Get Mystery Box with random crypto!

ዘ-ተዋህዶ TUBE

የቴሌግራም ቻናል አርማ z_tewahido_tube — ዘ-ተዋህዶ TUBE
የቴሌግራም ቻናል አርማ z_tewahido_tube — ዘ-ተዋህዶ TUBE
የሰርጥ አድራሻ: @z_tewahido_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.81K
የሰርጥ መግለጫ

https://www.youtube.com/@z-tewahido_tube1

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-13 09:34:19
በሰሙነ ሕማማት የሚሆኑ ጥቅሶችን ለማግኘት ከታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉን

ሼር ማድረግ እንዳይረሳ


subscribe
https://t.me/+HwOebIO8pAc0NTI8
https://t.me/+HwOebIO8pAc0NTI8
subscribe
4 views06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 08:39:32
እንግዳቃላት

ግብረሕማማትውስጥየሚገኙ
እናትርጉማቸው።

ኪራላይሶን፦ ትርጉም Read more..

ናይናን፦ ትርጉም Read more..

እብኖዲ፦ ትርጉም Read more..

ታኦስ፦ ትርጉም Read more..

ማስያስ፦ ትርጉም Read more..

ትስቡጣ፦ ትርጉም Read more..


አምነስቲቲ_ሙኪርያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ


ይቀላቀሉን
            
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░ ► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵  ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵
  
37 views05:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 23:07:12
በሰሙነ ሕማማት የሚሆኑ ጥቅሶችን ለማግኘት ከታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉን

ሼር ማድረግ እንዳይረሳ


subscribe
https://t.me/+HwOebIO8pAc0NTI8
https://t.me/+HwOebIO8pAc0NTI8
subscribe
29 views20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:43:12 ዘ-ተዋህዶ TUBE pinned «ሐሙስ የምሥጢር እና የነጻነት ቀን ይህ ዕለት ብዙ ምሥጢር እና ታሪክ የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ በብዙ ስሞች ይጠራል ጥቂቶቹን ከምክንያታቸው ጋር እንዲህ አቅርበናቸዋል ጸሎተ ሐሙስ:- የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን ነውና ‹ጸሎተ ሐሙስ› ይባላል (ማቴ. ፳፮፥፴፮-፶፮)፡፡ ሕጽበተ…»
18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:42:31
•➢ ሼር // SHARE

ዘ-ተዋሕዶ TUBE
https://www.youtube.com/@z-tewahido_tube1
    𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
https://t.me/+VK34SmV504JkMjdk
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
121 views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 21:41:03 ሐሙስ የምሥጢር እና የነጻነት ቀን

ይህ ዕለት ብዙ ምሥጢር እና ታሪክ የተፈጸመበት ዕለት ስለሆነ በብዙ ስሞች ይጠራል ጥቂቶቹን ከምክንያታቸው ጋር እንዲህ አቅርበናቸዋል

ጸሎተ ሐሙስ:- የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ መኾኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ቀን ነውና ‹ጸሎተ ሐሙስ› ይባላል (ማቴ. ፳፮፥፴፮-፶፮)፡፡

ሕጽበተ ሐሙስ:- ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለምን ዅሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ የንጽሕና፣ የቅድስና አምላክ መኾኑን ያጠይቃል፡፡ ስለዚህም ዕለቱ ‹ሕጽበተ ሐሙስ› ይባላል፡፡ ይህን

የምሥጢር ቀን:- ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ምሥጢረ ቍርባን በዚህ ቀን ተመሥርቷልና ዕለቱ ‹የምሥጢር ቀን› ይባላል፡፡ ይኸውም ጌታችን ኅብስቱንና ጽዋውን አንሥቶ ‹‹ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቈረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ፤ ብሉ፡፡ ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል ላይ የሚፈስ ደሜ ነው፤ ከእርሱም ጠጡ፤›› በማለት እርሱ ከእኛ፤ እኛም ከእርሱ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምሥጢር ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመኾኑ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ:- መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመኾኑ ይህ ዕለት ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ይባላል (ሉቃ. ፳፪፥፳)፡፡ ‹ኪዳን› ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ዅሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለ ኾነ ይህ ዕለት ‹የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ› ተባለ፡፡

የነጻነት ሐሙስ:- ይህ ዕለት ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ኾኖ መኖር ማብቃቱ የተገለጠበት፤ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለ ኾነ ‹የነጻነት ሐሙስ› ይባላል፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፡፡ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤›› በማለት ከባርነት የወጣንበትን፤ ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመኾኑ ሊቃውንቱ ‹የነጻነት ሐሙስ› አሉት (ዮሐ. ፲፭፥፲፭)፡፡
ስለዚህ ይህን ዕለት ከኃጢአት እና ከዲያቢሎስ ባርነት በእግዚአብሔር ቸርነት ነጻ መውጣታችንን የምናስብበት ስለሆነ የተከፈለልንን ዋጋ አስበን ዛሬ ከታሠርንበት የኃጢአት ሠንሰለት በንስሐ ነጻ ሆነን ልናስበው ይገባል፡፡

•➢ ሼር // SHARE

ዘ-ተዋሕዶ TUBE
https://www.youtube.com/@z-tewahido_tube1
    𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
https://t.me/+VK34SmV504JkMjdk
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
119 views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:42:06 ዘ-ተዋህዶ TUBE pinned « አምስቱ ችንካሮች እነማናቸው? ፩. ሳዶር ➤ ቀኝ እጁን ቸነከሩት ፪. አላዶር ➤ ግራ እጁን ቸነከሩት ፫. አዴራ ➤ ማሀል ልቡን ቸነከሩት ፬. ዳናት ➤ ሁለት እግሩን ቸነከሩት ፭. ሮዳስ ➤ ደረቱን ቸነከሩት •➢ ሼር // SHARE ዘ-ተዋሕዶ TUBE https://www.youtube.com/@z-tewahido_tube1     𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒 ➮ከወደዱት ያጋሩ…»
12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 15:14:48
በሰሙነ ሕማማት የሚሆኑ ጥቅሶችን ለማግኘት ከታች ባለው ሊንክ ተቀላቀሉን

ሼር ማድረግ እንዳይረሳ


subscribe
https://t.me/+HwOebIO8pAc0NTI8
https://t.me/+HwOebIO8pAc0NTI8
subscribe
278 views12:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:19:57 አምስቱ ችንካሮች እነማናቸው?

፩. ሳዶር ➤ ቀኝ እጁን ቸነከሩት
፪. አላዶር ➤ ግራ እጁን ቸነከሩት
፫. አዴራ ➤ ማሀል ልቡን ቸነከሩት
፬. ዳናት ➤ ሁለት እግሩን ቸነከሩት
፭. ሮዳስ ➤ ደረቱን ቸነከሩት

•➢ ሼር // SHARE

ዘ-ተዋሕዶ TUBE
https://www.youtube.com/@z-tewahido_tube1
    𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
https://t.me/+VK34SmV504JkMjdk
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
156 views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 14:10:34 ​​#በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸሙ_ሥርዓቶች

1, #ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, #ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, #ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, #አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. #አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, #ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, #ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, #ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

  #ሼር_ሼር_ሼር

ዘ-ተዋሕዶ TUBE
https://www.youtube.com/@z-tewahido_tube
    𝙎𝙐𝘽𝙎𝘾𝙍𝙄𝘽𝙀 𝙉𝙊𝙒

➮ከወደዱት ያጋሩ
share & join
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆  
https://t.me/+VK34SmV504JkMjdk
   𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
154 views11:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ