Get Mystery Box with random crypto!

Yoni Arts

የቴሌግራም ቻናል አርማ yoniarts5 — Yoni Arts Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yoniarts5 — Yoni Arts
የሰርጥ አድራሻ: @yoniarts5
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 761
የሰርጥ መግለጫ

👉 ያነበብኳቸውን የብእር ትሩፋቶች፣ የሰማኋቸውን መረጃዎችና ያየኋቸውን እውነቶች የማቀርብበት ቻናል ነው። ቤተሰብ ይሁኑ!
You Tube Channel Subscribe Now
https://youtube.com/channel/UCekLT0ck645BHB8D6rJ5g4w

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-21 20:55:29 ከታሪክ ማኅደር

የ"ቶ" ፊደል ቅርፀ መስቀል ምሥጢር

የዚህን ፊደል ትርጉም የትየለሌ ጦማሪያን የከርሰ ምድር ታሪክ መዝባሪዎች ምሁራን ቢመራመሩት እስከ አሁን ድረስ ግራ ቢገባቸው "The lost image of cross" እስከ አሁን የጠፋው ታላቅ ኃይል ያለው የመስቀል ምልክት በሚል ጽሑፍ አበርክተዋል። እጅግ ምስጢራዊነቱ የሚነገርለትና የተጻፈለት ይህ በ "ቶ" ፊደል ስለተቀረፀው መስቀል በጥቂቱ እንመልከት

“ቶ” ሰባተኛዋ ፊደል ነች፡፡ ሰባት ቁጥር ትልቅ ትርጉም ያላት ነች ፍጹምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ሰባተኛው ዙፋን የጌታ እንደሆነ፣ ሰባተኛው ቀን ሰንበት እንደሆነች፣ 7 ቁጥር ብዙ ምስጢር አላት፡፡ “ቶ” ሰባተኛዋ ቁጥር በመሆኗ ፍጹምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ክርስቶስን የምትወክል ነች፡፡ ክርስቶስ ለኛ ሲል በቀራኒዮ መስቀል ላይ ራቁቱን መሰቀሉን የምታመለክት ነች።

ትልቁ ከዚህ በላይ ያለው ምስጢር አባቶቻችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ አንጻር ሲተነትኑ በሰማይ መላእክት ዘንድ ውጊያ ሆነ ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ከሳጥናኤል ጋር ሲዋጉ ሁለት ጊዜ ተሸንፈዋል፡፡ በሦስተኛው እንዲያሸንፉ ሲልካቸው ይህን ቀስተ ደመና ቀርፆ፣ ይህን ምልክት የኮከቡን ቅርፅ የ“ቶ” ቅርፅ ያለው መስቀል በየክንፋቸው ቀርፆላቸዋል። "ኤል" የሚለውንም ምስጢራዊ ስም አትሞባቸዋል። ይህን ካደረገላቸው በኋላ ተመልሰው ወደ ውጊያው ቢሄዱ ሳጥናኤል ኃይላቸውን ሊቋቋመው አልቻለም ውድቀቱ ፈጠነ ሽንፈቱ የከፋ ሆነበት ጽልመትን አልብሰው ወደ በርባኖስ ውስጥ ጥልቅ ጨለማ ላይ ወረወሩት። የአምላክ ክንድ ጽኑ መሆኗን ሳጥናኤል ያውቃልና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሥላሴን ሥሉስ ቅዱስ እያለ እየተንቀጠቀጠ ይገዛል ይላል። ሆኖም ምግባር ስለሌለው ጽድቅን አያያትም።

ሰዎች "ቶ"ን የሕይወት ምልክት አድርገዉ የሚወስዱት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ነዉ። የሚገርመዉ ደግሞ ይህ ምልክት አገልግሎት ላይ የዋለዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት 3000 አመታት ቀደም ብሎ ጥንት ግብጻዉያን ቶ-ኔቶር (የፑንት ምድር) ብለዉ በሚጠሯት ሀገር ነዉ። ግብጻዉያን እንደሚሉት የፒራሚድ ግንባታ ጥበብን የተማሩት ከቶ-ኔቶር (የአሁኗ ኢትዮጵያ) ሰዎችና አማልክቶች ነዉ። በ670 ዓ.ዓ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረዉ ንጉስ ቲርሀቅ ኢየሩሳሌም የአሶር ንጉስ በሆነዉ በሰናክሬም ስትወረር ለኢየሩሳሌም መከታ ሆኖ ሲዘምት ኃያላን ከሚባሉ ወታደሮች ጋሻ ላይ የ "ቶ" ምልክት እንደተቀረፀና ንጉሱም በ"ቶ" ቅርፅ የተሰራ መስቀል ማሰሩን የሚያስረዱ የድንጋይ ላይ ጽሑፎች ተገኝተዋል።

የ"ቶ" ምልክት የተፈጠረዉ በቅርብ ጊዜ ነዉ ለሚሉ ሰዎች "ቶ" የተፈጠረዉ አለም ሲፈጠር ነዉ ብንል እዉነት እንጅ ውሸት አይሆንም። ለዚህ ማስረጃችን ደግሞ የሰው ልጅ የተፈጠረዉ "ቶ" ቀመር መሆኑ ነዉ። ይህ ምልክት ግብጽ በሚገኙ የዋሻ ሥዕሎች ላይ የሕይወትን ገፀ ባሕሪ ይዞ እንደነበር የሚያስረዳ ሲሆን ይህ ምልክት አገልግሎት የጀመረው ኢትዮጵያ ላይ ከሆነ ግብጽ ላይ እንዴት ተገኘ? ብሎ ለሚጠይቅ ግብጽ ላይ የነገሱት 18 ኢትዮጵያዊ ንጉሶች ተጠቃሽ ናቸዉ:: ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 ዓ.ዓ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 ዓ.ም የቆመ ሀውልት እንደነበረዉና ሀውልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሐይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ግሪካዊው የታሪክ ጸሐፊ ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል:: ክራር ደግሞ የኢትዮጵያ የባህል መሳሪያ መሆኑ ደግሞ አጀብ ያስብላል።

በሳባውያን የዋሻ ላይ ሥዕሎችና ማህተሞች ላይ "ቶ" ተመስሎ ጣቱን የቀሰረ ምስል እንዳለ (አስቻለዉ ከበደ የተባለ ፀሐፊ ከርከቤዴል ሳዶፍ) በሚል መጽሐፉ አስፍሮታል:: ሳባውያን ሰውን ለመሳል "ቶ"ን መጠቀማቸው ያጋጣሚ ይመስላችኋል? በሮማውያን አፈ ታሪክ ላይ የሕይወት ምልክት ተደርጎ የተወሰደው የተጋደመዉ የ ለ ፊደል ሲሆን በግራና በቀኝ ሁለት ጭረቶች አሉት። ይህ ምልክት ለሮማዉያን ከአማልክቱ የተሰጠ መስሎ ቢታያቸውም እውነቱ ግን በአንድ ባልታወቀች የአፍሮዳይት ኦራክል የተፈጠረ እንጅ የሕይወት ምልክት ላለመሆኑ ከሰው ጋር አብሮ የተፈጠረዉ "ቶ" አስረጅነቱ የትየለሌ ነዉ።

ለምሳሌ እንኳ ብንወስድ ጠቢቡ ሰሎሞን ታላቁን ቤተ-መቅደስ ከመስራቱ አስቀድሞ በሚሰራበት ቦታ ላይ አሰድ እሳት የተሰኘችው ኮከብ እና ፀሐይ በ45 ዲግሪ ትይዩ ወጥተው ነበር፡፡ በዚህም የተነሳ እስራኤል የአንበሳ ከተማ ተብላ ትንቢት ተነግሮላታል። አንበሳ አሰድ እሳት የተሰኘው ኮከብ መለያ ምልክት እንደሆነ ልብ ይበሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ጌታችን
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ወቅት ይህ አሰድ እሳት የተሰኘው ኮከብ ከፀሐይ ጋር ትዩዩ ሆኖ በመውጣት የጌታችን ንጉስነትን አብስሯል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለበት ወቅትም ፀሐይን ጨምሮ የተለያዩ ኮከቦች የመስቀል ቅርጽ ሰርተው በኢየሩሳሌም አናት ላይ ታይተዋል፡፡

ቶ ጠልሰም (ምሳሌ፣ አርማና ምልክት) የኢትዮጵያን ምስጢራዊ ታሪክ በማጥናት አለም አቀፍ እውቅና የተሰጣቸው አባ ተስፋሥላሴ ሞገስ ይህን ጽፈዋል: "....ክርስቶስን የሚወክለው "ቶ" ፊደል የተደረገበት (በመጽሐፋቸው ላይ በኢትዮጵያ ካርታ መሀል ላይ የ "ቶ"አርማ ይገኛል) ከዓለም ሕዝብ በፊት ጀምሮ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ኦሪትን ከሐዲስ ጋር አዋሕዳና አስማምታ የምታምንና የምታሳምን ኢትዮጵያ ብቻ መሆኗን የሚያመለክት ነው, ...."

" ቶ " እስከ ዛሬ ከተመለከትነው ትርጉሙ ባሻገርም ሌላ ትርጉም አለው። ቶ አቶ ወይንም እኔ ማለት ነው። አ፣ ኦ ያሉት ቃላት ከጉሮሮ ተነስተው በአንደበት የሚሰራጩ አናባቢዎች ናቸው። በዚህ መሰረት አ አናባቢ ሲሆን ተነባቢው ቶ ነው። ከዚህ በመነሳት ቶ ከስም ቀድሞ የሚገባ ባለቤትን አመልካች ነው። ይህ ትርጉም ከሱባ ቋንቋ ጋር ተዛምዶ እንዳለው መራሪስ አማን በላይ በመጽሐፋቸው ጽፈዋል።

ምንጭ:- Yunael blog (ከዩናኤል ቀዩ ንስር)
ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ ነው የተዋሕዶ አንበሳም መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /በአባ ተስፋ ሥላሴ ሞገስ የተዘጋጀ መጽሐፍ/
መጽሐፈ ብሩክ /በመራሪስ አማን የተጻፈ መጽሐፍ/


ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5
2.1K viewsedited  17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 12:54:27
410 views09:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 12:37:30 ከፍቅር ጉያ

ፍቅር

ለማወቅ የምንፈልገውን ነገር ሁሉ መጀመርያ እናፈቅረው ዘንድ የተገባ ነው። ለማንኛውም የህይወት ዘርፍ የስኬት ቁልፍ ፍቅር ነው። ዳቪንቼ ሥዕልን ከምንም በላይ አፈቀራት ታወቀባትም፤ ሞዛርት ሙዚቃን አፈቀራት ፥ ከፍ ከፍም አረገችው፤ ሼክስፒር ሥነ-ጽሑፍ ፍቅረኛው ሆነች፥ በስሟም አነገሰችው።

የፍቅር ንጉስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅሩ አለምን ማረከ ፥ አለም ተንበረከከችለትም። እውነተኛ ታላቅነት እንግዲ 'ሚመጣው ከማፍቀር ነው። ኢየሱስን መምሰል ሚቻለው በፍቅር ብቻ ነው።

ፍቅር ነፍስን በሚወዱት ሰው ውስጥ መግደል ነው ይለናል ኦሾ። ፍቅር ከስግብግብነት የፀዳ ማንነት ነው። እውነተኛ አፍቃሪ የሚያፈቅረውን ሰው ደስታ ለማየት ለመሰዋት የተዘጋጀ ነው። ሀዲስ አለማየው ስለ ፍቅር እንዲህ ይላሉ፥ አይንን ክፉ ከማየት ምላስን ክፉ ከማውራት ጆሮንም ከመስማት፥ ምናብንም ከፉ ከማለም የማይከለክል ፍቅር፥ ፍቅር አይደለም።

ፍቅር ለአሉታዊ ውጤት ምንም ግምት አይሰጥም። ለፍቅር አለም ሁሌም ብሩህ ናት። ፍቅር ሙሉነትን የመፈለግ መንገድ ነው። ግን ይለናል ኦሾ ቀጥሎ ፦ እንደመሰለው እንደመሰላት እንደመሰለን እንፋቀራለን። በማይረባ መንገድ። እራስ ወዳድነትን በተላበሰ መንገድ እናፈቅራለን። ማፍቀር ግዴታ ይመስል እናፈቅራለን። ጥላቻ አርግዘን እናፈቅራለን። እራስ ወዳድነትን አርግዘን እናፈቅራለን። ፈርተን እናፈቅራለን። ከዛም ሲሰለቸን ስለ እውነተኛ ፍቅር መሞት ማላዘን እንጀምራለን። ባዶነት ይሰማናል። ትላንት ያፈቀርነው ዛሬ ጠላት ይሆንብናል። የማናውቀው ሰው ጠላት ሊሆነን አይችልም። ጠላት እንኳን ጠላት ለመሆን የግድ በጓደኝነት ውስጥ ማለፍ አለበት። ልክ ያልሆነ ፍቅር ወዳጅ ሳይሆን ጠላት ያተርፋል። የማፍቀር ብቸኛው ምክንያት ፍቅር ካልሆነ ሌላው አላፊ ነውና ጭንቀትን ይወልዳል።

አንድ ሰው ስታፈቅር ፥ ሰውዬውን ሙሉ በሙሉ ትቀበላለህ። ከነሙሉ እንከኑ። ምክንያቱም ይህ እንከን የሰውዬው አካል ነውና። የምታፈቅረው ሰው ለመለወጥ አትሞክር። እንዲህ ከሆንክ እወድሃለው አትበል። ምክንያቱም ለመቀየር የምታደርገው ጥረት ''እኔ ማፈቅረው ግማሽ አንተን ነው'' የሚል አስተሳሰብ አለበትና። ሰው ባያፈቅርህም እራስህን መሆን አትተው። አበባ ሰው የለም ብሎ ጫካ ውስጥ ማበቡን አይተውምና። ስታፈቅርም በቃ በቀላሉ አፍቅር!

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5
963 views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 10:34:57 የእሑድ ጉርሻ

ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት

በዶ/ር ምህረት ደበበ

ይሰለቹሃል አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!
'ሼም ነው' የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!
አይባልም "... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።
ክፈል አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።
ነውር ነው ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
አታቋርጥ ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ።ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።
አታብሽቅ ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።
አመስግን ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመስግን።
ያለስስት አድንቅ ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።
ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን
ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።
ስነ-ስርዓት ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።
ክብር ለሁሉም ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።
ስልክህን አስቀምጥ ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።
አድብ ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
ተቆጠብ ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።
መነጽርህን አውልቅ ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!
አትሳሳት በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።
ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።
ዕቃ መልስ የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።
አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ።

ብሩህ ቀን ይሁንልን!

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5
1.3K views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 09:37:39 እለተ ሰንበት

የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ የአለማት ሁሉ ገዢ ልዑለ ባሕርይ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ሁሉ ካለመኖር ወደ መኖር ሲያመጣቸው አሐዱ ብሎ የጀመረበት ቀን እሑድ ነበር። ፍጥረታትን ፈጥሮ የጨረሰበትና ያረፈበት ቀን ደግሞ ቀዳሚት ሰንበት ነው።

ዳሩ ግን በሐዲስ ኪዳን የጠፋውን አዳምን ፍለጋ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህች ምድር ሲመጣ የማዳኑን ሥራ አጠናቆ ሞትን በሞቱ ደምስሶ የሕይወትን ብስራት ያበሰረበት ለትንሣኤያችን በኩር ሆኖ በክብር የተነሣው በእለተ እሑድ ነውና ይህም እለት በሐዲስ ኪዳን ሰንበተ ክርስቲያን ተብሎ ይጠራል። እለቱን እንቀድሰው ዘንድም "የሰንበትን ቀን አክብር" በማለት ትዕዛዝ ከኦሪት ጀምሮ በተሰጠን መሰረት ማክበር የክርስቲያኖቹ ሁሉ ኃላፊነት ነው።

"ሰንበት" እረፍተ ነፍስ የምናገኝባት የገነት አምሳል ነውና እረፍተ ሥጋ እያደረግንበት ሰማያዊቷን ሀገራችንን በማሰብ ቀኑን ልናሳልፈው ይገባል።

መልካም እለተ ሰንበት!

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5
1.6K viewsedited  06:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 22:52:26 ከፈላስፋዎች ጉያ

የቻንድራ /OSHO/ ወጎች

ድንቁርና አለማወቅ አይደለም

አለማወቅ የሚያመለክተው የአንድን ሰው ምንም አለማወቅ አይደለም ፤ አለማወቅ ገሚስ እውነታን ብቻ ማወቅ ነው ፤ አንድ ሰው አለማወቁን እንኳ ቢያውቅ የሆነ ነገር ያውቃል ፤ እናም ማወቅ በሁላችንም ውስጥ አለ ፤ ስለዚህ ድንቁርና አለማወቅ አይደለም ፤ ከሁሉ የባሰው ደንቆሮ እንኳ የሆነ ነገር ያውቃል!!!"

ዝም ብሎ ማፍቀር

አንድ ሰው ስታፈቅር ፥ ሰውዬውን ሙሉ በሙሉ ትቀበላለህ። ከነሙሉ እንከኑ ። ምክንያቱም ይህ እንከን የሰውዬው አካል ነውና። የምታፈቅረው ሰው ለመለወጥ አትሞክር። እንዲህ ከሆንክ እወድሃለው አትበል። ምክንያቱም ለመቀየር የምታደርገው ጥረት ''እኔ ማፈቅረው ግማሽ አንተን ነው'' የሚል አስተሳሰብ አለበትና። ሰው ባያፈቅርህም እራስህን መሆን አትተው። አበባ ሰው የለም ብሎ ጫካ ውስጥ ማበቡን አይተውምና። ስታፈቅርም በቃ በቀላሉ አፍቅር!!!!

መወለድ መሞት ነው

እኔነትን ጥላችሁ የሁለተናው አካል መሆናችሁን ከተረዳችሁ ሞት የሚባል ነገር የለም፤ ሞት ልክ አሮጌ ልብሳችሁን ጥላችሁ አዲስ ልብስ እንደ መልበስ ይመሰላል። በእናታችው ማኅጸን ለዘጠኝ ወር ቆይታችው ትወለዳላችሁ ለዚህ ምድር ውልደት ሲሆን በእናታችው ማኅጸን ለነበረው ሕይወታችሁ ግን መወለድ መሞት ነው።

በዝምታ የማይቆጠር ምስጢር አለ

ዝም ስትል ብዙ ጩኸቶች ትሰማለህ! በምትጮህ ሰዓት ደግሞ ብዙ አፈ ሙዞች ታገኛለህ! አስተውል በአንተ ዝምታ ውስጥ የማይቆጠር ምስጢር አለ! ዝምታህን ከሰዎች ለመሸሽ ብቻ አትጠቀምበት! እንደውም እነሱ ዝም ሲሉ አንተ በመጮህ የምስጢሩ ተካፋይ አድርጋቸው!

እውነት ተሞክሮ ነው

የተነገራችሁን ሁሉ ቀጥታ እንደወረደ አምናችሁ አትቀበሉ ከዚያ ይልቅ እውነትን በብልሃትና በንቃት ለማግኘት ሞክሩ።
እውነት ሁልጊዜ ተሞክሮ ነው። የእኔ እውነት የእናንተ ሊሆን አይችልም ፤ ያለማወላወል የእኔ ብቻ ነው። እውነትን ልንጋራው አንችልም። እኔ የምሰጣችሁ ግንዛቤ ብቻ ነው። ከዚያ በተረፈ እያንዳንዱ ሰው እውነትን ደጋግሞ በራሱ ማግኝት አለበት። ስለሆነም ለመመራመር፣ ለመጠየቅ፣ ለመሞከር ለመተግበር ትጉ።"

ከድጡ ወደ ማጡ

የበታችነት ስሜት በሽታ ነው፤ ይህን የበታችነት ስሜት ለመደበቅ የሚመጣው የበላይነት ስሜት ደግሞ የባሰ በሽታ ነው። አብዛኛውን ጊዜ መድኃኒቱ ከበሽታው ይልቅ አደገኛ ነው። አንድ ሰው ተፈጥሯዊ ሚዛኑን መጠበቅ የሚችለው ከበታችነትም ሆነ ከበላይነት ስሜት ነፃ ሲሆን ነው።

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5
774 viewsedited  19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 22:44:46 Channel name was changed to «Yoni Arts»
19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 08:15:50 https://vm.tiktok.com/ZMN9PnuUN/?k=1
633 views05:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:04:15
ወርቃማ ድል

ቀዝቅዞ የነበረው የኢትዮጵያ አትሌቶች ፌዴሬሽን አቆጥቁጦ እንደተነሳ ትንሳኤውን ወርቃማዎቹ ጀግኖች ልጆቿ ድልን በማስመዝገው ጀብድ በመስራት አሳይተውናል። ከዚህ በፊት በወንዶቹ ማራቶንና በሴቶቹ 10 ሺ ያስገኙትን የወርቅ ሜዳልያ አይቼ ተገርሜ ሳላባራ ደግሞ በሴቶች ማራቶን የወርቅ ሜዳልያው ተደገመ።


ምርጥ ልጆች ቀዝቅዞ የነበረውን መንፈስ ዳግም አንሰራርቶ እንዲነሳ እና ደማችን ደመ ሙቅ እንዲሆን አድርገውናል። ጀግኖቹ ክብረት ይስጥልን።


ኢትዮጵያዬ የለውጥሽ ትንሣኤም ሩቅ እንደማይሆን ተስፋ አለኝ። አኩሪ ልጆችሽ ዛሬም በአለም መድረክ ላይ ክብርሽን አውጀው ሰንደቅሽን አውለብልበዋል።


የሞት ዜና አብቅቶ የለውጥ፣ የእድገት፣ የአንድነትና እንዲህ ያለ የድል ዜና የምንሰማበትን ጊዜ ፈጣሪ ያምጣልን። ኢትዮጵያ ትንሣኤሽን፤ የፊትሽን ፈገግታ፤ የእጅሽን ስፋት፤ የስልጣኔሽን ቁንጮነት ለማየት እንጓጓለን።


እንኳን ደስ አለን ከፊል ደስታ ቢሆንም።

@yoniarts5
@yoniarts5
@yoniarts5
2.1K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ