Get Mystery Box with random crypto!

የንባብ ገፅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenibab_gets — የንባብ ገፅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenibab_gets — የንባብ ገፅ
የሰርጥ አድራሻ: @yenibab_gets
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.01K
የሰርጥ መግለጫ

ከምርጦች የተሰባሰቡ የስነፅሁፍ ማህደሮች
(ግጥም፣ወግ፣ልብወለድ፣ሙዚቃ)
#በድምፅና #በቪዲዮና #በፅሁፍ እዚህ ያገኛሉ።
ይህን ይጫኑ @yekal_tebta
Inbox @Natitg2 0940219376
@Dagi_tecno @akuna444
ፕሮግራማችን
እሁድ_ከክላሲካል ጋር የተቀናበሩ የድምፅ ግጥሞች
ማግሰኞ_የድንቅ ደራሲዎቻችንን ወጎች በድምፅ
ሃሙስ_የሳምንቱ ምርጥ ሙዚቃ ግብዣችን
ቅዳሜ የመፅሃፍ ትረካና ግብዣ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-23 03:30:16 @ ጎ ጃ ም
…………………………………………………
ጎ ጃ ም ማለት ምን ማለት ነው
……………………………………………………………………
@ ፈጣሪ ከጥፋት ውሃ በሗላ ለኖህ እዲህ ሲል ቃል ገባለት ። ከእንግዲህ ወዲያ ፍጥረት በጥፋት ውሃ አይጠፋም። የቃል ኪዳን ምልክት የሆነ ቀስቴንም በደምና ላይ አኖራለሁ ። ዘፍ9"
ኖህም አዳም ጥፋት አጥፍቶ ከተባረረባት ምድር
መኖር ጀመረ ። ስሟንም አዳም ከተባረረባት ምድር እግዛብሄር እራርቶልኝ ፈቀደልኝ ሲል
ጌታ ራራ ሲል ሰየማት። ከጊዜ በሗላም ፡ታ ፡
ን አውጥተው ጌራራ ተባለች ያሁኒት ጎጃም

ኖህ የተቀበረበት ጎንደር ፋሲለደስ ቤተ መግስት የተሰራበት ላይ ሲሆን የሚስቱ የእመት አይክል መቃብር በጭልጋ ነው ይባላል።
ከእመት አይከል መቃበር ላይ ታላቅ ዛፍ በቅሎበት ቅማቶችም ፀሎት ያደርሱበታል ይባላል

አፄ ፋሲል የነገሱ ግዜም አምላክ ሁሉን ነገር ገልጦላቸው የኖህ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በኖህ መርከብ አምሳል ቤተ መንግስት በኖህ መቃብር ላይ ሰሩ ። ጎንደር ማለት ጉንድ ሀገር ፡ ከሚል የግእዝ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም የአገር ራስ ፡ ማለት ነው። ከጥፋት ውሃ በሗላ ለሰው ዘር የተረፈው ፡ የአለም አገራት ህዝቦች ሁሉ አባት የሆነው ኖህ የተቀበረበት ስፍራ ነውና የአገር ራስ ትባላለች ።

@ በከነዓን ረሀብ በገባ ጊዜ አብርሀም ወደ አዜብ ምድር ፡ ኢትዮጲያ ፡ መጥቶ ፡ ከጌራራው ንጉስ ከአቤሜሌክ ጋር ተቀመጡ ። ዘፍ 20።
አቤሜሌክ በአፄ ቴድሮስ ዘመን እደነበሩት የጎዥም ደጃዝማች ተደላ ጓሉ ያለ ደግ ፡ በህዝብ ዘንድ የተወደደ ስለ ነበር አቤሜሌክ ሲሞት ህዝቡ ለመታሰቢያ ይሆን ዘንድ ጌራራ ይባል የነበረውን አበሜለከክ ሲሉ ሰይመውታል ። አበሜለክ ማለት ደግሞ አባት ማለት ነው ይላሉ ።

ብዙ ጥንታዊ በልሳን ግዕዝ የተፃፉ መጠሀፍት አበሜለክ ተብለው ተፅፈው እናገኛለን። የጎንደር ታሪክን መፅሀፍ የፃፉት ያሬድ ግርማ ሀይሌ የጎጃምን ስም አበሜለክ ብለው ፅፈውታል ።

ጥንታዊ ግብጣዊያን አባይ ፈልቆ የሚመጣልን ከአምላክ ዙፋን ስር ነው ብለው ያምኑ ስለነበር በዚህም የተነሳ ፡ ጎዣም፡ ተባለ ይላሉ።
ጎዣም ፡ ማለትም የአምላክ ምድር ፡ የአምላክ መፈጠሪያ ፡ ማለት ነው። አዳም የተፈጠረበት ምድር ነው ሲሉ ሊቃውንቱ ይተነትኑታል ።

ከክርስቶስ ልደት በፊት ወደ አማራ ምድር የመጣው ግሪካዊው አጥኝ ሄሮዱቱስ ፡ ጎዣም፡ ማለት የአምላክ ምድር ማለት ነው። ጎዣም የደጋጎች ፡ የበቁ ቅዱሳን መኖሪያ ናት ።ብሎ ጥፏል ።

አዳንድ ሰዎች ፡ጎዣም ፡ ከመባሉ በፊት ፈለገ ግዮን ይባል ነበር የሚሉም አሉ።
በገድለ ቅዱስ ዘርአብሩክ ተፅፎ እደምናገኘው ግን ፈለገ ግዮን የሰከላ ወረዳ መጠሪያ እንጂ የሙሉ ጎጃም መጠሪያ አይደለም።

አንድም ጎጃም ማለት ቃሉ አማረኛ ሲሆን ትርጉሙም ፡ ጎጇም ፡ ቤታም ፡ ቤተኛ፡ የስልጣኔ ምንጭ ማለት ነው ።

የሰው ልጅ በዋሻ ፡ የድንጋይ ቤት ሰርቶ በየዛፉ ሰሌን ሰርቶና ዘርግቶ በድንኳን ይኖርበት በነበረበት ዘመን ፡ ጎጃሞች፡ ግን ሳር አጭደው ፡ እጨት ቆርጠው ፡ ጎጆ፡ ቤት ፡ በመስራት የሰው ልጅ ቤት ሰርቶ እዲኖር አድርገዋልና ጎጃሞች ቤታሞች ቤተኞች ጎጇሞች የስልጣኔ ምጮች ይባላሉ።

የጎጃም ስሞች በቅደም ተከተል
@ጌታ ራራ
@ ጌራራ
@ አበሜሌክ
@ ጎዣም

በሗላም ፡ዣ ፡ ትቀርና ወደ ፡ ጃ፡ ተለውጣ ጎጆ ቤት ከአለም ቀድሞ የተሰራው ጎጃም ላይ ስለሆነ ጎጃም የተባለ ሲሆን ጎጃሞ ማለትም የአምላክ ምድር ፡ የአምላክ ፡መፈጠሪያ ፡ የስልጣኔ ምንጭ ማለት ነው።

፡ ጎጃም የቅኔ መቀኛ የእውቀትና የጀግንነት መፍለቂያ የስልጣኔ ምንጭ ናት






፡ ፡

@yenbab_gets
178 views【Nati..B】, 00:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 03:24:42
መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንልህ።

ደራሲና ኃያሲ እንዳለ ጌታ ከበደ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ ጉዞ ጀመረ ፦

ተወዳጁ ደራሲ ይህን የትምህርት እድል ያገኘው ከ 115 የዓለም ሀገራት ጸሐፍቶች ጋር ተወዳድሮ ሲሆን ፤ ከሀገራችንም ለእጩነት ከቀረቡት 3 ተፎካካሪዎቹ በብቸኝነት አሸንፎ ነው።

አፍሪካን በመወከል ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ግብፅ፣ ዚምባብዌ፣ ጋናና ቤኒን የተሳተፉ ሲሆን አንድ አንድ አሸናፊዎቻቸውን በመላክ አህጉራችን በአምስት ደራሲያን እንድትወከል አድርገዋል።

ዛሬ ማምሻውን ጉዞ የጀመረው እንዳለጌታ ቆይታውን የሚያደርገው የሥነ-ጽሑፍ ከተማ ተብላ በዩኔስኮ በተመዘገበችዋ Iowa ግዛት ሲሆን ፤ ለዓመታት እንደሚቆይና ሙሉ ወጪውንም ዩኒቨርስቲው እንደሚሸፍንለት ሰምተናል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ በታሪክ እንደዚህ አይነት እድል አግኝታ የምታውቀው በ 1947 ዓ.ም. ሲሆን ፤ የወቅቱ ተመራጭ ደራሲዋ ደግሞ ዳኛቸው ወርቁ ነበር።

ምንጭ-ኢትዮፒካሊንክ
@DBU_ENTERTAIN
189 views【Nati..B】, 00:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 02:45:14
ባል የሚገዛበት የህንዱ የሙሽራ ገበያ

ከ700 ለሚበልጡ ዓመታት የህንድ የቢሃር ግዛት ሴቶች
በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶች በህንድ ቢሃር ግዛት ማዱባኒ በተባለ በአከባቢ ወደሚገኘው የገበያ ቦታ በመሄድ ፒፓል ዛፎች ስር የሚሰበሰቡ ሲሆን፤ እዛ በመሆንም ሚስት የምትሆናቸው ሴት እስክትመርጣቸው ድረስ ይጠባበቃሉ።

የሙሽራ ገበያው “ሳውራት ሜላ” ወይም “ሳባጋቺሂ” እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፤ በዓመት አንድ ጊዜ የሚቆምና ለ9 ቀናት ይቆያል።

በራጃ ሃሪ ሲንግ የካርናት ስርወ መንግስት ከ700 መቶ ዓመታት በፊት እንደተጀመረ የሚነገርለት ይህ የባል ገበያ ሴቶች ይሆነኛል ብለው ያመኑበትን ባል እንዲመርጡ ለማስቻል እንደተጀመረ ተግሯል።

በገበያው ባል ለመሆን ለሚቀርቡ ለእያንዳንዱ ሙሽራ የትምህርት ደረጃቸውን እና የቤተሰቡን የኑሮ ሁኔታ መሰረት ባድረገ መልኩ ዋጋ የሚቆረጥለት መሆኑም ተነግሯል።

የቢሃር ባህላዊ የሙሽራ ገበያ ኢንጂነሮች፣ ዶክተሮች እና የመንግስት ሰራተኞች በጣም እንደሚፈለጉ የሚነገር ሲሆን፤ ወጣቶች በጣም ተወዳጅ እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በባል መረጣ እና ግዢው ላይ ከሙሽሪት ይልቅ ለቤተሰቦቿ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፤ በዚህም ጥሩ ልምድ ያለውን ባል በተመጣጣኝ ዋጋ በማመዛዘን የሚወሰን ይሆናል።

ምንም እንኳን ጥሎሽ በህንድ ውስጥ በይፋ ህገ-ወጥ ቢሆንም፣ አሁንም ወጣት እና ብቁ የሆኑ ዋት ያላገቡ ወንዶች ከሙሽሪት ቤተሰብ ከፍተኛ ጥሎሽ እንደሚጠይቁ ይነገራል፤ የሙሽራ ገበያው ዋነኛ ዓላምም ጥሎሽለን ለማስቀረት ያለመ ነው ተብሏል።

የሚያስገርመው በህንድ የባል ገበያ እንዳለ ሁሉ የሚስት ገበያም መኖሩ ሲሆን፤ በህንድ ሃውዳቲ ውስጥ በሚገኘው የሙሽሪት ገበያ እንደየብቃታቸው እና የቤት ስራ ችሎታቸው ለተለያዩ ዋጋዎች ተቆርጦላቸው ያገባሉ።

@YENIBAB_GETS
175 views【Nati..B】, 23:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 21:46:58 አለማጋራት ንፉግነት ነው !!
==================
አፄ ሚኒሊክ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀሟቸው አምስት ለማመን የሚከብዱ ዘግናኝ ታሪካዊ ወንጀሎች !!!!!

ስለ አፄ ምኒሊክ ብዙ ግዜ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን ፅፊያለሁ። ነገር ግን ታሪክን ታሪክ የሚያሰኘው ጥሩውንም መጥፎውንም ስናውቅ ነውና አፄ ሚኒሊክ ከሰሩት ጥሩ ነገር ባሻገር የሰሩትን አምስት ታሪካዊ ጥፋቶች ደግሞ እንደሚከተለው በአጭሩ አስቀምጣለሁ ።

1ኛ . በዘር ተከፋፍሎ እርስ በእርስ በፍቅር እየተዋጋና በሰላም እየተገዳደለ ሲኖር የነበረውን ጨዋ ህዝብ በግድ አንድ ሁን ብለው መንግስት መስርተው ያለ ፍላጎቱ በሰላምና በፍቅር እንዲኖር አደረጉት ።

2ኛ . ቴሌቪዥን የሰይጣን ስራ ስለሆነ እምቢ አላይም ያለውን ስልጡን ብሔር ጦር አዝምተው አዝምተው በፍቅር ከማረኩት ብኋላ ቤተ መንግስት አስገብተው እጅግ ዘግናኝ በሆነ መልኩ ሲኒማ እንዲያይ አደረጉት !! አቤት የሚኒሊክ ጭካኔ

3ኛ . ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ ድረስ በእግሩ ዘና እያለ ሀገር እያየ ለሶስት ወር ሲጓስ የነበረውን ህዝብ ባቡር የሚባል ነገር አስመጥተው ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ በአንድ ቀን እንዲገባ አድርገውት በእግሩ ወክ እያደረገ እንዳይሄድ ከለከሉት ።

4ኛ . ጣሊያን ኢትዮጵያን ወርሮ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ በእኩልነትና በፍቅር እየረገጠ
ሊገዛ ሲመጣ ሚኒሊክ ግን አይሆንም ብሎ ተዋግቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ በግድ ነፃነት ሰጠ ።

5 ኛ . እህል በድንጋይ እየፈጨ የጣፈጠ ምግብ ሲበላ የኖረውን ብሔር ምንም ሳያስፈቅዱት ወፍጮ የሚባል ማሽን አስመጥተው ህዝቡ ወፍጮ ቤት ገብቶ እንዲያስፈጭ አደርገውት የዱቄት ብናኝ የህዝቡ አይን ውስጥ እንድገባ አደረጉ !!!!

ይሄን ሁሉ ጭካኔ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈፀሙት ንጉስ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ከአንድ መቶ ሰባ አምስት አመታት በፊት ነው የተወለዱት ።


@yenibab_gets
277 views【Nati..B】, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 20:36:55 Samsung
ምን ማለት ነው

Sam በኮርያ ቋንቋ 3 ማለት ሲሆን
Sung. ማለት ደግሞ ኮከብ ማለት ነው
3ቱ ኮከቦች እንደማለት ነው
ይህም 3 መርሆችን ለመከተል ያደረገው ነው
Great,Numerous, Power

ትልቅ ሃያልና ጠንካራ ድርጅት የመሆን ህልሙን በስሙ አትሞታል።

የንባብ ገፅ
@yenbab_gets
300 views【Nati..B】, 17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 18:53:21 Channel photo updated
15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 11:56:54 ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች

ናትናኤል ነኝ
ከዛሬ ጀምሮ ወደ ቴሌግራም ቻናል ገፄ ተመልሻለው።ለተወሰነ ጊዜ ከዚህ በመጥፋቴም 3500 የነበረው ተከታይ አሽቆልቁሎ 1200 ደርሷል።

በፊት የቃል ጠብታ የነበረውንም ስም ወደ
" የንባብ ገፅ" ቀይሬው አብረን እንቆያለን። ያላችሁን አስተያየትና ሃሳብ @NatiTg2 ላይ እንድትገልፁልኝ እላለው።

ቸር እንቆይ
308 views【Nati..B】, edited  08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 11:52:08 Channel name was changed to «የንባብ ገፅ»
08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 11:25:23 ሁለቱም የግጥም ስራዎቼ ነሃሴ ዓመት ይሞላቸዋል። በዓውደ አመት ማግስት ነሃሴ ላይ አሳዛኝ ክስተትን ሰምተን ነበር። አመት የሞላው ቢሆንም ግን ሃዘን ለአዛኙ ሁሌም አዲስ ነው።
አበባ አየሽ ወይ ልንል ስንል የእንባ እንባ አየሽ ወይ ወደሚል ዜማ በተቀየረበት ጊዜ ነበር።
የደም ዘመን የሚል ርዕስ የሰጠሁት
የደም ዘመን






ደግሞም በሃገር ባህል ወግ ለሃዘን ድባብ ልብስ ይመረጣል። ቀይ እንልበስ ወይስ ጥቁር ወይንስ ነጭ አልኩ።

ሃዘንም የልብስ ጌጥ አለውና።


የሃዘን ልብስ







ሁለቱንም ስራዎች ሊንኩን በመንካት መመልከት ትችላላችሁ።
633 viewsNati. B, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 06:29:25 ቅኑን በቅን አቅኑት አቤል አማረ እና ናትናኤል ብርሃኑ


2.1K viewsNati. B, 03:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ