Get Mystery Box with random crypto!

ስተውሸ አንቺማ : ግዜ እንደ ሸክላ ፥ሰብሮ ንደጣለው ንጉሰ የንግስና ፥ ዘውድ ንደሌለው ገዢ ስ | ቢንያም ፀጋዬ

ስተውሸ

አንቺማ
:
ግዜ እንደ ሸክላ ፥ሰብሮ ንደጣለው
ንጉሰ የንግስና ፥ ዘውድ ንደሌለው
ገዢ ስልጣኑን፥ በትሩን እንዳጣው
የቀን ጎዶሎ ፥ የቀን ክፉ መቶ
መንግስት ባደባባይ ፥መለወጡን ወቶ
እንዳወጀው ብር፥እንዳሮጌው መቶ

ወድቄ ከግርሽ
ማሪኝ ብዬ ስለምንሽ
ግዜው አልፎብሃል፥
ብለሽኝ ተራመድሽ

#ግና.......

ከቶ አይጨበጥ ፥ተስፋዬ ጉም ሆኖ
ንፋስ እንደነካው፥ ደመና ተበትኖ
ራሴን ለውጬ፥ ስኖር ንደራሴ
ወቅቴን ጠብቄ ፥አብቤ ንደከሴ
ሃዘን ሳይዳብሰኝ ፥ሳይከደን ጥርሴ
ከዛ ከትርምስ ከሰው ግርግር
ሾልኮ ንደወደቀ ፥እንዳዲሱ መቶ ብር
ጎንበስ ብለሽ አንስተሽኝ
እኔ ግን የሰው ነኝ
አንቺ አገኘሁ አልሽኝ።


ቢንያም ፀጋዬ
@YOPPPP