Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአደጋ ስራ ላይ ህይወታቸዉን ላጡ ሰራተኞቹ እዉቅና | YeneTube

የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአደጋ ስራ ላይ ህይወታቸዉን ላጡ ሰራተኞቹ እዉቅና ሰጠ!

የአዲስአበባ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአደጋ መከላከል ወቅት አደጋ አጋጥሟቸዉ ህይወታቸዉን ላጡ የቀድሞ ሰራተኞቹ እዉቅና ሰጥቷል።

በዛሬዉ እለት በተካሄደዉ ስነስርዓት ከ 1981 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰቱ አደጋዎች ህይወታቸዉን ላጡ የቀድሞ ሰራተኞች ቤተሰቦች የሜዳሊያ ፣ የእዉቅና ሰርተፍኬት እና የ 20 ሺህ ብር ቦንድ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ኮሚሽኑ ለቀድሞ 8 ሰራተኞቹ ነዉ እዉቅናዉን በዛሬው እለት የሰጠዉ። ሰራተኞቹ በእሳት አደጋ ፣ ከወንዝ ሰዎችን ለማዉጣት ባደረጉት ጥረት በተበከለ ዉሃ በመመረዛቸዉ ፣ በመኪና አደጋ እና በአደጋ መከላከል ወቅት በተለያዩ ጉዳቶች ህይወታቸዉን ያጡ ናቸዉ። ኮሚሽኑ ለሰራተኞች ቤተሰቦች እዉቅናዉን ሰጥቷል።

በነገዉ እለትም በአለማቀፍ ደረጃ ለ 24ኛ በአዲስአበባ ደረጃ ለ 2ኛ ግዚ በሚያከብረዉ የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ቀንን "የሚጠብቁንን እናክብር በሚል ቃል" ነዉ።

[ዳጉ ጆርናል]
@YeneTube @FikerAssefa