Get Mystery Box with random crypto!

​​ የባከነች_ነብስ #የመጨረሻው ክፍል እነሆ #ክፍል1⃣ የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ | 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂

​​ የባከነች_ነብስ
#የመጨረሻው ክፍል እነሆ
#ክፍል1⃣
የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

የመጨረሻው ክፍል

... <<...ግንቦት 9 ቀን 2004 ዓ/ም ፍርድ ቤቱ በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ ወ/ሪት ቤዛዊት አለሙ በፈፀመችዉ የከባድ ነብስ ማጥፋት ወንጀል ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ ወንጀለኛዋ የፈፀመችዉ ድርጊት ኢሰብአዊ በመሆኑ እንዲሁም ድርጊቱን የፈፀመችዉ በበቀል ተነሳስታ በመሆኑ በተጨማሪም በቀረበዉ የሰዉና የሰነድ ማስረጃ ወንጀለኝነቷ በመረጋገጡ በ 15 ዓመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኗል!>>

እንግዲህ ዓለም እንዲህ ናት ሚዛናዊ መሆን ይከብዳታል መንፈስና ሞራሌ ሲሰበር ማስረጃና ምስክር የጠየቁኝ ሁሉ ዛሬ እኔን በአደባባይ ለመወንጀልና ለእስራት ለመዳረግ ተሽቀዳድመዋል። አዎ እኔ አቤልን ገድዬዋለሁ የገዛ ሱቅ ዉስጥ በስለት ከ ሰባት ጊዜ በላይ ወግቼ ገድዬዋለሁ እዉነቱን መካድ አልችልም አልክድምም! የእኔና የእሱ ልዩነት አንድ ነዉ እሱ በክፋት ልቤን ወግቶ ክፉኛ አቁስሎኛል እኔ ደግሞ በስለት ወግቼ ከምድር አሰናብቼዋለሁ። በተፈረደብኝ ዉሳኔ ብቻ ሳይሆን በፈፀምኩት ወንጀል ከእየሩስ በስተቀር ሁሉም ዘመዶቼ ፊታቸዉን አዙረዉብኛል ለእኔ ግን ህይወት ፊቷን አዙራ ከጋተችኝ የመከራ ፅዋ የእነሱ ከእኔ መሸሽ ጋር ሲተያይ ዋጋ ቢስ ይሆንብኛል። ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቴ በፊት ካረፍኩበት የፓሊስ ጣቢያ ጊዜያዊ እስር ቤት እየሩስ ለመጨረሻ ጊዜ ልትጠይቀኝ መጣች። ገና ከፊት ለፊቷ ስቆም እንባዋን መቆጣጠር አቅቷት አምርራ አለቀሰች
<<እየሩሴ ለምን ታለቅሺያለሽ? ለምን? የንፁህ ሴቶችን ህይወት እያበላሹ በኩራት ደረታቸዉን ነፍተዉ ከሚራመዱ በርካታ ወንዶች መካከል እኔ መቀነስ የቻልኩት አንዱን ብቻ ነዉ! ፍርድና ዉሳኔ የፈጣሪ መሆኑን ባልክድም እሱ ላይ ባደረኩት ነገር ቅንጣት ታክል ፀፀት አይሰማኝም! በእኔ መንገድ ባይሆንም በደለኞችን የማጋለጥና ለንፁሀን የመቆም ሀላፊነት እንዳለብሽ ለደቂቃ እንኳን መዘንጋት የለብሽም!>>

እየሩስ አትሰማኝም! ወይም ደግሞ መስማት አትፈልግም! አልያም ደግሞ የምናገረዉ እያንዷንዷን ቃል ከልቧ እያተመችዉ ይሆናል! ብቻ እንቧዋን እያፈሰሰች ትኩር ብላ ከተመለከትችኝ በሗላ ተሰናብታኝ ሄደች!
ሁሉም ይሄዳል...የሚቆም ነገር አይኖርም...በመቆም ሳይሆን በመሄድ በተሞላች አዙሪታም ምድር ላይ መቆም ዋጋ የለዉም!
እኔም
አንቺም
አንተም
እናንተም
ሁላችንም ያለ መድረሻ እንሄዳለን የራቅን ይምስለን እንጂ እዉነታዉ አሁንም የጀመርንበት ቦታ መሆናችን ነዉ ካለን ላንጨምር ከተጨመረዉ ልናጎድል ለሰከንድ ፈገግታ የንፁሃንን ዘላለማዊ ደስታ ለምን እንደምናጠፋ አይገባኝም እንዲገባኝም አልፈልግም።

~~~ተፈፀመ~~~

የባለታሪኳ መልዕክት

የህይወትን መራራ ፅዋ በትዕግስት ለተጎነጨዉ ከስኳር ልቆ ይጣፍጠዋል!

ምስጋና
ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ!

በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች አስተያየት መስጫ የሚለውን በመንካት ያድርሱን፡፡

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ @Abusmovies አድርሱን


Join&share
@Zeget77
ማንበብ ባህላችን ይሁን