Get Mystery Box with random crypto!

​​ የባከነች_ነብስ #እውነተኛ ታሪክ #ክፍል1⃣ የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ ... '' | 😁 ዝገት ከ ከሌጋ 😂

​​ የባከነች_ነብስ
#እውነተኛ ታሪክ
#ክፍል1
የቤዛዊት አለሙ እዉነተኛ ታሪክ

... ''ሀዘን በጊዜ ክንፎች ይበራል'' የሚባለዉ ለካ እዉነት ነዉ! የአባቴ ክህደትና የእናቴ ሞት እድሜ ዘመኔን ከልቤ ታትሞ የሚኖር የስቃይ ጠባሳ ቢሆንም በዘመድ አዝማድ ልመናና ቁጣ በየቀኑ ማልቀሴን ቀነስኩ። ቀን በቀን እየተተካ አዲስ ሳምንት ይወለዳል... ሳምንትም እራሱን አሳድጎ ወር ይሆናል... እኔም የእናቴን አርባ ካወጣሁ በሗላ የነበሩንን ንብረቶች ሙሉ በመሉ ሽጬ እናቴን የነጠቀኝን ከተማ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብቼ አዲስ አበባ አክስቴ ጋር ኑሮዬን ከጀመርኩ ቀናቶች ተቆጠሩ። በዚህ ሁሉ ጊዜ ዉስጥ ታዲያ የአቤል ደብዛ መጥፋት ይገርመኝ ያስጨንቀኝም ነበር። ያ ሁሉ ዛቻና ማስፈራሪያዉ እንደዘበት ቀርቶ የዉሃ ሽታ የሆነዉ ምናልባት ሌላ ተንኮል እያሰበ ሊሆን እንደሚችል እንጂ እንዲሁ ዝም ብሎ እንደማይተወኝ ዉስጤ ካመነ ሰነባብቷል። ስለ አባቴ ይህን ሰማሁ... እዚህ ቦታ አየሁት... የሚል አንድም ሰዉ አልተገኘም ብቻ አባቴን ሳስብ የእናቴ ገዳይነቱ እንጂ ወላጅነቱ አልታይሽ እያለኝ በሌላ በኩል እንደ አቤል አይነት የሰዉን እምነት ከአፈር የሚቀላቅል ወንድ በምድር ላይ እስካለ ድረስ እኔ ያለቀስኩትን እንባ፤የተሰቃየሁትን ስቃይ ዳግም ሌላ ሴቶች መቅመሳቸዉ የማይቀር መሆኑን ሳስብ የበቀል እሳት በዉስጤ ይርመሰመሳል። ለእየሩስ አቤል ያደረገኝን ነገር በሙሉ አንድም ሳላስቀር በዝርዝር ባስረዳትም
<<ለምን አንከሰዉም?>> ከሚል ሀሳብና እጅግ በጣም ከማዘን የተሻለ አማራጭ ልትሰጠኝ አልቻለችም። ምን ብዬ እከሰዋለሁ? በምን ማስረጃ? መንፈሴ ላይ ላደረሰዉስ የጥፋት አለንጋ ማን ምስክር ይሆነኛል? ይልቅ መዉጫ መግቢያዉን የሚኖረበትን ሰፈር በአጠቃላይ ስለ እሱ የሚያጣራ ሰዉ እንደትፈልግልኝ እየለመንኩ ጠየኳት አላሳፈረችኝም! ሰፈራቸዉ የሚገኝ ኤልያስ ከተባለ ልጅ ጋር አስተዋወቀችኝ የጠየኩትን ነገር እንደሚያከናዉንልኝ እኔም ለሚያደርግልኝ ነገር ጥሩ ክፍያ ልፈፅምለት ተስማማን። አቤል ከሚኖርበት ፒያሳ አካባቢ በጠዋት ተነስቶ ቦሌ ወደሚገኘዉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ ሱቅ እንደሚሄድ ማታ 2:30 አካባቢ ሱቁን ዘግቶ ወደ ሚኖርበት ፒያሳ እንደሚመለስ አብዛኛዉን ጊዜ ድርጊቶቹ ተመሳሳይ እንደሆኑና በብዛት ሴቶች ወደ ሱቁ እንደሚመላለሱ በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ አጣርቶ ነገረኝ። እየሩስን አቤል ወደሚሰራበት ሱቅ መሄድ እንደምፈልግ ስነግራት በሀሳቤ እንደማትስማማ ገለፀችልኝ የቱንም ያህል ብትቃወመኝም ልታሳምነኝ ስላልቻለች ያላት አማራጭ ሀሳቤን መደገፍ ብቻ ሆነ። ሙሉ ጥቁር በጥቁር የሀዘን ልብሴን እንደለበስኩ ከሳሪስ ወደ ቦሌ የሚሄድ ታክሲ ዉስጥ ከእየሩስ ጋር ገባን።
በዳይ ይረሳል
ቀን ቀን ወልዶ
ቀን ሲጨምር ቀን ሲተካ
አይረሳም ተበዳይ ለካ
የበደልሽኝ እንዳልረሳ ሆኛለሁ
ከልቤ እንዴት እስቃለሁ?
በሚያሳዝን ቅላፄ ከታክሲ ዉስጥ የሚንቆረቆረዉ የመልካሙ ተበጀ ዜማ ውስጤን ያላዉሰዉ ጀመር...
ልቤ ቆስሎ
ዉስጥ አንጀቴ እርር ብሎ
ፍም መስሎ ተቀጣጥሎ
በደል ረመጥ ሆኖ አቃጥሎኝ
ስንገበገብ ጥርሴን ባሳይሽም
ልቤ አይስቅልሽም!

<<ቦሌ ወራጆች መጨረሻዉ!>> የማይስቅ ልቤን ይዤ ከታክሲዉ ወረድኩ
የበቀሌ የመጀመሪያ ቀን...ወደ አቤል ሱቅ በድፍረትና በልበ ሙሉነት ነበር የምራመደዉ...

........... ይቀጥላል..........

ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ
@Abusmovies አድርሱን


Join&share
@Zeget77
ማንበብ ባህላችን ይሁን