Get Mystery Box with random crypto!

የኤርትራ ወታደሮች ከአድዋ እና አክሱም ከተሞች እየወጡ መሆኑን የሁለቱ ከተሞች ነዋሪዎች ነግረውኛል | YeneTube

የኤርትራ ወታደሮች ከአድዋ እና አክሱም ከተሞች እየወጡ መሆኑን የሁለቱ ከተሞች ነዋሪዎች ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ነዋሪዎቹ ዛሬ ጣት፣ የኤርትራ ወታደሮችንና ወታደራዊ መሳሪያዎችን የጫኑ በርካታ አውቶብሶችና አይሱዙዎች ከሁለቱ ከተሞች ሲወጡ ስለማየታቸው መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የዓይን ምስክሮቹ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአድዋ ከተማ ዳርቻ ሠፍሮ ማየታቸውንም እንደገለጹ ዜና ምንጩ አመልክቷል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ ፌደራል መንግሥቱ፣ ሕወሃት ወይም የኤርትራ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ያሉት ነገር የለም።

Photo: File
@YeneTube @FikerAssefa