Get Mystery Box with random crypto!

መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemariann — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemariann — መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪
የሰርጥ አድራሻ: @zemariann
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.23K
የሰርጥ መግለጫ

@zemarian የቀደመው ቻናል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር @zemariann ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት ..@zemariiii_bot

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-01-18 22:48:59 የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡ ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡
@zemariian
በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ

ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡ የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጇ ወደ ወዳጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡ እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን አቆይተሃል›› አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡
‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?››
ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል ፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23) በመሆኑም ጌታ አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡ ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡፡ ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡ ይህ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡፡ለአብነት ይሆን ዘንድ ጥቂት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት፡-
የሰራፕታዋ ሴት በ 1ነገ 17÷18 ላይ እንደምናገኘው ልጇ በሞተባት ጊዜ ኤልያስን በሐዘን በለቅሶ እንዲህ ብላ ነበር ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› ትወልጃለሽ ብለህ የወለድኩት ልጅ ምን በድዬህ ምንስ አስከፍቼህ ሞተብኝ? ስትል ነው እንጂ አባባሏ የንቀት ወይም የማቃለል አይደለም፡፡
በጌርጌሴኖን አንድ አጋንንት ያደረበት ሰው ወደ ጌታችን ቀርቦ ‹‹የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› አለው፡፡ እውነት ይህ ቃል የንቀት ይመስላልን? የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ብሎ አምላክነቱን እየመሰከረ ሊያቃልለው ይችላልን? ደግሞስ ላለመጥፋት ፍፁም የሚፈልግ ሰው ሊያድነው ሥልጣን ያለውን ሊንቅ ይችላልን? አይችልም፡፡
@zemariian
ይህ ቃል የሚያመለክተው ምን አጠፋሁ ስለምን ልታጠፋኝ ወደድክ በማለት መፍራት መራዱን ነው፡፡ (ሉቃ 8÷28-29)
ስለሆነም ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለው የንቀት አለመሆኑን ከሁለቱ ጥቅሶች መረዳት እንችላለን፡፡ እመቤታችን እና ጌታ በንግግር አልተቃረኑም ንግግራቸው የፍቅር ነበር፡፡ ንግግራቸው የመግባባት ስለነበር ነው
@zemariian
!‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?››!

ካላት በኋላ ዘወር ብላ አገልጋዮቹን የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ያለችው፡፡

‹‹ጊዜዬ አልደረሰም››
ጌታ ይህን ቃል የተናገረው ስለ ብዙ ምክንያቶች ነው፡፡
ይህም ጊዜዬ አልደረሰም ማለቱ፡-
እግዚአብሔር ነገሮችን የሚያከናውንበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ተአምር የምፈፅምበት ጊዜዬ አልደረሰም ሲል ነው፡፡
ጋኖቹ ውስጥ የቀረ ወይን ስለነበረ ባለው ላይ አበርክቶ እንጂ ውኃውን ወደ ወይን አልለወጠውም እንዳይሉ ወይኑ ከጋኑ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡
ይሁዳ ከሠርግ ቤት ወጣ ብሎ ነበርና ወደ ሠርግ ቤቱ እሰኪመለስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡ ይሁዳ በቃና የገለጠውን ምስጢር ለእኔ ስላላሣየኝ ተከፍቼበት ከተአምራቱ ቢያጎድለኝ በሞቱ ገባሁበት፤ ሸጥኩት እንዳይል ምክንያት ለማሳጣት እንዲህ አድርጓል፡፡
እውነተኛ የሕይወት ወይን የሆነውን ደሜን የምሠጥበት ጊዜ ገና ነው ሲል፡፡
የድንግል ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሣለ የወይኑን ማለቅ የማይመለከት ሆኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን የእናቱን የድንግል ማርያምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለወይኑ ማለቅ እስክትነግረው ድረስ አንዳች ነገር አላደረገም፡፡ ኋላ ግን የጭንቀት አማላጅ ድንግል ማርያም ስለ ወይኑ አሰበች ልጇ ወዳጇን ለመነች፡፡ እርሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈፀመ፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሣይነግሯት በልብ ያለውን የምታውቅ የምትመረምር እናት ናትና የሠርጉ አስተናባሪዎች ይሄ ጎደለ ሣይሏት የልቦናቸውን ሐዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች፡፡ ያስጨነቃቸውንም አርቃለች፡፡ በችግራቸው ደርሳላቸዋለች፡፡

ታዲያ ሳይነግሯት የልቡናን አይታ ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትም እንዴት አብልጣ አታማልድ?
ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን በረከቷን ያሳድርብን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር


መልካም የከተራ በዓል ፤
መልካም ጥምቀት ፤
መልካም ቃና ዘገሊላ ።
17.0K views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 22:48:56 በመቀጠል ከ1426-1460 ዓ.ም ለ34 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በታላቁ ንጉሥ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥትም ንጉሡ ከሊቃውንት ጋር በመወያየት የበዐሉን ታሪክ ተከትሎ ታቦታቱ ጥር 10 ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት

እንዲወርዱና ጥር 11 እንዲመለሱ ተወሰነ።
@zemariian
ታቦተ ጽዮን በሄደችበት ሁሉ በረከትን ትሰጥ እንደነበር የአቢዳራን ቤት በበረከት እንደሞላች፤ የዮርዳኖስን ባህር እንደከፈለች፣ የኢያሪኮን ቅጽር እንዳፈረሰች፣ የፍልስጤማውያን ጣዖት ዳጎንን ቀጥቅጣ እንዳጠፋች ሀገሪቱ ትባረክ ዘንድ ርኲሳን መናፍስት ይርቁ ዘንድ ምድሪቱ በቃል ኪዳኑ ታቦታት ትቀደስ ዘንድ ታቦታቱ በመጡበት መንገድ እንዳይመለሱ ታላቅ ዐዋጅ አሳውጀው በዐዋጁ መሠረት ዛሬ ድረስ በደመቀ መልኩ በዓሉ እየተከበረ ይገኛል፡፡
ከባሕር ማዶ ሰዎች ውስጥ ቼሩሊ በዐጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ቁመቱ 14 ወርዱ 8 ክንድ የኾነ ባሕረ ጥምቀት እንደተዘጋጀ ሲጽፍ፤ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዐጼ ልብነ ድንግል በተገኙበት እጅግ ታላቅ ድንኳን በባሕረ ጥምቀቱ ዙሪያ እንዴት ተተክሎ እንደተከበረ ፍራንቺስኮ አልቫሬዝ ሲጽፍ፤ በ17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረውን ደግሞ ፔድሮ ፔየዝ ዘግቦት ነበር።
@zemariian
አሁን ባለንበት ጊዜም ዳዊት በመዝ 44፡16 ላይ “በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ” በማለት እንደተናገረ ከመቼውም በበለጠ እግዚአብሔር የወጣቱን ልብ በረድኤት ጎብኝቶት ለቃል ኪዳኑ ታቦታት ክብር አካባቢውን እያስዋበ፣ ታቦታቱ የሚሄዱበትን መንገድ እየጠረገ፤ ታላላቅ ምንጣፎችን ታቦታቱ በሚሄዱበት መንገድ እያነጠፈ ለቃል ኪዳኑ ታቦት እንደ ነቢዩ ዳዊት ከፍተኛ ክብር በመስጠት እግዚአብሔርን እያገለገለ ይገኛል (1ኛ ነገሥት 6፡1-23)፡፡
“የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት” (ኢያ 3፡3)

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ትምህርተ ሐይማኖት መጽሐፍ ደሞ ትንሽ ይለናል ከላይ የዘረዘርናቸውን ምሳሌነታቸውን #በጥቂቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ባህረ ዮርዳኖስ በ ቅዱስ ዮሐንስ እጅ የተጠመቀበት እና ጥምቀትን የመሰረት ምስጢር ነው
ኢየሱስ ክርስቶስ #ለምን #ተጠመቀ?
@zemariian
ኢየሱስ ክርስቶ የተጠመቀበት ዋናው ምክንያት ዳቢሎስ በ ዮርዳኖስ የቀበረውን የ እዳ በደል ደብዳቤ ለመደምሰስ ነው ደብዳቤውም የሚለው "አዳም የ ዳቢሎስ ወንድ ባርያ ነው ሔዋን የዳቢሎስ ሴት ባርያ ናት "የሚል ነበር ይህ ደብዳቤ እየሱስ ክርስቶስ በ ተጠመቀ ግዜ አጠፋው ።

የኢየሱስ በዮሐንስ መጠመቅ ለ ሁለቱም ክብር ነበር ለዮሐንስ ጌታውን ማጥመቁ
ለኢየሱስ ደግሞ በባርያው እጅ መጠመቁ ትህትናውን እንዲወራ ያደርገዋልና እየሱስም ዮሐንስ የ እግዚአብሔር አብ የባህሪ ልጅ የመንፈስ ቅድስ ቃል አንተ ነህ እያልክ አጥምቅፕኝ ባለው መሰረት እንደተባለው እጠመቀው
ዮርዳኖስ ከላይ አንድ ሆኖ መሀል ላይ ይክፈላል ደግም ዝቅ ብሎ ይገናኛል።

ከላይ አንድ መሆኑ የ አዳምና ሔዋን ልጆች መሆናችንን መከፈሉ ደግሞ የኦሪትና የወንጌል ምሳል ነው ጌታ የተጠመቀው በሚገናኝበት ነው ይህ ሚስጢሩ ኦርትን እና ወንጌልን አንድ ማድረጉ ሰውን ከመላህክት ጋር ማስታረቁን ነው።
@zemariian
#የጥምቀት_ምስጢራዊ_ምሳሌ፦

የ ኖህ መርከብ ዘፍ 7÷17 ወደ መርከቧ የገቡት ሁሉ እንደዳኑ ወደ ጥምቀት የገቡ ሁሉ ይድናሉ ያልገብ ግን ይሞታሉ።
የ አብርሃም ግዝረት ዘፍ 17÷9
ክርስቲያን ለመባል በ ብሉይ ኪዳን መገረዝ እንደሚያስፈልግ ሁሉ በ ሐዲስ ኪዳንም ክርስቲያን ለመባል መጠመቅ አለብን

የ እስራኤል ኤርትራ ባህርን መሻገር ዘፍ 14÷21 ሙሴ የኢየሱስ ምሳሌ በትሩ የመስቀል ምሳሌ ባህሩ የጥምቀት ምሳሌ እዝብ የ ህዝበ እስራኤል ምሳሌ ይሆናል ለምን እኛ በ 40 እና 80 ቀን እንጠመቃለን?
@zemariian
በ ኢትዮጱያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወንድ በ 40 ቀኑ ሴት ደግሞ በ 80 ቀኗ ታጠምቃለች ይህም የሆነው አዳም በተፈጠረ በ 40 ቀኑ ገነት ሲገባ ሔዋን ደግሞ በ 80 ቀኗ ነው ወደ ገነት የገባችሁ ።

ኩፋሌ 4÷9
ጥምቀት በ ሦስት መንገድ ሊፈፀም ይችላል ይህም •የመንፈስ ጥምቀት ይህ በ ሰው ሳይሆን በመንፈስ የሚደረግ ጥምቀት ነው ልክ እንደ ሐዎርያት ጥምቀት 1ቆሮ 12÷13
• የ ውሃ ጥምቀት ይህ ደግሞ በካህናት አማካኝነት የሚፈፀም ነው ማቴ 3÷13
• የ ደም ጥምቀት። ይህ ጥምቀት የ ሰማህታት ጥምቀት ነው ማቴ 20÷22
በስተመጨረሻ ጥምቀት ለምን በውሃ ሆነ???

ጥምቀት በውሃ ለምን ሆነ እየሱስ ክርስቶስ ለምን በውሃ ተጠመቀ ባለፀጋ ነው ለምን በወተት ወይም በማር አልተጠመቀም ?

ምክንያቱም በውሃ የተጠመቀበት
በኖህ ዘመን የሰው ልጅ በውሃ ጠፍቶ ነበር በግብፃዉያን በባህር ሰምጠው ነበር ሰለዚህ ውሃ ለመሀት ብቻ ሳይሆን ለምህረትም እንደሚሆን ለማስረዳት ነው
ማርና ወተት ሌላም በባል ፀጋ ቤት ነው የሚገኘው ውሃ ግን በ ሁሉም ቤት ስለሚገም ነው

በውሃ ካልታጠብን እንደማንነፃ እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከ ስጋና ነፍስ እድፍ ትጠራላችሁ ሲል ሲያመላክት ነው
ውሃ መልክን እንደሚያሳይ እናንተም ብትጠመቁ ስላሴን ታያላችሁ ሲል ነው።
ት/ት ሐይማኖት መጽሐፍ
#3 ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡
@zemariian
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በዋዜማው የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌ።
@zemariian
‹‹ቃና ዘገሊላ›› ምንድነው?

ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት(ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡ ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡
8.3K views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-18 22:48:51
@zemariian
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

እንኳን ለበአሉ በሰላም በጤና አደረስዎ አደረሰን እነሆ በዛሬው መርሐ ግብር ጥቂት ነገሮችን ልንነግራቹ ወደድን

#1 ጥምቀት ምንድንነው ምን ልዩ ምስጢር አለው?

#2 ከተራ ምን ማለት ምንስ ምስክር ተፈጸመ?

#3 ቃና ዘገሊላ ምን ማለት ነው?


#1_ምስጢረ_ጥምቀት?

ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ጥምቀት ማለት ቃሉ የግእዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም “መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውሃ ውስጥ ገብቶ መውጣት” ማለት ነው፡፡ ጥምቀት ማለት አንድ ሰው አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በተጸለየበትና በተባረከ ውሃ ሦስት ጊዜ ጠልቆ ዳግመኛ ከሥላሴ ተወልዶ የቤተ ክርስቲያን አባል የእግዚአብሔር ሕዝብ ወገን የሚሆንበት ቅዱስ ምስጢር ነው (ማቴ 28፡19-20)፡፡
ምስጢረ ጥምቀት ምስጢር መባሉ ካህኑ ለጥምቀት የተመደበውን ጸሎት አድርሰው ለማጥመ ቅ የተዘጋጀውን ውሃ ሲባርኩት ውሃው ተለውጦ በዕለተ ዐርብ በመስቀል ላይ ከጌታ ጎን የፈሰሰውን ውሃ ስለሚሆንና ለተጠማቂው ሰው በሚፈጸምለት የሚታይ ሥርዐት የማይታይ የልጅነት ጸጋ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሚሰጥ ነው (ዮሐ 3፡5)፡፡
ምስጢረ ጥምቀትን የመሰረተልን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ሲመሰርትም በማዘዝ ብቻ ሳይሆን በሥራ በማሳየት ጭምር ነው (ማቴ 3፡17፤ ማር 1፡9፤ ሉቃ 3፡21፤ ዮሐ 1፡31)፡፡
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እከብር አይል ክቡር የባሕርይ አምላክ ሆኖ ሳለ በዮርዳኖስ ወንዝ በአገልጋዩ (በፍጡሩ) በዮሐንስ የተጠመቀበት ምክንያት፦
1) አንድነቱን ሦስትነቱን ለመግለጽ
2) የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ
3) በእርሱ ጥምቀት የእኛን ጥምቀት ለመቀደስ
4)ለጥምቀታችን ኀይልን ለመስጠት
5) ለአብነት ርሱ ተጠምቆ እናንተም ተጠመቁ ብሎ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደ በ30 ዘመኑ ጥር 11 ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት፤ ማክሰኞ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡
ጌታችን በዮርዳኖስ እንደሚጠመቅና የዮርዳኖስ ወንዝ ጌታን ስታይ እንደምትሸሽ ነቢዩ ዳዊት በመዝ 113፡3-5 “ባሕር አየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ፤ ተራሮች እንደ ኮርማዎች፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ፤ አንቺ ባሕር የሸሸሽ፥ አንቺም ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽ ምን ሆናችኋል?” በማለት ከ1000 ዓመት አስቀድሞ ትንቢት የተናገረ ሲሆን፤ ብዙ ምሳሌም አለው፨
ምስጢሩ ግን ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ መከራ አጸናባቸው፤ ከዚያም ለኔ የባርነት ስም ብትሰጡኝ መከራውን አቀልላችሁ ነበር አላቸው፤ እነሱም “አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን አመቱ ለዲያብሎስ” (አዳም የዲያብሎስ ወንድ አገልጋይ ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው አሉ፤ ርሱም ይህንን በዕብነ ሩካም አድርጎ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል ጥሎት ነበርና፤ ጌታም በዮርኖስ ጥልቅ ወንዝ የተጣለውን የሰው ልጆች ሁሉ የዕዳ ደብዳቤ በጥምቀቱ ለማጥፋት ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡
ዮሐንስ ወደ ጌታችን መምጣት ሲገባው ጌታችን ወደ ዮሐንስ የሄደበት ምክንያት ትሕትናን ለማስተማር ሲሆን ሁለተኛው ለአብነት ለምሳሌ ነው፤ ይኸውም ዮሐንስ ሄዶ አጥምቆት ቢሆን ዛሬ ባለሥልጣናቱ ካህናትን ቤታችን ድረስ መጥታችሁ አጥምቁን ይሏቸው ነበርና ሄዳችሁ ቤተ ክርስቲያን ተጠመቁ ለማለት ሄዷል።
ዮሐንስ ግን ወደርሱ በትሕትና የመጣው አምላኩ ክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ሲል ጌታችንም “ጽድቅን ልንፈጽም” ይገባናል ብሎ ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽም እንደመጣ ሲነግረው ዮሐንስ እሺ አለ።
ከዚያም ተያይዘው ወደ ዮርዳኖስ ሲወርዱ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት እንደሚያስተምሩት የዮርዳኖስ ወንዝ 40 ክንድ ወደ ኋላዋ ሸሽታለች በዚህም ዳዊት በመዝ 77፡16 ላይ “አቤቱ፥ ውኆች አዩህ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ፥ ውኆችም ጮኹ” ብሎ የተናገረው ትንቢት ተፈጸመ።
ጌታችንም ተጠምቆ ከውሃው ከወጣ በኋላ አብ በሰማይ ኹኖ “ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ዘቦቱ ሠመርኩ” (በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው) ብሎ ሲመሰክር፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስም በጽንፈ ዮርዳኖስ ቁሞ ታየ፡፡
ይኸውም በምስጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደምንረዳው ከሰማይ ኾኖ የመሰከረው ክርስቶስ በቃልነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ያሉበት (ሕልው የኾኑበት) አብ ነው፤ ወርዶ በወልድ ራስ የተቀመጠው አብ በልቡናነት ክርስቶስ በቃልነት ሕልው የኾኑበት መንፈስ ቅዱስ ነው፤ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ የታየው አብ በልቡናነት መንፈስ ቅዱስ በእስትንፋስነት ሕልው የኾኑበት አካላዊ ቃል ክርስቶስ ነው፤ እንዲኽ አድርገው የአካል ሦስትነታቸውን የፈቃድ አንድነታቸውን ለማስረዳት አብ በአየር ኾኖ መሰከረ፤ መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ ወርዶ ታየ፤ አካላዊ ቃል ክርስቶስ በጽንፈ ዮርዳኖስ ቆሞ ታየ።
@zemariian
በዚኽም የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በሚገባ ሲታወቅ በተጨማሪም “በርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይኽ ነው” ብሎ እግዚአብሔር አብ በመመስከሩ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት የተወለደው በኋለኛው ዘመን ከእመቤታችን ያለ አባት በኅቱም ድንግልና የተወለደው እግዚአብሔር ወልድ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ብቻ መኾኑ በሚገባ ተረጋግጧል፤ ዕለቱም በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋንያ ሲባል በግእዝ አስተርእዮ በዐማርኛም የመታየት የመገለጥ ጊዜ ተብሏል፡፡
@zemariian
ኢትዮጵያ ሀገራችን ስለ ነገረ ጥምቀት የሰማችው ከሌላው ዓለም አስቀድማ ጌታችን ባረገ በጥቂት ወራት (በ34 ዓ.ም) ነው (የሐዋ 8፥26-39)፤ ይህም በዐል ከዘጠኙ ዐበይት በዐላት አንደኛው ሲሆን የታሪክ ድርሳናት እንደሚያስተምሩን ጌታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ስላመራ ይህንን ለማሰብ ታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ያመራሉ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በዚህ መልኩ መከበር የተጀመረው ከ515-529 ዓ.ም ለ14 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በአጼ ገብረ መስቀል ዘመን ሲሆን በጊዜው ቅዱስ ያሬድ የነበረበት ጊዜ በመሆኑ ከዝማሬው በመነሣት ታቦታቱ ጥር 11 ጠዋት ከመንበረ ክብራቸው ተነሥተው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አምርተው አመሻሹ ላይ ይመለሱ ነበር፡፡
@zemariian
ከዚያም ከ1157-1197 ዓ.ም ድረስ ለ40 ዓመት ኢትዮጵያን በመራው በታላቱ ጻድቅ ንጉሥ በላሊበላ ዘመን በአንድ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስትያናት ታቦታቱ ባንድ ላይ እንዲያከብሩ ንጉሥ ላሊበላ ታላቅ መንፈሳዊ ዐዋጅን አሳውጆ በአንድ አካባቢ፣ ወረዳ፣ ያሉ በአንድ ላይ ማክበር ጀመሩ፤ በርሱ ዘመን የነበሩት ታላቁ ጻድቅ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በጎንደር፣ በሸዋ፣ በአንኮበር፣ በመርጡለ ማርያም እየሄዱ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡
በመቀጠልም ከ1245-1268 ዓ.ም ለ23 ዓመት ኢትዮጵያን በመሩት በዐጼ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አሳሳቢነት ታቦታቱ በባሕረ ጥምቀት ሲውሉ ምእመናን በታላቅ ድምቀት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንዲውሉ መንፈሳዊ ዐዋጅ አሳወጁ፡፡
6.1K views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 19:51:50 ጋዜጠኞቹ ተፈተዋል
የቅደስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ ደቀ መዛሙርት ያደረጉትን ሰላማዊ ሰልፍ ለመዘገብ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ተገኝተው የነበሩ ሁለት የማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጠኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው የነበረ ሲሆን የማኅበሩ አመራሮች ባደረጉት ጥረት ሁለቱም ጋዜጠኞች ተፈተዋል።
7.1K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 19:04:29
የማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጠኞች ታሰሩ!
~~

ዛሬ ጥር 2/2014 ዓ.ም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ የሥነ መለኮት ተማሪዎች የመስቀል አደባባይ የቤተ ክርስቲያን ይዞታነትን መንግሥት እንዲያስከብር እና የሌሎች ሃይማኖቶችን ትንኮሳም እንዲያስቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ከዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አድርገው ነበር፤

ይህንን የተማሪዎቹን ሰላማዊ ሰልፍ ለመዘገብ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ቅጥር ግቢ ተገኝተው የነበሩ የማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጠኞችን ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሏቸዋል፤ ቀሪውን የጋዜጠኞቹን ሁኔታ እየተከታተልን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል::

**
6.3K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-10 19:04:28
5.1K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ