Get Mystery Box with random crypto!

በተያያዘ ዜና በሻሸመኔ አፈና እንደቀጠለ ነው! ሕገ ወጡን ሹመት አልቀበልም በማለቷ ምክንያት በኦ | ሊቀ መዘምራን

በተያያዘ ዜና
በሻሸመኔ አፈና እንደቀጠለ ነው!

ሕገ ወጡን ሹመት አልቀበልም በማለቷ ምክንያት በኦሮሚያ የጸጥታ ኃይሎች በተደረገው ግድያ ውድ ልጆቿን የገበረችው የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት መናገሻዋ ሻሸመኔ ዛሬም ብዙ ልጆች እየታሠሩባት ይገኛሉ።

እሥሩም ከወጣቶች ወደ ከተማዋ ባለኃብቶችና ሽማግሌዎች ተሸጋግሯል።

በዛሬው ዕለት በከተማዋ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ባለ ኃብቶች፣ የከተማዋ የተከበሩ ሽማግሌዎችና እጅግ ብዙ ወጣቶች ታሥረዋል።

እንደመረጃ አድራሾቻችን ገለጻ ከሆነ በምእመናን ላይ የደረሰውን ሞትና አካል ጉዳት ለመሸፋፈንና ተጠያቂ እንዳይኖር ለማድረግ የመንግሥት አካላት የሚመለከታቸውን ሰዎች ሁሉ ምንም እንዳይናገሩ ለማስገደድ እየሞከሩ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌