Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ የፈጸ | YeneTube

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ውስጥ የፈጸሟቸውን ወንጀሎች ለመዳኘት አገራዊ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፍ በቂ አይደለም በማለት ስጋታቸውን ገልጠዋል። ጌታቸው ይህንኑ ስጋታቸውን የገለጡት፣ ከተመድ ስደተኞች ኮሚሽን የምሥራቅ አፍሪካ ሃላፊ ማርሴል ክሊመንት ጋር መቀሌ ውስጥ በተወያዩበት ወቅት እንደኾነ የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ክሊመንት በበኩላቸው፣ በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ ወንጀሎችን የማየቱ ሂደት ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ መኾን እንዳለበት መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። በርካታ አገር በቀል ሲቪል ማኅበራትም፣ በረቂቅ ደረጃ ላይ የሚገኘው የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ማዕቀፍ የኤርትራ ወታደሮች በጦርነቱ ወቅት የፈጸሟቸውን ወንጀሎች ጭምር እንዲያካትትና የኤርትራ ወታደሮችን ወንጀሎች የሚመለከት ልዩ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም የሚጠይቅ የምክረ ሃሳብ ሰነድ በቅርቡ ለፍትህ ሚንስቴር ማስገባታቸው ይታወሳል።

[Wazema]
@Yenetube @FikerAssefa