Get Mystery Box with random crypto!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድናት ልማት ላይ የተሰማሩ አካላት ከፀጥታ ስጋት ተላቀው ሥራቸውን እ | YeneTube

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድናት ልማት ላይ የተሰማሩ አካላት ከፀጥታ ስጋት ተላቀው ሥራቸውን እንዲሠሩ ሁኔታዎች እየተመቻቹ መሆኑን የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ዑማ አስታወቁ።

በዛሬው ዕለት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኩሩምክ ወረዳ ተገኝተው ባህላዊ የማዕድን ኩባንያዎች ያሉበትን ደረጃ መመልከታቸውን አስታውቀዋል።

በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰን እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።ኩባንያዎቹ ለሥራቸው እንቅፋት የሆኑባቸው ጉዳዮች መፍትሔ እያገኙ ነው ያሉት ኢንጂነር ታከለ ዑማ፣ በቀጣይም በሙሉ አቅማቸው ወደ ሥራ እንዲገቡ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጠላትን ከፊት እየጠረገ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ለመልሶ ግንባታው መደላድል የመፍጠር ተልዕኮውን በጀግንነት እያሳካ ነውም ብለዋል።“የመከላከያ ሠራዊታችን እና ሌሎች የፀጥታ አካላት እያሳዩ ላለው ጀግንነት ክብር ይገባቸዋል” ሲሉም ገልጸዋል።

@YeneTube @FikerAssefa