Get Mystery Box with random crypto!

#በየትኛውም_የመውሊድ_ክብረ_በዓል_ላይ_የምትታደሙ_ወጣቶች፦ 1– ሆን የተባለ ኢኽቲላጥን ተጠንቀቁ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

#በየትኛውም_የመውሊድ_ክብረ_በዓል_ላይ_የምትታደሙ_ወጣቶች፦

1– ሆን የተባለ ኢኽቲላጥን ተጠንቀቁ!

2– አረንጓዴ ሻል ሐራምን ሐላል እንደማያደርግ እወቁ!

3– ለፎቶ ብላችሁ ሴት ከወንድ አጓጉል መጠጋጋትና መተሻሸትን ራቁ!

4– በሸሪዓ ፊት ምንም ዓይነት ምክንያት ልታቀርቡ እንደማትችሉ ተረዱ!


5– በ"ሙሐባ" ስም ዑዝር የሚሰጣችሁ "እብዶች" ወይም የፈናእ ባለቤቶች አይደላችሁምና አጉል ትርኪምርኪ ሙግታችሁን ተው!

6– እልም ያለ የዳኺል ሐድራ ውስጥ ሆናችሁ እጃችሁ ለካሜራ የሚፈጥን ሰዎች፣ በስልክ ከማስቀረትና እዚያው ከመቅረት የቱ ይሻላል?

7– ትልልቆቹን ፎቶ አብሮ ለመነሳት አዛ አታድርጉ። "እምቢ" ማለት አለመቻላቸው እንደ ፍቃድ አይታይም።

8– በአጠቃላይ የመውሊድን ክብር ለመጠበቅ ሞክሩ።