Get Mystery Box with random crypto!

ለክረምት የሴቶች ልጆች አዳሪ መርከዝ ፕሮግራም? በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፣ በጣም ሩህሩህ፡፡ | 👑ክብሯን የጠበቀች እንስት ሁሌም እዴተከበረች ትኖራለች!!💎

ለክረምት የሴቶች ልጆች አዳሪ መርከዝ ፕሮግራም?
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፣ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብዩ ሙሐመድ፣ በባለቤቶቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሀቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
ለክረምት ሴት ልጆችን በአዳራ ፕሮግራም ከ 12-18 እድሜ ያሉትን የቁርአን እና የኮርስ ፕሮግራም ለመስጠት አስበናል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ጥርጣሬዎችን ለማስወገድ ስል ይቺን አጠር ያለች ፅሁፍ አዘጋጅቻለሁ፡፡
ተውሒድ መርከዝ ላለፉት አራት አመታት በዋናነት የወንዶች አዳሪ ፕሮግራም ተቀብለን እየሰራን ነው፡፡ ለሴቶችም ተመላላሽ ደርሶች እና ቁርዓን ፕሮግራም ነበረው፡፡ አሁን አንፎ ድልድይ ሙሀጂር መስጂድ ላይ ዘውትር እሁድ የሚሰጠው ደርስም መጀመሪያው አነሳሱ ከተውሒድ መርከዝ ነበር፡፡ ፕሮግራሙም ለወንዶችም ለሴቶችም ነው፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እድሜያቸው ለምን በዚህ ገደብ ውስጥ እንዲሆን ተፈለገ?
በዚህ እድሜ ያሉ እህቶች በጣም የተርቢያ ትኩረት ስለሚፈልጉ ነው፡፡ መርከዙ ላይ ደርሱ በሴቶች ኡስታዞች ነው የሚሰጠው፡፡ ጊቢው በቁልፍ ይቆለፋል፡፡ ስልክ መያዝ አይፈቀድም፡፡ ለምንም ጉዳይ ከጊቢው መውጣት አይችሉም፡፡ ህመም ቢያጋጥማቸው እራሱ እዛው አካባቢ ክሊኒክ አለ፡፡ የሚሄዱትም ከእናቶች ጋር አብረው ይሆናል፡፡ እዚሁ ከተማ ያሉ ተማሪዎችን ነው የምንቀበለው፡፡ ከ 12 በታች ያሉ ተማሪዎች አብዛኛውን ጊዜ ቁርዓን ላይጨርሱ ይችላሉ፡፡
በአላህ ፍቃድ የራሴ የሴት ልጅ እዛው ውስጥ ተማሪ ስለምትሆን ለራሴ ልጅ የማደርገውን እንክብካቤ ሁሉ ለሌሎች ወንድምቼ ልጆች የቻልኩትን ጥረት አደርጋለሁ፡፡ እርዳታና እገዛንም ከአላህ እከጅላለሁ፡፡ በአላህ ፍቃድ ዘንድሮ ሴት እህቶቻችን
- በቀን 2 ጁዝ ቁርኣን እንዲቀሩ፣
- ከ ለሊቱ 10 ሰኣት ላይ ተነስተው ለይል እንዲሰግዱ እና ሙራጀአ እንዲያደርጉ፣
- ጁዝ አመ ተፍሲር (ትርጉም) እንዲማሩ፣
- አጠር ያሉ ኪታቦችን 2 ወይ 3 ቀርተው እንዲወጡ በሁለት ወር ውስጥ በአላህ ፍቃድ እንሞክራለን፡፡
ወንድምና እህቶቼ ሌላ የማታውቁትን እና ያላያችሁትን ነገር አታውሩ አላህ ዘንድ ያስጠይቃችኋል፡፡
በአላህ ፍቃድ ከተማው ላይ ያሉ ሌሎች ቦታዎች ላይ በተመላላሽ ከ 12 አመት በታች ላሉ ወንዶችና ሴቶች በቀኑ ክፍለ ጊዜ፣ ከአሱር በኋላ ለአዋቂ ሴቶችና ወንዶች የክረምት ኮርሶች በአላህ ፍቃድ ይሰጣሉ፡፡ ምዝገባውን፣ ቦታውና ፕሮግራሞቹን ጭምር በአላህ ፍቃድ እናሳውቃለን፡፡
አላህ እሱ ለሚወደው ተግባር ይምራን፡፡ መጨረሻችንን ያሳምርልን፡፡
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem