Get Mystery Box with random crypto!

በሞተር ብስክሌት ላይ እስከ ሰኞ ገደብ ተጣለ በአዲስ አበባ ከነገ አርብ የካቲት 22/2016 ዓ. | YeneTube

በሞተር ብስክሌት ላይ እስከ ሰኞ ገደብ ተጣለ

በአዲስ አበባ ከነገ አርብ የካቲት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ እስከ ሰኞ የካቲት 25/2016 ዓ.ም እስከ ጠዋት 12:00 ሰአት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ፍጹም  የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

ቢሮው ክልከላው ለምን እንደተጣለ በግልፅ ያሳወቀው ነገር የለም።

ክልከላው የፀጥታ እና የትራፊክ ቁጥጥር የሚሰሩ አካላትን አያካትትም ተብሏል።

የሞተር ብስክሌት ባለንብረቶች ሆኑ አሽከርካሪዎች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው አሳስቦ ይህን መልእክት በሚተላለፉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲል አስጠንቅቋል።

ባለፈው ከአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ ጋር በተያያዘ ለቀናት የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎባቸው እንደነበር ይታወሳል።

@Yenetube @Fikerassefa