Get Mystery Box with random crypto!

የልጁን ፍቅረኛ ለማስገደል 40 ሺህ ዶላር የከፈለው ፓስተር 40 ሺህ የተከፈለው ቅጥረኛ ገዳይ የ | YeneTube

የልጁን ፍቅረኛ ለማስገደል 40 ሺህ ዶላር የከፈለው ፓስተር

40 ሺህ የተከፈለው ቅጥረኛ ገዳይ የተኮሳቸው ጥይቶች ሳይገድሉት ቀርተዋል ተብሏል የልጁን ፍቅረኛ ለማስገደል 40 ሺህ ዶላር የከፈለው ፓስተር

ፓስተር ሳሙኤል ዳቫሎስ የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት የሚኖር የሀይማኖት መምህር ነበር፡፡

ይህ የጌታ አገልጋይ የሆነው ሰባኪ እና መምህር ሴት ልጁ በቅርቡ ያዘችውን አዲስ ፍቅረኛ አልወደደውም፡፡ ልጁንም እንዲህ አላት ፍቅረኛሽ ደስ አይለኝም፣ አልወደድኩትም ስለዚህ ከእሱ ራቂ ሲል ያስጠነቅቃታል፡፡

ፍቅረኛዋ በአባቷ ያልተወደደላት ይህች ወጣት እንስትም እንደተባለችው ፍቅረኛዋን አባቴ አልወደደህም እና ፍቅራችን መቀጠል አይችልም ከማለት ይልቅ አብራው መቀጠልን መረጠች፡፡
ትዕዛዙ በልጁ ያልተከበረለት ፓስተር ሳሙኤልም ይህን ያልወደዱትን የልጃቸውን ፍቅረኛ ለማስወገድ ይመርጣሉ፡፡

ለዚህ እቅዳቸው እንዲረዳቸውም ቅጥረኛ ገዳይ በ40 ሺህ ዶላር የቀጠሩ ሲሆን የልጃቸውን ፍቅረኛ አድራሻ ይሰጣሉ፡፡
ይሁንና 40 ሺህ ዶላር ተከፈለው ይህ ቅጥረኛ ግደል የተባለውን ወጣት በተሽከርካሪው ውስጥ እያለ የተኮሳቸው በርካታ ጥይቶች ኢላማቸውን ስተው የወጣቱ ነፍስ ተርፋለች ተብሏል፡፡

ወጣቱ የገጠመውን የመቁሰል አደጋ በአቅራቢያው ወዳለ ሆስፒታል ራሱ አምርቶ ታክሟል የተባለ ሲሆን ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታተል በመጨረሻም የወጣቱ ፍቅረኛ አባት ዋና አቀነባባሪ መሆናቸውን በምርመራው አረጋግጧል፡፡

የ47 ዓመት ጎልማሳ የሆኑት የፍቅረኛው አባት ከሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በህግ ቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

ABC News
@Yenetube @Fikerassefa