Get Mystery Box with random crypto!

የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዝን ስለማሳወቅ ••••••••••••••••••••• ህገወጡ የአዲስ አበባ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የመውሊዱን ፕሮግራም መሰረዝን ስለማሳወቅ
•••••••••••••••••••••
ህገወጡ የአዲስ አበባ መጅሊስ የሚሊኒየሙን መውሊድ አስቁሙልን ብሎ ለአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ መሰረት፣ መስከረም 4/2015 ከንቲባ ፅህፈት ቤቱ በደብዳቤ የፈቀደውን የመውሊድ ፕሮግራም ሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤቱ በቃል ደረጃ የጸጥታ ችግር ስላለ አቁሙ የሚል ትእዛዝ ሰጥቷል። ነጃሺ እስላማዊ ማህበር እስከዚህ ሰአት ድረት በደብዳቤ የተፈቀደ ፕሮግራም በደብዳቤ ከልክላችሁ አሳውቁን ብሎ እየጠየቀ ያለበት ሁኔታ ላይ ቢሆንም ከሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ምላሽ ማግኘት አልተቻለም።

በመሆኑም አገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ በማየት እና ማህበረሰባችን ላይ ሊደርስ ከሚችለው ጉዳት አንፃር በጥልቀት በማየት እና በመወያየት የነገው የመስከረም 15/2015 የሚሊኒየም መውሊድ ፕሮግራም መሰረዙ ለማህበረሰባችን ደህንነት የተሻለ መሆኑን ስላመንን በአስገዳጅ ሁኔታ የነገውን የመውሊዱን ፕሮግራም ለመሰረዝ ተገደናል።

ስለሆነም በነገው እለት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ባለመሄድ ከፀጥታ አካላት ጋር በሚደረግ ግጭት በማህበረሰባችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማስቆም ግዴታችን በመሆኑ የአሽረፈል ኸልቅ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ወዳጆች ነገ ጠዋት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ባለመሄድ እንድትተባበሩን እንማፀናለን።

በረሱል ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ፍቅር እና በዑለማኦቻችን መንገድ ሕያው ነን!