Get Mystery Box with random crypto!

'19 መስጅዶች ፈርሰዋል::' የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአዲሱ የሸገር ሲ | ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

"19 መስጅዶች ፈርሰዋል::"

የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በአዲሱ የሸገር ሲቲ ከተማ አስተዳደር ከረመዳን 1 ጀምሮ የፈረሱ መስጂዶች ቁጥር 19 መድረሳቸውን አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ትናንት ግንቦት 15/2015 አዲስ አበባ በሚገኘው ዋና ፅህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ በከተማ አስተዳደሩ እየተካሄደ ያለውን የመስጂድ ፈረሳ ያወገዘ ሲሆን፤ በተለያዩ ጊዜያት ለሚመለከተው አካል አቤቱታውን ቢያቀርብም በጉዳዩ ላይ እስካሁን በጎ ምላሽ አለማግኘቱን በማንሳት ድርጊቱ አሁንም በአስቸኳይ እንዲቆም በድጋሚ ጠይቋል።በመላው ኦሮሚያ የመጭው ጁምዓ ኹጥባዎች መስጂድ ፈረሳውን የተመለከቱ እንዲሆኑ መልዕክት ተላልፏል።