Get Mystery Box with random crypto!

የታሪክ ማህደር

የቴሌግራም ቻናል አርማ yetarikmahdaer — የታሪክ ማህደር
የቴሌግራም ቻናል አርማ yetarikmahdaer — የታሪክ ማህደር
የሰርጥ አድራሻ: @yetarikmahdaer
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.70K
የሰርጥ መግለጫ

❎በ አይነቱና በ አቀራረብ ልቆ በትንሽ ቀናት ውስጥ ተከታዮቹ አንደ ጎርፍ የተዝጎደጎዱለት ታሪክን ዞር ብሎ በ አዚህ ቀን ይህ ሆነ አያለ የሚነግረን ፣ በ አለማችን ብሎም በ እንቁዋ ምድር ኢትዮጵያ ለ ሀገር ለ ወገን ድንቅ ቅርስ አስተላልፈው የሄዱትን ማለትም በስነ-ጥበብ ፣በሙዚቃ ፣ በጀግንነት ያለፈትን የኛው ጀግኖቻችንን የህይወት ተሞክሮ ከ ስራወችቻው ጋር ፣አረ ምኑ ተነግሮ የዚህ ቻናል

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-22 18:29:30
602 views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 06:24:00 እኔ እንደ ቴዎድሮስ ጥይትን አልጠጣም
ወይ እንደ ዮሐንስ አንገቴን አልሰጥም
በሀገሬ እንባ ሆዴ ቢረበሽም
አዎ ሀገር አለኝ
በሩቅ ምትናፍቀኝ
ምኒልክ ዋ ብሎ አዋጅ ያወጀላት
ጴጥሮስ ሳይፈራ ደረት የሰጠላት
በሩቅ እያዬኋት
እንደ እፅ በለስ መቼም የማልደርሳት
ድብት ሀዘኗ ግን ሁሌም ሚያስለቅሰኝ
አወ ሀገር አለኝ በሩቅ ምትናፍቀኝ
ኢትኤል በራዕዩ ያያት ቢጫ ወርቅ
እንዴት አላለቅስም ዛሬ ለብሳ ማቅ
አዎ ሀገር አለኝ
በሩቅ ምትናፍቀኝ

ኢትዮጵያ ማለት ቢጫ ወርቅ ማለት ነው
ዛሬ ግን ሀገሬ ቀይ ሆናለች ደም ለብሳለች
791 views03:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:44:38 ኢትዮጵያ በእናት ትመሰላለች
ሀገር እናት ናትና እርስት ናትና ::
ሀገር ህዝብ ነው በህዝብ ውስጥ ደግሞ ታሪክ ባህል ቱፊት ወግ ልማድ አለባበስ ህብረብሄራዊ አንድነት ግን የጎደለው ነገር ሰላም ነው ሰው እንኳን ከሌላ ሰው ጋር ይቅርና እራስ በራሱ እየተጣላ እየተፈላቀለ እየተዋጋ ነው ስለዚህ መጀመሪያ ከሌላ ሰው ጋር ከመታረቃችንና ሰላም ከማውረዳችን በፊት ከእራሳችን ጋር እንታረቅ ከዛ ውስጣችን ሰላም ሲሆን የሰውን ሁሉ ሰላም እንመኘዋለን እንደግፈዋለን እናም ከሰዎችም ጋር እንታረቃለን ያ ነው ኢትዮጵያዊነት የሰላም የፍቅር የአንድነት የወዳጅነት የእናትነት እሴት በሀገራችን የነበረው ያንን ለማምጣት እኛ ልጆቿ ልንደግፋት ይገባል :: ይህ የታሪክ ማህደር የተሰኘው ቻናላችን ያለፈው ታሪካችን ውስጥ ያሉትን ጀግኖች የአሁኖቹንም ተምሳሌቶች ይዳስሳል እናም እባካችሁ ታሪካችንን በእውነተኛው መንገድ እንየው ታሪክን ቀይረን በሌላ ትርጉም አንተርጉመው የራሱን ትርጉም እንስጠው ::
ኢትዮጵያ ትቅደም ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !
903 viewsedited  20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:59:02 ከወርቅ ከቡና፤
ከቂቤው ወዘና ፤
ከጊቤ ማህፀን ከእንብርቱ ፈልቀህ፣
እሳት ሲፈትንህ፤
ወርቅ ሆነህ ኖረሀል ለሀቅ ተዋድቀህ።

ከነሆደ አምላኩ፤
ከነንትና ጎሬ፤
ሀድራው ሲደራ እጣን ተጫጪሶ፣
አንተ ግን እውነት ነህ፤
አጋንጠህ አድረሃል ለሊቱን በለቅሶ።
አንተ ሰው ሀቅ ነህ !
ሀሰት ያልበገረህ፤
ውሸት ያልመተረህ እውነት ስትል ወርደህ፣
ቢላል ለቀደሰው፤
ሼሁ ላወደሰው ለሀቂቃው አብደህ፣
እንደ ነበልባሉ እንደ እቶን ነደህ፣
የመኖርን እውነት፤
የእምነትን ፅናት የስልምናን ጥጉ፣
ኖሮ በማሳየት፤
ነበርክ እኮ ካስማው ነበርክ እኮ ዘንጉ።

አንተ የሰው ምሰሶ አንተ ያገር ማገር፣
አንተ የሰው ጥጉ አንተ የሰው ድንበር፣
አንተ የሰው ቅኔ አንተ የሰው ምስጢር፣
ፈርተህ የማትፈራ የጀግኖቹ ጀግና፣
በእሳት ንዳድ ውስጥ እምነትህ የፀና።

በደራው ገበያ፤
በሰፊው ጎዳና ገዢ ተቸንክሮ፣
ዝምታህ ተሽጧል፤
በሰባራ ፊደል በቃል ተቸርችሮ ።
እንኳን ሰው ቀርቶ፤
የአለም መቀመጫ ግዙፊቷ ምድር፣
አንተነትህ ከብዷት፤
መግዘፏ ተናንሶ ደክማ ስትታትር፣
የቃልህን ልቀት ነበረች ምስክር።

ይሄን ባየው ጊዜ ፤
ሰተት ብዬ ገባው ሰተት ብዬ ወጣሁ፣
ብዕሬን ሸክፌ፤
እንኳን የማቀልመው የማነበው አጣሁ።
በሀሰት ገበያ እውነት እንደ ቅርጫ፣
ነግዶ ማትረፊያ ሆኖ መለወጫ።
የኖርክለት ቅኔ የሞትክለት እውነት፣
በተውሶ ልምሻ ስንቱ እያጌጠበት።
እውነትን ማስፈሪያ ቃላት ባመሳጥር፣
አይጥ ሆኖ አገኘሁ የድንቢጥ ምስክር።

ሰተተተተተተተተተተት፤
ቃሉ ምን ሊረባ ሰው ካልታከለበት፣
መዶሻ ቢያቀና የጠመመ ብረት፣
ቅባት ተቀብቶ አይወረዛም እንጨት።
ቆንጆ ነኝ እያለ ሲመጣም ዝንጀሮ፣
አንይ እየተካደ ቢታመንም ጆሮ።
እውነታ በራቀው በማስመሰል አለም፣
የሚሆንህ ቀርቶ የሚመስልህ የለም።

አይ ከድሮ፤
ከኖሩማ አይቀር እንዳንተ ነበር፣
ጌጣ ጌጡን ጥሎ የሰውን ልጅ ማክበር፣
የሰውን ልጅ ማፍቀር።

ሰተተተተተተተተት፤
ጌጡ ምን ሊረባ ሰው ካልታከለበት፣


ከድሮ ከድሮ ደገሂ ዋን ሁንዳ፣
ዱጋን ዱካመሜ ሰቦቱ በሬዳ።
አቺስ አከም አከም አከም፣
ፈጣሪ ሲጠይቅ መልሱ ሲጠራቀም፣
በብዕር ብራና በቃል ነው ወይ ማከም
176 views10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:54:44 በሰሞነ ሁዳዴ ህዝበ አዳም ፈሰከ፣
ለአምላኩ ታምኖ ለሴት ተማረከ።
እድሜ ላማረ ጥርስ ለገዳይ ፈገግታሽ፣
ስትስቂ ነው አሉ ስንቱን ፆም ያስፈታሽ።
.
.
"እድሜ ለፈገግታሽ"
.
.
የሚበር አሞራን 'ባንድ ተኩስ የምጥል፣
ከመንጋ ንብ መሃል ንግስት የምነጥል፣
ስሜ እንኳን ሲጠራ ልብ የማንጠለጥል፣
ኩሩ ጀግና ነበርኩ ሺ ገዳይ ባገሩ፣
ጠልፎ ጣለኝ እንጂ የሳቅሽ ገቢሩ።
.
.
በጥርስሽ ውብ ስንኝ በተደረደረው፣
አምላክ በጥበቡ ለጉድ በሰደረው።
ምን ተጋብቶት ይሆን የሚያደናቅፈኝ፣
በምንስ ስሌት ነው ሳቅሽ የጠለፈኝ።?
ብዬ አልጠይቅሽ ሸንጎ አልሰይም ነገር፣
ሀጃ አታውቅም ነፍስሽ ከመፈገግ በቀር።
.
.
እድሜ ለፈገግታሽ፤
እድም ላማረ ጥርስ፤
ልክ እንዳ'ባቶቼ ልክ እንደ ትላንቱ፣
ታንክ በከዘራ እንደማረኩቱ።
"ዘራፍ ወንዱ!
ቅጥሬን እንዳታልፉ አትንኩኝ" አልልም፣
በሳቅ ትጥቅ የፈታ ምርኮ አይሸልልም።
እድሜ ለፈገግታሽ፤
እድሜ ለጥርሶችሽ፤
እጅ የሰጠ ልቤ ከ'ግርሽ ስር የዋለ፣
ጀግና መች ይሆናል "ጀግና ነኝ" ስላለ።
.
.
ቢሆንም ቢሆንም፤
ብርቱ ነው የኔ ልብ ለሳቅ አይረታም፣
ላንዲት ቆንጆ ብዬ፤
እንኳን ቀበቶዬን ጫማዬን አልፈታም።
ያ ደማቅ ፈገግታሽ፤
የሳቅ ስርቅርቅታሽ፤
እያወናበደ ሩህ ቢወሰውስም፣
እኔ ያባቴ ልጅ!፤
ለምትስቅ ኮረዳ ልቤን አላውስም።
ማርኮ እንደረታ፤
ምሮ እንደፈታ፤
ከዘመን ቀድሜ፤
እንዲህ ስል የሸለልሁ በቀዬው ያናፋሁ፣
እንኳንስ ፈግገሽ፤
አይንሽን ሳይ ገና 'ባፍጢሜ ተደፋሁ።
( ድንቄም ያባቱ ልጅ¡¡ )

ተመልከች እንግዲህ፤
በየጥጋጥጉ በየሰርጣሰርጡ፣
ሀዘን የደረቡ ሳቃቸውን ያጡ።
እልፍ ያገሩን ሌጣ ስቀሽ ስታክሚ፣
የታረዘች ነፍሱን ሀሴት ስተሸልሚ።
እኔ ያንቺ ምርኮ በግዞትሽ ያለሁ፣
በሳቅሽ ታምሜ አልጋ ላይ ውያለሁ።

እናም የኔ አበባ፤
እንደ መ'ዳኒቴ ልክ እንደ እናቴ እቅፍ፣
ስንኩል ቀን ሸሽጎ ክፉ እንደሚያሳልፍ።
ሰርክ እየታወስሺኝ ስለምትናፍቂኝ፣
ፈገግታሽን ይዘሽ ነይና ጠይቂኝ።
157 views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:48:42 ጀግና የጀግንነት ጥግ
149 views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:48:24
173 views10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:47:48
181 views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 13:46:11
189 views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 20:38:24
1.9K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ