Get Mystery Box with random crypto!

​​ የባከነች_ነብስ #እውነተኛ ታሪክ #ክፍል1⃣ የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ | 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂

​​ የባከነች_ነብስ
#እውነተኛ ታሪክ
#ክፍል1⃣
የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

በቀጣዩ ክፋል ያልቃል Plzzz Like

... እንግዳ ከሌለበት ሱቅ ዉስጥ አቤል ለብቻዉን ቁጭ ብሎ አገኘሁት። ገና ሲያየኝ ፊቱ ላይ የሚታየዉ ንቀትና ትዕቢት የንዴቴን መጠን በእጥፍ ቢጨምረዉም አራሴን አረጋግቼ በእናቴ ሞት ምክንያት ወደ ጅማ ሄጄ እንደነበረ አሁን ሙሉ ገንዘቡን ልከፍለዉ እንደምችልና በምትኩ እሱ ጋር ያለኝን ፎቶና ቪዲዮ እንዲያጠፋዉ ጠየኩት። እየሩስ ወደ ሱቅ ዉስጥ መግባት ስላልፈለገች ከዉጭ ቆማ እኔና አቤልን የምናደርገዉን እንቅስቃሴ ትከታተላለች።

<<አሁን ፋይሎቹን አልያዝኳቸዉም ነገ እደዉልልሽና የትና እንዴት ተገናኝተን ገንዘቡንና ፍይሉን እንደምንለዋወጥ አሳዉቅሻለሁ!>> አለኝ

<<ግን...አንተ...ሙሉ በሙሉ ፋይሎቹን እንደምትሰጠኝና አንተ ጋር ኮፒ እንደማይኖር ምን ማረጋገጫ አለኝ?>>

<<ማረጋገጫ አይኖረኝም! አንቺ ግን ያለሽ ብቸኛ አማራጭ እኔን ማመን ብቻ ነዉ!>>
ዉስጤ ያለዉ የጥላቻና የበቀል ስሜት አንጀቴ ሲያላዉሰዉ ይታወቀኛል
<<ስለየትኛዉ እምነትና መታመን ነዉ የምታወራዉ ከሀዲ!!>> ብለዉ ዉስጤ ያለዉ ህመም በትንሹም ቢሆን እርጋታ እንደሚያገኝ ባዉቅም ቸኩዬ ነገሮችን ማበላሸት ስላልፈለኩ

<<እሺ!>> አልኩት!

<<ምንም አይነት ብልጠት ወይም ደግሞ ተንኮል አስባለሁ ብትዪ አሁን ካለሽበት ሁኔታ የባሰ መቀመቅ ዉስጥ እንደምከትሽ አትርሺ!>>
በእናቴ ሞት የተሰማኝ ሀዘን ላይ ሲያንጓጥጥ መመልከቱ ከሞትም በላይ ሞት ቢሆንም ያለኝ ብቸኛ አማራጭ ትዕግስት ስለነበረ የሚናገራቸዉን ንግግሮች እየመረረኝም ቢሆን መዋጥ ግዴታ ሆነብኝ። በግምት በእድሜ አቻ ልትሆነኝ የምትችል ጠቆር ብላ የደስ ደስ ያላት ወጣት ሴት ወደ ሱቁ ገብታ በፓስታ የታሸገ ነገር አቀበለችዉ አቤል ደግሞ በምትኩ የሚሞሪ ካርድ ሲሰጣት ተመለከትኩ! ፊቷ ላይ ይታይ የነበረዉ ሀዘንና ተስፋ መቁረጥ እሷም እንደኔ የጥቃቱ ሰለባ ስለመሆኗ ምስክር ነበር። <<እስከመች?>> አልኩኝ በዉስጤ! ለሴት ልጅ ህመምና ሀዘን እየሰጠ በምትኩ ገንዘብ እየተቀበለ የሚኖረዉ እስከመች ነዉ?

<<ነገ ከሰአት 8:00 ሰዓት ላይ የምትችል ከሆነ እዚሁ ሱቅ መጥቼ ገንዘቡን ላቀብልህና ፋይሎቹን ስጠኝ?>>
<<እደዉልልሻለሁ!>> ብሎ አሰናበተኝ! ከእየሩስ ጋር ተያይዘን ወደ ቤት ተመለስን
አክስቴ ፈቃደኛ ባትሆንም በብዙ ልመናና ለቅሶ ከጅማ ሽጬ ከመጣሁት ገንዘብ ላይ የተወሰነዉ በእናቴ ስም የሚጠራና በአክስቴ ባለቤትነት የሚተዳደር ሆቴል አዲስ አበባ ዉስጥ እንድትከፍት አስማምቼያት የተቀረዉን ገንዘብ የእናቴ የዘወትር ህልም የሆነዉና ሳትፈፅመዉ ሞት የቀደማት የእርዳታ ድርጅት መክፈት በእኔ አቅም የማይቻል ስለሆነዉ ገንዘቡን ለእርዳታ ድርጅት ለመስጠት መወሰኔን ገለፅኩላት!
<<ስለ እራስሽም የነገ ህይወት ማሰብ ይኖርብሻል?>>

<<አስቤያለዉ አክስቴ አሁን ለእኔ ገንዘብ ሳይሆን ማረፊያ ነዉ የሚያስፈልገኝ የማይከፈልበት ማረፊያ!>>

<<አልገባኝም!>>

አክስቴ እንደማይገባት አዉቃለሁ ሊገባትም አይችልም እኔ ግን ነግቶ ነገ ላይ ለመቆም ልቤ ቆሟል ሁሉም ነገር ፍፃሜዉን ሊያገኝ አንድ ምሽት ብቻ ፊት ለፊቴ ተደንቅሯል እንዳረጀ ዉሻ ሂድ ብሎ ይህንን ምሽት በካልቾ መቶ የሚያባርርልኝ ማን ይሆን? ማንም!
<<አይገባሽም አክስቴ ተይዉ!>>...

............. ይቀጥላል..........
plzzz 60 Like
ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ @Abusmovies አድርሱን


Join&share
@Zeget77
ማንበብ ባህላችን ይሁን