Get Mystery Box with random crypto!

በዛሬው ዕለት ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ! በ3ኛው ምዕ | YeneTube

በዛሬው ዕለት ከ1 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ!

በ3ኛው ምዕራፍ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሳኡዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለስ ስራ እየተከናወነ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 71 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ ተችሏል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 1 ሺህ 71 ዜጎች ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ዘጠኙ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ተብሏል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa