Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኢትዮጵያው 'ቦርከና' ጋዜጣ 'በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ውጥረት | YeneTube

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር የኢትዮጵያው "ቦርከና" ጋዜጣ "በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ውጥረት እየተፈጠረ ይኾን?" በማለት ያተመውን ሃተታ "በሐሰትና ግምታዊ ድምዳሜ የተሞላ" በማለት ተችቷል።

ሚንስቴሩ በመግለጫው፣ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ በቅርቡ ስለ ሱዳኑ ግጭት በሰጡት ቃለ ምልልስ ኢትዮጵያን ጎሸም ያደረጉ አስመስሎ አቅርቧል በማለት ወቅሷል። ጋዜጣው "ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሥመራ መሄድ ፈልገው፣ የኤርትራ መንግሥት ሁለት ጊዜ ፍቃድ ነፍጓቸዋል" እንዲኹም "ኤርትራ ለአማራ ፋኖዎች ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠቷ የዐቢይ ካድሬዎች ኢሳያስን እየተቹ ነው" በማለት የጻፋቸው ነገሮች "ሐሰት" መኾናቸውንም ሚንስቴሩ ገልጧል። ሚንስቴሩ፣ ኤርትራ አዲስ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረገች እንደኾነ ጋዜጣው ያሰራጨውን ወሬም "የተሳሳተ" በማለት አስተባብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa