Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኬንያ የውጭ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተነገረ የ | YeneTube

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኬንያ የውጭ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተነገረ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ኬንያ አቀኑ። የ77 አመቱ ፕሬዝዳንት በዲፕሎማሲያዊ ሁኔታ በእንዲህ ዓይነቱ የስራ ጉብኝት  ላይ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ብዙም አይስተዋል።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት ፕሬዝዳንቱ ከኬንያ አቻቸው ዊልያም ሩቶ ጋር በኬንያ ርዕሰ መዲና ናይሮቢ እንደሚወያዩ ይጠበቃል ማለታቸውን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።

ባለፈው ወር የኤርትራ እና የኬንያ መሪዎች የቀጠናውን ሰላም እና ደህንነት ለማስጠበቅ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ይታወሳል። የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኤርትራ ፕሬዝዳንት ኢሳይስ የቀይ ምንጣፍ አቀባበል ሲደረግ የሚያሳይ ምስልን በትዊተር ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።

Via :- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa