Get Mystery Box with random crypto!

ኢራን በእስራኤል ላይ የምትሰነዝረውን ጥቃት መጀመሯን አስታወቀች! ኢራን ወደ እስራኤል በርካታ ቁ | YeneTube

ኢራን በእስራኤል ላይ የምትሰነዝረውን ጥቃት መጀመሯን አስታወቀች!

ኢራን ወደ እስራኤል በርካታ ቁጥር ያላቸው ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን መተኮሷን አስታወቀች።እስራኤል ባሳለፍነው ሳምንት በሶሪያ መዲና ደማስቆ በሚገኝ የኢራን ኢምባሲ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ወታደራዊ አዛዦችን ጨምሮ ዘጠኝ ኢራናዊያ መገደላቸው ይታወሳል።ይህንን ተከትሎ በኢምባሲዋ ላይ ለደረሰው ጥቃት እስራኤልን እንደምትበቀል ስትዝት የቆየችው ኢራን በዛሬው እለት መጠነ ሰፊ የድሮን እና ሚሳዔል ጥቃተ ወደ ቴልአቪቭ መክፈቷን አስታውቃለች።

የኢራን ሪቮሉሽናሪ ጋርድ ዛሬ ምሽት በሰጠው መግለጫው፤ ወደ እስራኤል ድንበር በርካታ ሚሳዔሎችን እና ድሮኖችን መተኮሱን አስታውቋል።እስራኤል በበኩሏ በርካታ ድሮኖች ከኢራን መተኮሳቸውን ያረጋገጠች ሲሆን፤ ሚሳዔል ስለመተኮሱ ግን እስካሁን ማረጋገጫ አላገኘሁም ብላለች።የእስራኤል ጦር ቃል አቀባይ በሰጡት አስተያየት፤ ኢራን ወደ የተኮሰቻቸው ድሮኖች የእስራኤል ድንበር ላይ ለመድረስ ሰዓታት ይፈጃሉ ብለዋል።

ኢራን ወደ እስራኤል ድሮኖችን እና ሚሳዔሎችን እንደተኮሰች ማሳወቋን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔታ በፍጥነት እየተቀያየረ ሲሆን፤ መንግስታትም የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛል።ጆርዳን፣ ሊባኖስ እና ኢራቅ የአየር ክልላቸውን መዝጋታቸውን ያስታወቁ ሲሆን፤ እነዚህ ሶስቱ ሀገራት የኢራን ድሮኖች እና ሚሳዔሎች ሊያልፉባቸው የሚችሉ ናቸው ተብሏል።ኢራን እና እስራኤልም ከወታደራዊ አውሮፕላኖች በስተቀር ለሌሎች አውሮፕላኖች የአየር ክልላቸውን መዝጋታቸው ነው እየተነገረ ያለው።

ኢራን በእስራኤል ላይ የአየር ወለድ ጥቃትን መጀመሯን የአሜሪካው ነጩ ቤተ መንግስት ወይም ዋይት ሀውስ አስታውቋል።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በብሔራዊ ደህንነት ቡድናቸው አማካኝነት ስለሁኔታው በመደበኛነት እየተከታተሉ መሆኑም ተነግሯል።ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና ቡድናቸው ከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር በተደጋጋሚ ግንኙነቶችን እያደረጉ እየተወያዩ መሆኑን ዋይት ሃውስ አስታውቋል።አሜሪካ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ተጨማሪ ኃይል መላኳም ይታወሳል።

[Al Ain]
@YeneTube @FikerAssefa