Get Mystery Box with random crypto!

ፈራን የነገን ቀን ፈራን የስጋን ሞት ጠላን ስለ ዝምታ ናፈቅን ምን ይሆን ስንል አለቅን ያለጋሻ | የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

ፈራን
የነገን ቀን ፈራን
የስጋን ሞት ጠላን
ስለ ዝምታ ናፈቅን
ምን ይሆን ስንል አለቅን
ያለጋሻ በዝምታ
ያለ ከልካይ በጭርታ
ጠላታችንን ባናውቀው
ልባችን መኖር ጨነቀው
ደም ሳናፈስ ጨዋ ሳለን
ባለ ጊዜን እንፈራለን
ባለ ጥይት እንሸሻለን
የእኛን ሰዎች ለመከለል
ደረት እንጂ ጋሻም የለን!
ይህን ስናውቅ እንፈራለን!

ቆንጂት ጌታቸው
ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

ለመቀላቀል

t.me/zemaritnsae
t.me/zemaritnsae
t.me/zemaritnsae