#ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

#የምስጢር_ቀን_ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

#የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

#የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

#ዓርብ
#የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

#መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

#ቅዳሜ
#ቀዳም_ስዑር_ትባላለች ፦
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።

#ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

#ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

(ስምዐ ጽድቅ መጋቢት ፳፻፪ ዓ.ም)
1.0K viewsLil slim shady, 03:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 19:59:09 #ነ_ፃ_ነ_ት

"በነፃነት ልንኖር ክርድቶስ ነፃነት አወጣን" ገላ 5፥1

ውድ ከሆኑ ነገሮች መሀል አንዱ ነፃነት ነው። የነፃነትን ትርጉም የሚረዳው ባርነትን ያየ ነው። ሰው ከሰው ጋር ያለው ግንኙነት ህይወት ያለው የሚሆነው ነፃነትን መተንፈስ ሲችሉ ነው። ነፃነት ከየትኛውም መደብር አንሸምታትም ከእግዚአብሔር ብቻ የምናገኛት ስጦታ ናት። እኛ ሰውን ነፃነት ብለን ስም እናወጣ ይሆናል እንጂ ነፃ ማውጣት አንችልም። መንፈሳዊ አዕምሮ ወይም መረዳት ያለው ሰው ማንንም ይህን እመን ያንን እመን ብሎ አይጫንም። መንፈሳዊ መረዳት ያለው ሰው ከኢየሱስ መለኪያ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ እንድንኖር ነው የሚነግረን። የተጠራነው ለሰዎች ህሊና ነፃነት እንድናቀርብ ነው። ይህ ማለት ሰዎች ለራሳቸው ሀሳብና አመለካከት ነፃ መሆናቸውን እንድንሰብክ ተጠርተናል ማለት አይደለም። እኛ ራሳችን በክርስቶስ ነፃ የማውጣት ኃይል ነፃ ከወጣን ሌሎችም ወደዚያ ነፃነት ይወጣሉ። ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የህይወታችን ጌታና ባለስልጣን እንደሆነ በማመን የሚገኝ ነፃነት ነው።

ህይወትን መለካት ያለብን በኢየሱስ ክርስቶስ መለኪያ ነው። የእርሱን ቀንበር ብቻ ለመሸከም ራሳችንን ማስገዛት አለብን። የኢየሱስ ክርስቶስ ያልሆነ ቀንበር ሌሎች ላይ እንዳንጭን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል። የኛን አመለካከትና አስተሳሰብ የማይቀበሉ ሁሉ እንደተሳሳቱ የማሰብ ዝንባሌ አለን ይህ የኛ እንጂ የእግዚአብሔር ሃሳብ አይደለም። እኛ ለራሳችንም ለሰዎችም ትዕግስት የለንም። ነፃ የሚያወጣው ወንጌል በአርባ አመታችን ይሆናል እኛ ግን ለሰዎች ዛሬ መስክረን ዛሬውኑ ካላመኑ እንላለን የፈጀነውን ዘመን አንርሳ እንጂ!

በሌሎች ላይ በቀላሉ መመረር የለብንም ትዕግስታችንም ሊሟጠጥ አይገባውም። እግዚአብሔር እኛን የተሸከመን በትዕግስቱና በምህረቱ መሆኑን አንዘንጋ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ " ሂዱና ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው" ማቴ 28፥19 አለ እንጂ የራሳችሁ አስተሳሰብና አመለካከት አድርጓቸው አላለም።
726 viewsLil slim shady, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-19 13:34:42 አባትነት

“ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ ፥ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፡- እነሆኝ ፥ እነሆኝ አልሁት ።” ኢሳ. 65 ፡ 1 ።

ሰፈሩ ለድሮ በቀበሌው ስም ይጠራ ነበር ። በ13 እና በ14 ቀበሌ መካከል ያለው መንገድ ምቹ ያልነበረ ፣ ለማየትም የሚማርክ አልነበረም ። ከመንገዱ ቤቶቹ የተሻሉ ነበሩ ። ዘመን ሰለጠነና እንደ ቅቤ ያለ መንገድ ተሠራ ። መንገዱ ሲሠራ የገባው ሥልጣኔ ብቻ ሳይሆን ኃጢአትም ሆነ ። ታዲያ ሰፈሩን “ቺቺንያ” ብለው ሰየሙት ። ትርጉሙን ብጠይቅ በቺቺንያ ጦርነት ሕፃናት ይሳተፉ ነበርና በዚህም ሰፈር ሕፃናት ለዝሙት ንግድ ተላልፈው ተሰጥተዋል ፤ ስለዚህ ሰፈሩ “ቺቺንያ” ተባለ የሚል መልስ አግኝቻለሁ ። ያንን አካባቢ የማውቀው በ1986 ዓ.ም. ጀምሮ ነው ። እግዚአብሔርን የሚወዱ ፣ ሰውንም የሚወዱ ሰዎች እንደ ነበሩበት አስታውሳለሁ ። አቅም የነበራቸው ወጣቶችም ነበሩበት ። ታዲያ ከሁለት ቀን በፊት በዚያ “ቺቺንያ” ተብሎ በተጠራው ሰፈር ጎዳና ላይ በመኪና ሳልፍ ድንገት አንድ አባት ሕፃን ልጅ ይዞ መልሶ ደግሞ እያቀፈ ቀጥሎ እያወረደ በቅጽበት አየሁ ። አባቱን ሳየው ዕድሜው 35 ዓመት ቢሆነውም ያለ ጊዜው ግን አርጅቷል ። መልኩ ክልስ ይመስላል ። መልሶ ደግሞ ጠቍሯል ። መለስ ብዬ ልጁን ሳየው ሕፃኑ ጠይም ነው ። በጠይምነት ጀምሮ በጠይምነት የቀጠለ የ6 ዓመት ልጅ ቢሆን ነው ። አባቱን ኑሮ ያጠቆረው መሆኑን አረጋግጬ ልጁን መልሼ ያየሁት ምናልባት የእኛው አየር ንብረት ያጠቆረው ሶርያዊ ይሆን ብዬ ነው ። በቅጽበት የሰማሁት የአባትና የልጅ ንግግር ግን ኢትዮጵያዊ እንደሆኑ መሰከረልኝ ። ያ አባት በዓይኔ በቅጽበት ውስጥ ገባ ። የለበሰው ሙሉ ልብስ ውድ ልብስ ነው ። ነገር ግን ከወለቀ ብዙ ጊዜው ሆኖ ደክርቷል ። ያ አባት የሆነው ወጣት መልኩ በቀይ ጀምሮ እንደነበር እርግጠኛ ነኝ ። አሁን ግን ጠይም ቢሆን ሂደት ነበር ። የቀይ ዳማ ቢሆንም በቅላትና በጠይምነት መካከል ነው ። ነገር ግን አመድማና መግለጥ የማይቻል መልክ ይዟል ። እስቲ የውኃን መልክ ግለጹልኝ ፣ ያ ወጣትና አባትም እንዲሁ ነው ። ኑሮ በደንብ እንደ ጎዳው ያስታውቃል ። ጥርሶቹ ተጎድተዋል ፣ ለመቦረሽም እድል አላገኙም ። ጫማው አዘንብሏል ። አሁን ያለው ሀብት ፍቅር ብቻ ይመስላል ። ልጁ ሲከብደው ያወርደዋል ፣ መልሶ ፍቅሩ አላስችል ብሎት ይሸከመዋል ። ልጁ የጫጨ ቢሆንም ለአቅመ ደካማው ወጣት አባት ግን ከባድ ነበረ ። አካሉ የተሟላ አባት ነው ፣ አቅም ግን ጥሎት ከሄደ የሰነበተ ይመስላል ። ማናልባት ሱስ ይሆናል ካላችሁ እኔ ግን አልመሰለኝም ። የአባቱ አቅም እንደ ተዳከመ ልጁ አያውቅም ። ልጁ የሚያውቀው አባቱ አፍቃሪና ኃያል መሆኑን ብቻ ነው ። አዎ አባቱ አፍቃሪ ነው ፣ ግን በጊዜ ደክሞታል ። በዕድሜ ሳይሆን በኑሮ አርጅቷል ። ያንን አባት ለማወቅ ቤቱን ማየት አያስፈልግም ፣ ቁመናው ቤቱን ያሳያል ።

መገመት መልካም ነው ። ይህ የተዋበ አባት በውበት ጀምሮ በመወየም እየደመደመ ነው ። በቅላት የሚያውቀው ሰው ብዙ ይኖራል ። አሁን ግን አመድማም ከሰልማም ለመባል አስቸጋሪ ሁኗል ። ሳየው አዘንኩለት ። ማግኘትና ማጣትን የሚያውቅ ሰው ፣ በልዑልነት ጀምሮ የባሪያን መልክ እንኳ ያጣ ወገን ብቻ የሚያውቀው ሰው ነው ። መኪናው ለቅጽበት ቆም ያለው ከፊት ለፊቱ ጭንቅንቅ ስለነበረ ነው ። ይህን ሰው ያየሁትም የሰማሁትም ከአንድ ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ነው ። ልጁን ቁልቁል እያየ ምነው በኖረኝ ? የሚል ስሜት ይታይበታል ። ልጁንም ሳብ አድርጎ ወደ ላይ ካወጣው በኋላ አቀፈው ። ልጁም ከፍ ያለው ማማ ላይ ሲወጣ ዓይኖቹ ማዶ ላይ አሻግረው የተዋቡ ጫማዎች የሚሸጥበት ሱቅ ላይ አረፉ ። ውድ ቤት እንደሆነ ሱቁም ጫማውም ይናገራል ። ልጁ ግን፡- “አባ” አለው ። አባትም እንደ ልጁ ጮክ ብሎ ሳይሆን ዝቅ አድርጎ መለሰ ። የአባትነት ስሙ እንጂ አቅሙ የለኝም ብሎ ይሆናል ። ልጁ “አባ” አለ፡- “አቤት” በማለት በዝቅታ ፣ በኀዘኔታና በፍቅር ድምፅ መለሰለት ። ልጁ እጁን እየጠቆመ “አባ ጫማ ግዛልኝ” አለው ። ያ አባትም፡- “እሺ እገዛልሃለሁ” አለው ። የአባት መልስ ልጁን ቢያሳርፈውም አባት ግን ያረፈ አይመስልም ። አነጋገሩ እንደማይገዛ ያሳያል ። ግን ድምፀቱን ወደ ኋላ እየፈተሽኩ ስሰማው አንድ ቀን እገዛልሃለሁ ፣ እንደ መሸ አይቀርም የሚል ነው ።

መንገዱ ተለቀቀና መኪናው አፈተለከ ። እኔም ያንን አባትና ልጅ በአሳብ ይዣቸው ወደ ቤቴ ገባሁ ። አሁንም ፊት ለፊቴ ይታዩኛል ። ጥጋብ ሰውን ቢፈትንም ማጣት ግን ከዚያ በላይ ፈታኝ ነው ። ለወለዱት ልጅ መስጠት አለመቻል ትልቅ ሕመም አለው ። ስሙን ተሸክሞ በተግባር አባት መሆን ሲሳን ቁጭት አለው ። “እሺ እገዛልሃለሁ” አለ ። ልጁም አጭር የማስታወስ አቅም ስላለው ይረሳዋል ። በተስፋ ግን ደስ ብሎታል ። ጥያቄዬ ተመለሰ ብሎም ዝም ብሏል ። ያ አባት ግን የልጁ ጥያቄም የራሱ መልስም ሲያጫውተው ይውላል ።

ያ ልጅ ጠይቆ ማግኘት አልቻለም ። አባቱ ፈቃድ ቢኖረውም አቅም የለውም ። እግዚአብሔር ግን ላልጠየቁት ሕይወትን ፣ ብርሃንን ፣ የዛሬዋን ቀን ሰጥቷል ። ከሁሉ በላይ ቃሉንና ልጁን ክርስቶስን ሰጥቶናል ። ሳንለምን በተቀበልነው ነገር ውስጥ ለምነን ያላገኘናቸውን ነገሮች አስቡ ። ሦስት ነገሮች ብልጭ ይላሉ ። የመጀመሪያው፣ ሳንለምን የተቀበልነው ውድ ነገር ነው ። ሁለተኛው፣ ለምነን የከለከለን ፣ ጌታችን ክፉ ስለሆነ ሳይሆን ዓላማ ስላለው ነው ። ሦስተኛ፣ የተሰጠን ከሚሰጠን የሚበልጥ ነው ።
679 viewsLil slim shady, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 18:28:41
522 viewsLil slim shady, 15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 21:18:01
686 viewsLil slim shady, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-05 16:19:36
781 viewsLil slim shady, 13:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-01 22:07:59 ዘወረደ

( የዐቢይ ጾም አንደኛ ሳምንት )

ዘወረደ ትርጕሙ ‹ከሰማየ ሰማያት የወረደ› ማለት ነው፡፡ ከሰማየ ሰማያት የወረደውን፣ ከድንግል ማርያም የተወለደውን በጥንት ስሙ ወልድ፣ ቃል በኋላ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አማኑኤል የተባለውን ሰው የኾነውን አምላክ ለማመስገን ርደቱን (ከሰማየ ሰማያት መውረዱን) ለመዘከር የሚጾም ጾም ነው፡፡ ጌታችን ጾመ ከማለት አስቀድሞ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን መናገር አስፈላጊ ነውና የመጀመሪያው ሳምንት ‹ዘወረደ› ተብሏል፡፡ ‹‹አንተ በሰማይ ወአንተ በምድር ወአንተ በባሕር ወአንተ በየብስ፤ አንተ በሰማይ አለህ፤ በምድር በባሕርም በየብስም አለህ፤››የተባለውን በሰማይ በምድር ምሉዕ የኾነውን አምላክ ‹ወረደ፤ መጣ› ብሎ መናገር ‹ሰው ኾነ› ማለት ነው

ሰው ኾኖ መገለጡን ለማስረዳት ነው እንጂ መውረድ መውጣት የሚባሉ ቃላት በዅሉ ምሉዕ ለኾነው መለኮት አይስማሙትም፡፡ ቃላቱ ሰውኛ አነጋገርን የሚያመለክቱ ናቸውና፡፡ መተርጕማን አበው ‹‹‹ዘወረደ› ማለት ‹ሰው የኾነ› ማለት ነው›› ብለው ይተረጕማሉ፡፡ አምላካችን ሰው ከኾነ በኋላ ‹መጣ፤ ሔደ፤ ወረደ፤ ዐረገ› የሚሉ ቃላት ይስማሙታል፡፡ ምልዓቱን ሳይለቅ በሰው አካል ተወስኖ ታይቷልና፡፡ ስለዚህ ‹ወረደ› እግዚአብሔር ሰው ኾኖ መገለጡን፤ ‹ዐረገ› ደግሞ የሰውነቱን ሥራ መፈጸሙን ያሳያል፡፡ ዐረገ ስንልም ቀድሞ በሰማይ የለም ለማለት አይደለም፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ በዓለሙ ዅሉ ምሉዕ ነውና፡፡

ጾሙን ሐዋርያት፣ ስያሜውንና የምስጋናውን ሥርዓት ቅዱስ ያሬድ አዘጋጅተዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ነቢያትን በንባብ፤ ሐዋርያትን በስብከት፤ ሊቃውንትን በትርጓሜ፤ መላእክትን በዜማ ይመስላቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ የመላእክትን የምስጋና ሥርዓት ወደ ምድር አምጥቷል፡፡ የነቢያትን ትንቢት፣ የሐዋርያትን ትምህርት በሚገባ ተርጒሞ፣ አብራርቶ፣ አመሥጥሮ አዘጋጅቶታል

ሐዋርያት ጾሙን ጾመው የጾም ሕግ ደንግገዋል፤ ቅዱስ ያሬድም ለጾሙ ስያሜ ሰጥቶ ምስጋና ከነሥርዓቱ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡ቤተ ክርስቲያናችንም የመጀመሪያው የዐቢይ ጾም ሳምንትን (ዘወረደን) ስያሜ እንደ ቅዱስ ያሬድ ከሐዋርያት ተቀብላ ታስተምራለች፡፡ ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ614 ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ያላወቁ ‹ጾመ ሕርቃል› ብለው አንድ ጊዜ ጾመው ትተውታል፡፡ ጥንቱን የቅዱሳን ሐዋርያት መኾኑን ያወቁ ምእመናን ግን ዅልጊዜ በየዓመቱ ይጾሙት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ 15 ላይ ይገኛል
837 views.........., 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 20:43:24 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
እንኳን ጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዐብይ ጾም (ጾመ ኢየሱስ) በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!!

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን 40 ቀን እና ሌሊት ጾመ፤ እኛስ ለምን 55 ቀን እንጾማለን?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን 40 ቀን እና ሌሊት ጾመ
እኛስ ለምን 55 ቀን እንጾማለን

1ኛ. ነቢያት 40 ቀን ጾመዋልና 40 ጾመው ትንቢት የተናገሩለት ስለ እርሱ መሆኑን ለማጠየቅ

2ኛ. ቀድሞ ነቢያት 40 ቀን ጾመዋል፤ ጌታችንም ከ40 ቀን ቢያተርፍ ‹‹አተረፈ›› ቢያጎድል ‹‹አጎደለ›› ብለው ሕገ ወንጌልንም እንዲሁም ጌታን ላለመቀበል ምክንያት እንዳያደርጉ

3ኛ. ነቢዩ ሙሴ 40 መዓልትና ሌሊት ጾሞ ሕገ ኦሪትን ሰርቷል፤ ጌታችንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም 40 መዓልትና ሌሊት ጾሞ ሕገ ወንጌልን የሚሰራ ነውና፡፡

4ኛ. አዳም በ40 ቀን ያገኘውን ልጅነት አስወስዶ ነበርና ለእርሱ እንደ ካሣ ለማጠየቅ፤ እንዲሁም በ40 ቀን ተሥእሎተ መልክ ለተፈጸመለት ሰው ሁሉ ለካሣ እንደመጣ ለማጠየቅ፡፡

55 ቀናት መሆኑ

❖ ይህ ጾም አብዛኛውን የየካቲትና የመጋቢት ወራትን የሚይዝ ሲሆን የሚያዝያም ወር የሚጨምርበት ጊዜ አለ፤ እስከ ቀዳም ስዑር ለ55 ቀናት ይጾማል፡፡

❖ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ለ40 ቀናት ሲሆን እኛ ለ55 ቀናት የምንጾምበት ምክንያት በ55 ቀን ውስጥ 8 ሳምንታት (8 ቅዳሜና 7 እሑድ) ይገኛሉ፡፡

❖ አንድ ላይ አሥራ አምስት ቀናት ይሆናሉ፤ እነዚህን ሰንበታት ከጥሉላት (ሰውነትን ከሚጠግኑ) እንጂ ከእህልና ከውኃ ስለማይጾም የእሑድና የቅዳሜን ምትክ አስራ አምስት ቀናት ተጨምረው ይጾማሉ፡፡

በተጨማሪ
❖ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ይህ መታሰብያ ይዘከራል እስከዛሬ ድረስ ከጾመ 40 በፊት ያለው የ1 ሳምንት ጾም (ዘወረደን) ስንጾም እንኖራለን።

❖ ሕርቃል (አራቅሊዮስ) የበዛንታይን ንጉሥ ነበረ 614 ዓ.ም፤ ይህ ሳምንት በስሙ የተጠራበት ምክንያት በዘመኑ ፋርሶች ኢየሩሳሌምን ወርረው የጌታችን መስቀል ማርከው ወስደው ነበር ሕርቃልም በ628 ዓ.ም ወደ ፋርስ ዘምቶ ኮሰሮየን ድል አድርጎ የጌታችንን መስቀል አግኝቶ ሲመለስ መስቀሉን እርሱ እራሱ ተሸክሞ ከፋርስ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ አለጫማ በእግሩ እየሄደ አምጥቶ ለኢየሩሳሌም ምዕመናን አስረከበ።
❖ የኢየሩሳለም ምዕመናን፣ ኤጲስ ቆጶሳትና ካህናቱም በጣም ተደስተው ስለነበር ስለ እርሱ ብለው ሰባት ቀን ሙሉ በጾምና በጸሎት የያዙትን ሱባኤ ከጌታችን ጾም ጋር ሆኖ በየአመቱ ሰባት ቀን እንዲጾም አዘዙ።

❖ ስለዚህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ይህ መታሰብያ ይዘከራል እስከዛሬ ድረስ ከጾመ 40 በፊት ያለው የ1 ሳምንት ጾም(ዘወረደን) ስንጾም እንኖራለን።

❖ ሌላው ደግሞ ሰሞነ ሕማማት የመጨረሻው ሳምንት ስሆን ይህን ሐዋርያት የጌታችን ነገረ መስቀል ስቃዩን ግርፋቱን ስቅለቱን ሞቱን እያሰቡ የፆሙት ሳምንት ነው።

❖ ስለዚህም እኛም የሐዋርያትን ፈለግ ተከትለን የጌታችንን መከራውን ስቃዩን መገረፉን መሰቀሉን መሞቱን እያሰብን እንጾማለን፤ እነዚህ ሁለት ሳምንታት (ጾመ ሕርቃል እና ሰሞነ ሕማማት) ስጨመሩ 55 ቀን ይሆናል።

በእነዚህ 55 ቀናት ውስጠ ስምንት ሳምንታት አሉ፤ ስያሜአቸውና ትርጉም በቅደም ተከተል
❖ 55 ቀናት 15 ቀናት- 7 እሁድ እና 8 ቅዳሜ 40 ቀናት
1ኛ ሳምንት
❖ ዘወረደ- የክርስቶስ ከሠማይ መውረድ
2ኛ ሳምንት
❖ ቅድስት- የሰንበት ቅድስና
3ኛ ሳምንት
❖ ምኩራብ- ክርስቶስ በምኩራብ ስለማስተማሩ
4ኛ ሳምንት
❖ መፃጉ- ክርስቶስ በሽተኞችን መፈወሱ
5ኛ ሳምንት
❖ ደብረዘይት- በዚህ ተራራ ስለ ዳግም ምጽአቱ ማስተማሩ
6ኛ ሳምንት
❖ ገብርሔር- ለደግ አገልጋይ ዋጋ ያለው መሆኑ
7ኛ ሳምንት
❖ ኒቆዲሞስ- ጌታ ከኒቆዲሞስ ጋር መነገጋሩ
8ኛ ሳምንት
❖ ሆሳዕና- እየተመሰገነ ወደ ቤተ-መቅደስ መግባቱና ስለ እኛ ህማማትን መቀበሉ ይታሰብበታል

እነዚህ 55 ቀናት ለሦስት ይከፈላሉ
1ኛ. ዘወረደ
2ኛ. የጌታ ጾም (አርባ ቀን) ከቅድስት እስከ ሆሳዕና ያለው
3ኛ. ሰሙነ ሕማማት

እስከ ስንት ሰዓት እንጹም
❖ ቅዱሳን አባቶቻችን ከሌሎቹ አጽዋማት በተለየ ሁኔታ በዓቢይ ጾም እስከ ስንት ሰዓት መጾም እንዳለብን በመጽሐፈ ነገሥት በመጀመርያው አንቀጽ ቁጥር 15ላይ ልዩ ሥርዓት ሠርተውልናል፡፡ ይህም

1ኛ. ዘወረደን ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ (አሥራ ሁለት ሰዓት)

2ኛ. ከቅድስት እስከ ኒቆዲሞስ እስከ 11(አሥራ አንድ) ሰዓት ድረስ

3ኛ. በሰሙነ ሕማማት ከዋክብት እና ጨረቃ እስኪታዩ ድረስ (ማታ 1፡00)

4ኛ. አክፍሎት
❖ የተቻለው ከጸሎተ ሐሙስ እስከ ትንሳኤ፤ ያልተቻለው ደግሞ ከስቅለት እስከ ትንሳኤ ማክፈል እንደሚገባ ከዚህ ሥርዓት አብልጦ የጾመ ዋጋው እንደሚበዛለት አስፍረውልናል፡፡

ጾሙን መድኃኒተ ሥጋ መድኃኒተ ነፍስ የምናገኝበት ያድርግልን፡፡ አሜን፡፡
1.8K views.........., 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ