Get Mystery Box with random crypto!

ዳንኤል ገብረማርያም

የቴሌግራም ቻናል አርማ zedaniel24 — ዳንኤል ገብረማርያም
የቴሌግራም ቻናል አርማ zedaniel24 — ዳንኤል ገብረማርያም
የሰርጥ አድራሻ: @zedaniel24
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 322
የሰርጥ መግለጫ

በየዕለቱ ከማገኛቸው ሰዎች፣ ከማነባቸው መጻሕፍት፣ ከማያቸው አጋጣሚዎችና ከሕሊናዬ ገጾች ከማገኛቸው ሐሳቦች መካከል መልካሙንና የወደድሁትን መርጬ ለእናንተ የማጋራበት ገጽ ነው።
💚 💛 ❤️
(ሐሳብ ለመስጠት @yedanibot ን ይጠቀሙ።)

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-14 23:37:49
መቼም የትም ሰው እንሁን!
ከፍጥረት ኹሉ የመክበራችንና የታላቅነታችን ታላቁ ምስጢር ሰውነታችን ነው። ሰውነት ክብሩ ከመላእክትም በላይ ከፍ ይላል። ሰውነት ጸጋው አምላክ እስከመኾን የላቀ ነው። የፍጥረታት ኹሉ ገዢና አለቃ ሰውነት ነው። ከሚታየው ዓለም ባሻገር የማይታየውን ዓለም የመመልከት ልዩ ኃይል፣ ከተራራ በላይ የገዘፈ ታላቅ ማንነት ነው ሰውነት። ሰውነት በሥጋ ፈቃድ ተሸንፎ እንደእንስሳት በግብዝነት መራመድ ሳይኾን ከነገር ኹሉ በላይ ረቅቆ፣ ከደመናም በላይ ልቆ በልዕልና የመኖር ልዩ ጥበብና ከመለኰት የተቸረ ህልውና ነው። የትኛውም አመክንዮና ማንኛውም ምክንያት ከዚህ ከፍታችን አውርዶ እንደእንስሳት እንድንኖር ያደርገን ዘንድ ልንፈቅድለት አይገባም! ከኹሉም በላይ ሰውነት ይልቃል! ከምንም ነገር ሰውነት ይቀድማል ይበልጣልም! ሰው እንኹን!
ዳንኤል ገብረማርያም
@zedaniel24 @zedaniel24
152 viewsedited  20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 14:44:14
የሰው ክብር ከችግኝ አንሶ
ስብእና በዘር ሲለካ
የገዢዎች የዕለት እንጀራ
በንጹሐን ደም ሲቦካ
ታሪካችንን ከቶ ከረሳን
እንማር ከሥሪላንካ!!!

ዳንኤል ገብረማርያም
192 viewsedited  11:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 23:21:21
ታቻምና በኦነግ ፣ አምና በወያኔ
ዘንድሮ በሸኔ
እየተሳበበ ፣ ይጥሉኛል አርደው
እኔን ካልገደለ
ሚኖር አይመስለውም ፣ የመጣ የሔደው።
።።
የመጣ የሔደው
ህመምህን ሳይሽር ፣ ቁስልህን ሳያክም
ሬሳህ ላይ ቆሞ
ማን እንደገደለህ ፣ ሊያስረዳህ ሲደክም
እንደማይቀር አውቀህ ፣ ይቀራል ያልከው ግፍ
ወይ ለመኖር ታገል ፣ ወይ ሞትህን ደግፍ!!!

በላይ በቀለ ወያ
270 viewsedited  20:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 14:36:12
316 viewsedited  11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 00:13:48
"በምግባርህ ግዘፍ ልክ እንደተራራ
አካባቢው ሁሉ በስምህ ይጠራ!"
ዳንኤል ገብረማርያም
294 views21:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 19:20:50
352 views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 19:20:43 አንዳንድ ሰው...
ዳንኤል ክብረት በጻፈው "ከእቴጌ ዕሌኒ እስከ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ" መጽሐፍ ዙሪያ ከአንድ ሰው ጋር እየተወያየን ነበር። እናም መጽሐፉ ከሌሎች መጻሕፍት ተቀነጫጭቦ ለገንዘብ ማግኛ ብቻ የተሰነደ ሳይሆን በብዙ ድካም ከብዙ ማስረጃዎች (ተጨባጭ የመረጃ ምንጮች) ጋር የታተመ መሆኑን ተስማምተን በአንድ ጉዳይ ላይ የነበረን ሐሳብ ግን የተለያየ ሆነ። ይኸውም "ግራኝ አሕመድ ወራሪ ነው ወይስ አይደለም" የሚለው ሐሳብ ላይ ብዙ ተነጋግረንም መግባባት አልቻልንም። ወዳጄ የዳንኤል ክብረትን (በዚሁ መጽሐፍ ላይ የተቀመጠ) ሐሳብ መነሻ አድርጎ "ግራኝ አሕመድ ወራሪ ሊባል አይገባውም" ብሎ ሲሞግተኝ እኔ ደግሞ ራሱ ዳንኤል ክብረት አስቀድሞ ባሳተማቸው መጻሕፍትና ሌሎች የታሪክ ማጣቀሻዎችን ዋቢ አድርጌ ሰውየው ወራሪ ስለመሆኑ ሞገትሁ። በመጨረሻም ሞጋቹ ወዳጄ ጸሐፊው ዳንኤል ክብረት በቀደምት መጻሕፍቶቹ ማስረጃ ጠቅሶ "ግራኝ አሕመድ ወራሪ ነው" ብሎ ያረጋገጠውን መረጃ አሁን ለምን ለመለወጥ ፈለገ? የሚለው ላይ ማብራሪያ ሲሰጠኝ እንዲህ አለኝ፦ "ዳንኤል ዛሬ ይህንን ያለው (የግራኝን ወራሪነት የካደው ወይም ወራሪ አይደለም ማለቱ) ያለምክንያት አይደለም። ይልቁንም ግራኝ አሕመድን ወራሪ ልንለው አይገባም ማለቱ ለቤተክርስቲያንና ለክርስቲያኖች በማሰብ ነው" አለኝ። አስከተልሁና "እንዴት?" ስል ጠየቅሁት። ወዳጄም ቀጠለና "አየህ! በዚህ ወቅት ግራኝን ወራሪ ከማለት ይልቅ ወራሪ አይደለም ማለቱ ለቤተክርስቲያን የተሻለ ይጠቅማታል። ይኸውም አሸባሪ ሙስሊሞች ግራኝን ስለሚወዱትና እንደአርኣያ ስለሚመለከቱት ወራሪ አይደለም ስንላቸው ለቤተክርስቲያን ያላቸው ጥላቻ ይቀንሳል፣ በዚህም በየቦታው ቤተክርስቲያን ማቃጠላቸውን፣ ክርስቲያኖችን መግደላቸውንና ማፈናቀላቸውን ያቆማሉ" ሲል ሊያስረዳኝ ሞከረ። እኔም ወዳጄ ባቀረበው አመክንዮ አዝኜ ሐሳቡንም እንደማይቀይር ተረድቼ ሙግቴን አቆምሁ። አንዳንድ ሰው የተራቀቀ እየመሰለው ከእውነቱ እጅጉን ይሸሻል። እንደው ሌላው ቢቀር በውኑ የቤተክርስቲያን ጠላቶች "ግራኝ ወራሪ አይደለም" በሚል ቃል ከጥፋት የሚመለሱ ናቸውን? አይደሉም። እንግዲህ እንዲህ የሞገተኝ ሰው ዛሬ በቤተክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ የሚገኝ፣ ነገ ደግሞ አስተዳደራዊ መዋቅሯ ውስጥ ሊገባ የሚችል (እየገባ ያለ) ሰው ነው።

በእርግጥ የወዳጄ ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከመራቀቅ ሳይሆን ክግላዊ ጥቅም ጋር የተገናኜ ነበር። (እንደአስፈላጊነቱ ለወደፊት በዝርዝር እመለስበታለሁ።) ሰው ለግል ጥቅሙ ሲል እውነትን ደፍጥጦ ከሐሰት ጋር ሲያብር ግን እጅግ ያሳዝናል። በተለይም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ በማይሆን አመክንዮ ቤተክርስቲያንን ሲጎዱ ማየት የሚያሳምም ነው። እንደዚህ ዓይነት የጥቅም ሰዎች ለቤተክርስቲያን ከሚያስገኙት ይልቅ ከቤተክርስቲያን የሚያገኙት ይበልጣል። እነዚህ ከደጇ እስካልሸሹ ድረስ የቤተክርስቲያን ስደት ውጫዊ ብቻ ሳይሆን ውስጣዊ መሠረቱ እንደጸና ይቀጥላል። ስለሆነም ወደ ውስጥም እንመልከት!
326 views16:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 09:50:37
330 views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 09:50:34 የኢትዮጵያ ስቅለት
(ዳንኤል ገብረማርያም)
¤¤¤¤¤¤¤¤
በኢትዮጵያ አገራችን
ለረጂም ዓመታት ቀኑ ረቡዕ ነበረ
እውነትን ለመክሰስ እውነትን ለመስቀል
ብዙ ተነገረ ብዙ ተመከረ!

ጊዜ ጊዜን ወልዶ
ኀሙስ ሲተካ የምክር ቀን ሄዶ

በዕለተ ኀሙስም
በመልካሙ ምድር በአትክልቱ ሥፍራ
እውነትን ለመያዝ
የተላከው መንጋ የሐሰት ጭፍራ
በይሁዳ መሪነት
ችቦ እያበራ በድፍረት ቀረበ
ጊዜው ደርሷልና እውነት ተከበበ ፍትሕ ተከበበ!

በኀሙሱ ምሽት
የሚበራውን ችቦ ከርቀት ያየ ሰው
መሪውን ይሁዳ
የብርሃን መገኛ ብሎ አሞገሰው
የሮምንም ጭፍራ
የነጻነት ታጋይ ሲል አቆለጳጰሰው!

ሕዝብ ግን የዋህ ነው
የሮምን ሠራዊት ፊት ሆኖ ሲመራ
ለቅጽበት አየና
ፈርዖኑ ይሁዳን ሙሴ ብሎ ጠራ!

ይሁዳ ከሃዲ ነው
ጌታውን ለመሸጥ ለአይሁድ ቃል የሰጠ
በማስመሰል ስሞ
በሚጠፋ ዲናር አምላኩን የሸጠ
የነበረውን ክብር በብር የለወጠ!

የኢትዮጵያ ይሁዳም ለጠላት የዋለ
በማስመሰል ከንፈር ሕዝብ እያታለለ
በሐሰት ስሞ
አገሬን ሽጧታል ለአረመኔ ጭፍራ
እያደረሱባት ግፍና መከራ
እየወሰዷት ነው ወደ ቀራኒዮ ወደ ራስ ቅል ሥፍራ!

እንደቀያፋ ደጅ በኢትዮጵያ ምድር
ፍትሕ እንዲገደል እውነት እንዲቀበር
ውሳኔ ተሰጥቷል
ኀሙስ የቀን ቅዱስ የሚባለው ቀርቷል።

የሞት ጽዋ ትለፍ የተባለው ጸሎት
ከአገሬ አፍ ወጥቶ ቢደርስም ጸባዖት
የዓርቡን መከራ ስቃይ አላስቀረም
የከሳሾቿን ምክር እንዳይኾን አልሻረም።

ኀሙስ እንዲህ ቢያልፍም
በኢትዮጵያ ሰማይ ይኸው ለአራት ዓመት ዓርብ ሆኖ ቀርቷል
ክርስቶስ ተሰቅሎ በመስቀል ላይ ሞቷል
በመከራው ጽናት ደም ግባቱ ጠፍቷል።

ክርስቶስ እውነት ነው እውነት ነው ክርስቶስ
ክርስቶስ ፍትሕ ነው ፍትሕ ነው ክርስቶስ
ክርስቶስ ሕዝብ ነው ሕዝብ ነው ክርስቶስ
ታዲያ ምን ያደርጋል
በሮሞቹ ግዛት
በጸሐፍት ረበናት
በአይሁድ ጽኑ መሻት
በፈቃድ ተይዞ በመስቀል ይሞታል
ልብሱ ይቀደዳል በጥፊ ይመታል
ይላገጥበታል ይዘበትበታል።

እጹብ ነው ድንቅ ነው
የአገሬ ክርስቶስ ትናንት ይሰቀላል ዛሬም ይሰቀላል
በግፈኞች ሴራ በከሳሾቹ ፍርድ መስቀል ላይ ይውላል
አንተ ከኾንህ እውነት
እስኪ ራስህን አድን ኃይልህን ግለጥ ይባላል!

አገሬ ኢትዮጵያ ኾና ቀራንዮ ኾና ጎልጎታ
ሰርክ ይታይባታል
በግፈኞች ፍርድ ክርስቶስ ሲሰቃይ ፍትሕ ሲንገላታ።

በዚህ የራስ ቅል ሥፍራ
የሚኾነው ነገር እጅጉን ይደንቃል
አስመሳዩ ኹሉ እንደኢየሩሳሌም ሴት ደረቱን ይደቃል
ወዳጅ የተባለው ሦስት ጊዜ ክዶ ከመስቀል ይርቃል።

በዚህ ቀራንዮ በአገሬ ተራራ
በዚህ ጎልጎታ በራስ ቅል ሥፍራ
የሚሰማውን ድምጽ
የሚያየውን ሁሉ ከቶ ማንስ ያምናል?
ውኃው አፉ ደርቆ
ውኃ አጠጡኝ እስኪ ተጠማሁኝ ይላል
እንጀራው ርቦት
ወዮ የምግብ ያለህ ብሎ ይማለላል!

በሀገሬ ምድር
ዛሬም ቀኑ ዓርብ ነው ስቅላቱ አልቆመም
ያለአንዳች በደሉ
በግፍ በመከራ ሕዝብ ነው ሚገረፍ ሕዝብ ነው የሚታመም።

በዚህ የስቅለት ሥፍራ
ወዳጅ የተባለው በፍርሃት ቢርቅም
የሮሞች ጭካኔ እጅግ ቢያስጨንቅም
ከመስቀሉ ግርጌ በጽናት ቆማ
ስለተሰቀለው ደም የምታነባ
የክርስቶስ እናት ያቺው የተባለች
የሰቃልያኑ መሳቂያ የኾነች
የተሰቀለውን ወልዳ ያሳደገች
በተፈጸመው ግፍ ልቧ የቀለጠ አንዲት ምስኪን አለች!
መከራውም ይብቃ ግፉም ከቶ ይብቃ ብላ ትጸልያለች!።

በሕይወት ታሪኩ
በማንነት ልኩ
ክርስቶስ የኾነ የአገሬን ደግ ሰው
ሰቅሎ ለመግደል ነው
ይኸ ኹሉ መንጋ እንዲህ የሚጮኸው እንዲህ የሚታመሰው።

ምስኪኑ የአገሬ ሕዝብ ክርስቶስ አምሳሉ
ተፈጽሞበትም የዓለም ግፍ በሙሉ
ደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በራስ ቅል ሥፍራ
መስቀል ላይም ኾኖ ጸንቶበት መከራ
የሚያዝንለት የለም ለእርሱ የሚራራ
እወደድ ባዩ ሰው አድር ባዩ መጥቶ
የተሰቀለውን የሕዝቤን ጎን ወግቶ
ደም ውኃ ያፈስሳል
ሕዝቤ ግን የዋህ ነው
በርኅራኄው ብዛት ወጊው ለንጊዮስን ዐይኑን ይፈውሳል።

ግን እንዲህ አይቀርም
ዛሬ ዐርብ ኾኖ ፀሐይ ቢጨልምም
ከዋክብት ቢረግፉ ጨረቃ ብትቀልምም
ተስፋ አለኝ አሁንም
ሕልም አለኝ አሁንም
የዐርብ ፀሐይ መሽቶ ቅዳሜ ይመጣል
በግዞት ያለው ሕዝብ አርነት ይወጣል!!!

ቅዳሜም ያልፍና እሑድ ንጋቱ ላይ
መቃብር ተከፍቶ
ለኢትዮጵያ ይወጣል የትንሣኤ ብርሃን የትንሣኤ ፀሐይ
እግዚአብሔር ያድርሰን ይን ተአምር እንድናይ!!!!
አሜን።
316 views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 17:42:43
228 views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ