Get Mystery Box with random crypto!

ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ጋር በታሰሩት የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር ላይ አምስት ተጨማሪ የምርመራ ቀናት በ | YeneTube

ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ጋር በታሰሩት የኦነግ የፖለቲካ ኦፊሰር ላይ አምስት ተጨማሪ የምርመራ ቀናት በፍርድ ቤት ተፈቀደ!

ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ጋር አብረው የታሰሩት፤ ፖለቲከኛው አቶ በቴ ኡርጌሳ ላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ አምስት የምርመራ ቀናት ፈቀደ። የአዲስ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀናቱን የፈቀደው፤ ፖሊስ “የተጠርጣሪውን ስልክ ምርመራ ውጤት ለመቀበል” ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ያቀረበውን ማመልከቻ በመቀበል ነው።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የሆኑት አቶ በቴ፤ “አፍሪካ ኢንተለጀንስ” ለተሰኘው የዜና ድረ ገጽ ዘጋቢ ከሆነው አንቷን ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለፈው ሳምንት ሐሙስ የካቲት 14፤ 2016 ነበር። የኦነጉ ፖለቲከኛ እና ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት ባለፈው ቅዳሜ በቀረቡበት ወቅት፤ ፖሊስ “ከፋኖ እና ከኦነግ ሸኔ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሁከት ለማስነሳት በመሞከር” እንደጠረጠራቸው መግለጹ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አስቀድሞ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት የተጠርጣሪዎቹን ጉዳይ መመልከት ሲጀምር፤ ቅድሚያ የማስረዳት ዕድሉን የሰጠው ለመርማሪ ፖሊስ ነው። ፖሊስ በተሰጡት ስድስት ቀናት፤ የአንድ ሰው ቃል መቀበሉን እና የተጠርጣሪዎችን የሞባይል ስልክ ለማስመርመር ወደ ፌደራል ፖሊስ መላኩን አስረድቷል። ሆኖም የስልክ ምርመራ ውጤቱን ተቀብሎ ከምርመራ መዝገቡ ጋር ማያያዝ እንደሚቀረው ገልጿል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa