Get Mystery Box with random crypto!

Ministry of Labor and Skills - Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ fdre_mols — Ministry of Labor and Skills - Ethiopia M
የቴሌግራም ቻናል አርማ fdre_mols — Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @fdre_mols
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.48K
የሰርጥ መግለጫ

FDRE, Ministry of Labor and Skills

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-11 14:17:29 ከስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሀገራቸው የሥራ ዕድል እንዲመቻችላቸው ማገዝ ከሁሉም እንደሚጠበቅ ተገለፀ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከጃምቦ የፅዳት አገልግሎት ድርጅት እና ፈርስት ኮንሰልት ጋር በመተባበር በመሰረታዊ የፅዳት አገልግሎት የሰለጠኑ 1ሺህ 86 ከስደት ተመላሽ ዜጎች ስልጠናቸውን አጠናቀዋል።

ሰልጣኞቹ በሀገራቸው ላይ እንዲሰሩ ለተመቻቸላቸው ዕድል ምስጋናቸውን በገለፁበት ሥነስርዓት ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ሥምሪት ማስፋፊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃኑ አበራ በተለያዩ ሀገራት የተሻለ የሥራ ዕድል ፍለጋ ከሄዱት መካከል በሳዑዲ ከሚገኙት መቶ ሁለት ሺህ ዜጎችን የመመለስ ሥራው መቀጠሉን የገለፁ ሲሆን፥ እስካሁንም 76ሺህ ዜጎችን መመለስ መቻሉን ገልፀው ለእነዚህ ዜጎች ተባብሮ የሥራ ዕድል ማመቻቸት ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

በመንግስት በኩል የመመዝገብ ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀው ከ1ሺህ በላይ ለሚሆኑት ዜጎች የተሰጠው ስልጠና ከግሉ ዘርፍ ጋር በመተባበር ስምምነት በመፈፀም ዜጎቹን ወደሥራ ለማሰማራት የተደረገው ጥረት አካል ነው ብለዋል።

ዜጎቹን በፅዳት ሥራ አሰልጥኖ ወደ ሥራ ለማሰማራት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር እየሰራ የሚገኘው ጃምቦ የፅዳት አገልግሎት ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ገብርዬ በበኩላቸው ስልጠናው ለሥራ የሚያዘጋጅ መሆኑን ተናግረው ራሳቸውንና ወገናቸውን የሚጠቅሙበት እንደሚሆን እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ የሥራ ኢንተርፕራይዝና ልማት ቢሮ የሥራ ስምሪትና ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት አቶ ሰብሃዲን ሡልጣን በከተማዋ ከተመዘገቡት ከስደት ተመላሽ ሥራ ፈላጊ 7ሺህ 280 ዜጎች 1ሺህ ያህሉ ለመጀመሪያ ዙር መሰልጠናቸውን ተናግረው ቀጣይ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
939 views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 14:17:07
825 views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 22:09:00 ኤች. አይ. ቪ. ኤድስ በሥራ ቦታ ስርጭቱ ለመግታት የአሰሪና ሰራተኞች ግንዛቤ የሚያሳድጉ ተግባራት ማከናወን እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዓለም የኤች አይቪ ኤድስ ቀንን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡

በዉይይት መድረኩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች፣ የአሰሪና ሰራተኛ ፌዴሬሽንና ኮንፌዴሬሽን ተወካዮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ተካልኝ አያሌዉ እንደገለጹት፤ ኤች አይ ቪ ኤድስ በስራ ቦታዎች ወጣቶችንና አምራች ኃይል ላይ መጠነ ሰፊ ጉዳት እያደረሰ በመሆኑ በተለይ አሠሪና ሠራተኞች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መስራት ወሳኝ ነው፡፡

በመሆኑም ፋብሪካዎች እና ድርጅቶች ከመደበኛ ስራቸዉ ጎን ለጎን የቫረሱ ስርጭት መግታት የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በስራ ቦታ ላይ የሰራተኞች የሙያ ደህንነትና ጤንነት ላይ አቅዶ እየሰራ ይገኛል ያሉት መሪ ስራ አስፈፃው በተለይ ኤች አይቪ ኤድስ በስራ ቦታ ለመቆጣጠር እና ስርጭቱን ለመግታት የሶስትዮሽ ፖሊሲ ማዕቀፍ በኢትዮጰያ አሰሪዎች ፌዴሬሽንና ኮንፌዴደሬሽን፣ በኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽንና በስራና ክህሎት ሚኒስቴር መካከል በጋራ ለመስራት በመፈራረም አበረታች እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሥራ ሁኔታዎች ቁጥጥርና የሙያ ደህንነትና ጤንነት ዴስክ ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ታደሰ በበኩላቸዉ ስራዉ የሁሉም አካላት ቅንጅትና ትኩረት የሚሻ በመሆኑ በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ስርጩቱን ለመግታት ይሰራል ብለዋል፡፡//

ሕዳር 30/2015 ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
1.5K views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 22:08:57
1.3K views19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 13:12:36 የኢትዮ- ቻይና የቴክኒክና ሙያ ልማት ህብረት ይፋ ተደረገ

በቻይና አዘጋጅነት ዛሬ በተካሄደው የዓለም አቀፉ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት እድገት ኮንፈረንስ የኢትዮጵያ- ቻይና የቴክኒክና ሙያ ልማት ህብረት ተመስርቶ ይፋ ተደረጓል፡፡

በኮንፈረንሱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስት ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በቻይና እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የትብብር ማዕቀፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፡፡

ቻይና በኢትዮጵያ በትምህርትና ስልጠናው ዘርፍ እያደረገች ያለችው ድጋፍ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር እውን እንዲሆን ያደረገ ሲሆን ይህም የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው፡፡

የልማት ህብረቱ በቻይና እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ የንግድ ማህበራት፣ ባለሙያዎችና ምሁራንን የሚያስተሳስር ከመሆኑም በላይ ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለመስጠር የሚያስችል ምህዳር ለመፍጠር የሚረዳ ነው ብለዋል።

በመድረኩ በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ውስጥ 30 የሥልጠና ማዕከላትን በመገንባት 20 ሺህ የሚሆኑ ዜጎችን እንደሚሰለጥኑ፣ 100 የሚሆኑ ተቋማት ዓለም አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ደረጃዎችን እንዲያሟሉ እንዲሁም አንድ ሺህ ለሚሆኑ አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና ሰራተኞች የአጫጭርና የረዥም ጊዜ ስልጠናን እንዲያገኙ እንደሚደረግ ተመላክቷል፡፡
2.6K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 13:12:10
1.8K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 16:10:00 Live: Part 2


5.0K views13:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 09:50:34 Live


2.5K views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 00:43:27
2.2K views21:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 00:43:04 ሚሊዮን ፈተናዎች፤ ሚሊዮን ዕድሎች በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ በሚገኘው የኢንተርፕሪነርሺፕ ሣምንት ለችግር እጅ ሳይሰጡ ችግርን እራሱ ድል የነሱ፣ ከራሳቸው አልፈው ለበርካቶች ሥራ የፈጠሩና አርአያ የሚሆኑ #ፈርጦቻችን በአካል ተገኝተው ልምድና የህይወት ተሞከሯቸውን አካፍለዋል፡፡
2.1K views21:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ