Get Mystery Box with random crypto!

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ! | YeneTube

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ!

ከዚህ ቀደም ሲሰራበት የነበረዉን ደንብ በመሻር የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ለሚሰጣቸው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታዉቋል።

የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ አገልግሎት አዲሱ ደንብ ከመዉጣቱ በፊት ሲሰራበት የነበረዉን የሰነዶች ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎቶች ክፍያን በመሻር ማሻሻያዉ ከሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው የሰነድ ማረጋገጥ እና ምዝገባ አገልግሎቶች ክፍያ ለመወሰን ባወጣዉ በዚህ ደንብ በተቀመጠው አዲሱ የክፍያ መጠን የሰነድ አይነቶቹ ቢለያይም ለሁሉም አገልግሎቶች ከ 200 ብር ጀምሮ እስከ 500 ብር ድረስ ክፍያን ይጠይቃል።

ካፒታል በተመለከተዉ በዚህ ደንብ ላይ ለሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ሽያጭ ዉል ሰነድ ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረቶች ሽያጭ ፣ ለመመስረቻ ፅሁፍ ሰነድ እና በስጦታ መልክ ለሚሰጡ ንብረቶች ዉል ሰነድ የክፍያ አገልግሎት ተመን ከወጣላቸው መካከል ዉስጥ ተካተዋል።

@YeneTube @FikerAssefa