Get Mystery Box with random crypto!

ያ ፍሬ!! የዛፍ ቅጠል ችፍግ ብሎ ለምለም ሸማ ገፅን ፈትሎ ተከናንቦ..... ፍሬ አዝሎ መላካሉ | ቢንያም ፀጋዬ

ያ ፍሬ!!

የዛፍ ቅጠል ችፍግ ብሎ
ለምለም ሸማ ገፅን ፈትሎ
ተከናንቦ..... ፍሬ አዝሎ
መላካሉ እንደቅል ተንጠልጥሎ
ወፎች ስያዜሙ፥ ግንዱላይ በዝማሬ
በወፍ በረር የቃኝ ዛፋን ፍሬ
ቅርንጫፉን ዙረው ዙረው ፥ሲሆን ጥሬ
ከመቅፅበት ዓይኑ ገባች ፥አንዷ ፍሬ

ዛፍ ቅጠል ላይዋ ርቆ
ፀሐይ ብርዱ ተፈራርቆ
ውርጭ ርጥበት ውስጧ ዘልቆ
ጠወላልጋ መልኳን ፍቆ
ሊመገባት ወፉ ታይታው
ባፉ ሲላት ብስል መስላው
ሊቶኮቱክ ሲነካካው
መበስበሷ መሬት ጣላት፥
ከሷ አሸሸው።

ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP