Get Mystery Box with random crypto!

ከወርቅ ከቡና፤ ከቂቤው ወዘና ፤ ከጊቤ ማህፀን ከእንብርቱ ፈልቀህ፣ እሳት ሲፈትንህ፤ ወርቅ ሆነህ | የታሪክ ማህደር

ከወርቅ ከቡና፤
ከቂቤው ወዘና ፤
ከጊቤ ማህፀን ከእንብርቱ ፈልቀህ፣
እሳት ሲፈትንህ፤
ወርቅ ሆነህ ኖረሀል ለሀቅ ተዋድቀህ።

ከነሆደ አምላኩ፤
ከነንትና ጎሬ፤
ሀድራው ሲደራ እጣን ተጫጪሶ፣
አንተ ግን እውነት ነህ፤
አጋንጠህ አድረሃል ለሊቱን በለቅሶ።
አንተ ሰው ሀቅ ነህ !
ሀሰት ያልበገረህ፤
ውሸት ያልመተረህ እውነት ስትል ወርደህ፣
ቢላል ለቀደሰው፤
ሼሁ ላወደሰው ለሀቂቃው አብደህ፣
እንደ ነበልባሉ እንደ እቶን ነደህ፣
የመኖርን እውነት፤
የእምነትን ፅናት የስልምናን ጥጉ፣
ኖሮ በማሳየት፤
ነበርክ እኮ ካስማው ነበርክ እኮ ዘንጉ።

አንተ የሰው ምሰሶ አንተ ያገር ማገር፣
አንተ የሰው ጥጉ አንተ የሰው ድንበር፣
አንተ የሰው ቅኔ አንተ የሰው ምስጢር፣
ፈርተህ የማትፈራ የጀግኖቹ ጀግና፣
በእሳት ንዳድ ውስጥ እምነትህ የፀና።

በደራው ገበያ፤
በሰፊው ጎዳና ገዢ ተቸንክሮ፣
ዝምታህ ተሽጧል፤
በሰባራ ፊደል በቃል ተቸርችሮ ።
እንኳን ሰው ቀርቶ፤
የአለም መቀመጫ ግዙፊቷ ምድር፣
አንተነትህ ከብዷት፤
መግዘፏ ተናንሶ ደክማ ስትታትር፣
የቃልህን ልቀት ነበረች ምስክር።

ይሄን ባየው ጊዜ ፤
ሰተት ብዬ ገባው ሰተት ብዬ ወጣሁ፣
ብዕሬን ሸክፌ፤
እንኳን የማቀልመው የማነበው አጣሁ።
በሀሰት ገበያ እውነት እንደ ቅርጫ፣
ነግዶ ማትረፊያ ሆኖ መለወጫ።
የኖርክለት ቅኔ የሞትክለት እውነት፣
በተውሶ ልምሻ ስንቱ እያጌጠበት።
እውነትን ማስፈሪያ ቃላት ባመሳጥር፣
አይጥ ሆኖ አገኘሁ የድንቢጥ ምስክር።

ሰተተተተተተተተተተት፤
ቃሉ ምን ሊረባ ሰው ካልታከለበት፣
መዶሻ ቢያቀና የጠመመ ብረት፣
ቅባት ተቀብቶ አይወረዛም እንጨት።
ቆንጆ ነኝ እያለ ሲመጣም ዝንጀሮ፣
አንይ እየተካደ ቢታመንም ጆሮ።
እውነታ በራቀው በማስመሰል አለም፣
የሚሆንህ ቀርቶ የሚመስልህ የለም።

አይ ከድሮ፤
ከኖሩማ አይቀር እንዳንተ ነበር፣
ጌጣ ጌጡን ጥሎ የሰውን ልጅ ማክበር፣
የሰውን ልጅ ማፍቀር።

ሰተተተተተተተተት፤
ጌጡ ምን ሊረባ ሰው ካልታከለበት፣


ከድሮ ከድሮ ደገሂ ዋን ሁንዳ፣
ዱጋን ዱካመሜ ሰቦቱ በሬዳ።
አቺስ አከም አከም አከም፣
ፈጣሪ ሲጠይቅ መልሱ ሲጠራቀም፣
በብዕር ብራና በቃል ነው ወይ ማከም