Get Mystery Box with random crypto!

#Tech_News #ዜና_ቴክ × ኢትዮጵያ ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚያስከፍሉ ሀገራት በቀዳሚነት | Yidnek Tube

#Tech_News
#ዜና_ቴክ

× ኢትዮጵያ ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚያስከፍሉ ሀገራት በቀዳሚነት ተቀመጠች።

× መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገ 'ፕራይስ ኮምፓሪዝን' የተሰኘ የምርምር ተቋም አደረግኩት ባለው አዲስ ጥናት በዓለማችን ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚጠይቁ 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን በአንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

× ጥናቱ በኢትዮጵያ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በወር በ307.84 ዩሮ ገደማ እንደሆነ በመግለጽ ይህ ዋጋ ኢትዮጵያን በዓለም ላይ ከሚገኙት ሀገራት ከፍተኛ ዋጋ የሚጠየቅባት ሀገር ያደርጋታል ብሏል።

× ይህም ለወርሃዊ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ሽያጭ በአማካኝ 30.99 ዩሮ ከምትጠይቀዉ ዩናይትድ ኪንግደም ጋር በንፅፅር ሲቀመጥ የኢትዮጵያ ዋጋ ወደ አስር እጥፍ እንደሚጠጋ ተጠቁሟል።

× ውድ የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ካለባቸዉ ሀገራት መካከል ለብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በወር 236.09 ዩሮ የምታስከፍለዉ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

× በተቃራኒው በጥናቱ በአለም ላይ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በርካሽ ዋጋ ከሚገኝባቸው ሀገራት ተርታ መካከል ዩክሬን የአንደኝነት ደረጃን የያዘች ሲሆን ለአገልግሎቱ የሚከፈለዉ ወርሃዊ ክፍያ በአማካኝ 4.42 ፓውንድ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።


→ Join : @yidnek_tube
→ Join : @yidnek_tube_group

→ Subscribe : https://www.youtube.com/c/YidnekTube