Get Mystery Box with random crypto!

በያዝነው ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት በመጠኑ ቅናሽ አሳይቷል፡፡ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት | YeneTube

በያዝነው ወር የምግብ ዋጋ ግሽበት በመጠኑ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ የህዳር ወር 2014 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ33.0 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡የምግብ ዋጋ ግሽበት የሕዳር ወር 2014 ዓ.ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ38.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በያዝነው ወር በእህሎች፣ በአትክልትና ጥራጥሬ ዋጋ በአብዛኛው ቅናሽ አሳይቷል፤ ሩዝ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ማሽላ፣ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንቡራና ምሥር የዋጋ ቅናሽ አሳይተዋል፡፡ በተጨማሪም ሥጋ፣ ወተት፣ አይብና ዕንቁላል፣ ቅመማ ቅመም (በዋናነት ጨውና በርበሬ) ቅናሽ አሳይተዋል፡፡የምግብ ዘይትና ቅቤ በመጠኑ ቅናሽ ያሳዩ ሲሆን በአንፃሩ ቡናና ለስለሳ መጠጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa