Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዓለማቀፍ ዋጋ ወደ 110 ዶላር እንዳሻቀበ ዓለማቀፍ ዜና ወኪሎች | YeneTube

ዛሬ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዓለማቀፍ ዋጋ ወደ 110 ዶላር እንዳሻቀበ ዓለማቀፍ ዜና ወኪሎች ዘግበዋል።

አንድ በርሜል ነዳጅ በዚህ ዋጋ ሲሸጥ ከ7 ዓመታት ወዲህ የመጀመሪያው ሲሆን፣ ዋጋው የጨመረው በሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ሳቢያ ነው። ጦርነቱ ከነዳጅ ዋጋ አልፎ ለመላው ዓለም ከፍተኛ የደኅንነት ስጋት ሊደቅን እንደሚችል ታዛቢዎች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ።

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ዛሬ ባደረጉት ንግግር፣ ምዕራባዊያን ኃያላን ሀገራት ሩሲያ በዩክሬን ላይ በምትወስደው ወታደራዊ ጥቃት ጣልቃ ገብተው ሦስተኛው ዓለም ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጦርነቱ በጅምላ ጨራሹ ኒውክሊየር ቦምብ የታገዘ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል።

ላቭሮቭ አያይዘውም፣ አሜሪካ በቀድሞዎቹ የሶቪየት ኅብረት ሪፐብሊኮች ወታደራዊ ጦር ሠፈር ለማቋቋም እንዳታስብ አሳስበዋል።

@Yenetube @Fikerassefa