Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ! በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸ | YeneTube

በአዲስ አበባ የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ተደረገ!

በጥር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ ግምት ውስጥ በማስገባት የትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የጥር ወር ነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የአገልግሎት መስጫ የዋጋ ታሪፍን ማሻሻያ ጥናት መደረጉ ይታወሳል፡፡

አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

በዚህም መሰረት ለሚኒባስ የታክስ ተሸከርካሪዎች፦

የጉዞ ርቀት በኪሎ ሜትር እስከ 2 ነጥብ 5 ርቀት በነባር የክፍያ ታሪፍ 3 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በተስተካከለው ታሪፍ 4 ብር፣

ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 6 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር ሆኗል፡፡

በተጨማሪም ከ5 ነጥብ 1 እስከ 7 ነጥብ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 10 ብር የነበረው ታሪፍ በተመሳሳይ 10 ብር ሆኖ እንዲቀጥል ተወስኗል፡፡

=> የሃይገርና የቅጥቅጥ ታክሲዎች የታሪፍ ማሻሻያ በተመለከተም፦

እስከ 8 ኪሎ ሜትር 5 ብር የነበረው ታሪፍ በነበረው እንዲቀጥል፣

ከ8 ነጥብ 1 እስከ 12 ኪሎ ሜትር 7 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ክፍያ በአዲሱ ማሻሻያ 8 ብር፣

ከ12 ነጥብ 1 እስከ 16 ኪሎ ሜትር 9ብር ከ50 ሳንቲም የነበረው ታሪፍ ከነገ ጀምሮ በሚተገበረው ማሻሻያ 10 ብር እንዲሆን ተደርጓል፡፡

በተጨማሪም ከ16 ነጥብ 1 እስከ 20 ኪሎ ሜትር 12 ብር የነበረው ክፍያ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 13 ብር፣

ከ20 ነጥብ 1 እስከ 24 ኪሎ ሜትር 14 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 15 ብር፣

ከ24 ነጥብ 1 እስከ 28 ኪሎ ሜትር 17 ብር የነበረው 18 ብር እንዲሆን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ከ2 ነጥብ 6 እስከ 5ኪሎ ሜትር ርቀት 6 ብር ከ50 ሣንቲም የነበረው ታሪፍ በአዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ 7 ብር እንዲሆን መወሰኑን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa