Get Mystery Box with random crypto!

በ19ኛው ክፍለ ዘመን በብሪታኒያ ወታደሮች ከኢትዮጵያ የተወሰደውን ጋሻ የሀገሪቷ መንግስት ጫና ተከ | YeneTube

በ19ኛው ክፍለ ዘመን በብሪታኒያ ወታደሮች ከኢትዮጵያ የተወሰደውን ጋሻ የሀገሪቷ መንግስት ጫና ተከትሎ ዛሬ የሚደረገዉ የጨረታው ሽያጭ እንዲሰረዝ ተደርጓል!

እንግሊዝ በ 1968 ከመቅደላ የዘረፈችዉ "የጦር ጋሻ" ዛሬ ሐሙስ ለአለም አቀፍ ጨረታ መቅረብን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ጨረታዉ ተሰርዞ ወደ ትዉልድ ሀገሩ እንዲመለስ ደብዳቤ ፅፏል።እ.ኤ.አ በ 1868 በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተዘረፈው የኢትዮጵያ ጋሻ ሐሙስ በኒዉካስል ታይን ላይ ለአለም አቀፍ ለጨረታ ክፍት እንደሚደረግ ካፒታል ዘግቦ ነበር።

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዛሬ በሰጠዉ በመግለጫው የጨረታ ቤቱን እና የጋሻው ባለቤት ሽያጩን ለመሰረዝ እና "ወደ አገሩ ለመመለስ ድርድር ለመጀመር የወሰዱትን ጥበብ የተሞላበት ውሳኔ" በደስታ እንደሚቀበለዉ ገልጿል።

በቱሪዝም ሚኒስቴር ስር የሚንቀሳቀሰው ባለስልጣኑ ይህ ውድ ሀብት ወደ ትውልድ አገሩና ወደ ህጋዊ ባለቤቶቹ፣ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የሚመለስበትን ውጤት ለማስገኘት ጥረቴን እቀጥላለሁ ብሏል።

በኒውካስል ታይን የሚገኘው አንደርሰን እና ጋርላንድ የጨረታ ቤት ጋሻው ዛሬ የካቲት 21፤2016 ይካሄድ በነበረው “ጨርታ ዝርዝር ዉስጥ የጦር ጋሻዉን አካቷል” ለዚህም ለጋሻዉ ግምታዊ ዋጋዉ ከ1,000 እስከ 1,500 ዶላር አካባቢ መቀመጡ ታዉቋል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAseffa