Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ! ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ወሊሶ ከተማ ያደረገውን ጉዞ ተከትሎ | ሊቀ መዘምራን

መረጃ!

ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ወሊሶ ከተማ ያደረገውን ጉዞ ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች ግድያ፣ እሥርና ድብደባ መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል።

በዚሁ ምክንያት የታሠሩት የዓለም ገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን  አገልጋዮች እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡና 'ምርመራ' ተብሎ የተከፈተውን መዝገብ የያዘው መርማሪ እንኳን እንዳልታወቀ ለተ.ሚ.ማ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪም በሰበታ መካነ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሕገ ወጡን ቡድን የሚደግፈው የጸጥታ ኃይል በመኪና አፍኖ ወስዶ አዳራሽ ውስጥ ያጎራቸው 300 የሚደርሱ ኦርቶዶክሳውያን እስካሁን ድረስ እንዳልተለቀቁና ለመጠየቅ ወደ እነርሱ የሚሔዱ ወንዶችን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እየታሠሩ እንደሆነ ተገልጿል።
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች
                •➢ ሼር // SHARE

  •✥• @abenet_tmhert •✥•
  •✥• @z_tewodros •✥•
✥ @abenet_tmhert •✥•            
  ✧━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌