Get Mystery Box with random crypto!

#Tech_News #ዜና_ቴክ × ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል | Yidnek Tube

#Tech_News
#ዜና_ቴክ

× ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል።

× የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ የሆነው ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት ለመጀመር በሙከራ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

× ይህ ሥርዓትም ቢያንስ ከ1000 በላይ ተከታይ ባላቸው ቻናሎች ላይ እንደሚጀመር ነው የገለጸው።

× ከዚህ ቀደም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት የሌለው ቴሌግራም አሁን ላይ ተጠቃሚዎች ቻናላቸውንና ቡታቸውን በክፍያ እንዲያስተዋውቁ የሚያስችላቸውን አሰራር መዘርጋቱን ነው ይፋ ያደረገው።

× የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ እንደጠቀሰው በሙከራ ላይ የሚገኘው የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓቱ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን የግል መረጃን አይጠቀምም ብሏል።

× ከዚሁ ጋር ተያይዞ ማስታወቂያዎቹ በግል እና በቡድን መልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳዎች ላይ የማይታዩ መሆናቸውንና በክፍያ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች በቻናሎች ላይ ብቻ እንደሚቀርቡ ገልጿል።

× ማስታወቂያ ማስነገር የሚፈልጉ አስተዋዋቂዎች ቻናላቸውን ወይም ቡታቸውን ከ160 ባልበለጡ ፊደላት ገለጻ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በቋንቋ፣ በይዘት እንዲሁም በልዩነት ማስታወቂያው እንዲተላለፍላቸው የሚፈልጉትን ቻናል መርጠው ማስተዋወቅ ይችላሉ ተብሏል።

× ቴሌግራም ከቻናል ባለቤቶች ጋር የትርፍ ክፍፍል የማድረግ እቅድ እንዳለውም ያስታወቀ ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን መሰረታዊ ወጪዎቹን ከሸፈነ በኋላ እንደሆነ ገልጿል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube