Get Mystery Box with random crypto!

🌷💘🌹ፍቅርና💞ጥበብ💖💘

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeneta27 — 🌷💘🌹ፍቅርና💞ጥበብ💖💘
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeneta27 — 🌷💘🌹ፍቅርና💞ጥበብ💖💘
የሰርጥ አድራሻ: @yeneta27
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.31K
የሰርጥ መግለጫ

በፍቅርና❤ ጥበብ 📒
የምለቃቸው የጥበብ ስራዎች እነሆ
📑የግል ግጥሞችና የሌሎች ሰዎች ግጥሞች
❤የፍቅር ታሪክና ጥቅስ
🎵ሙዚቃ
🎦አስቂች vidio&pic
📙መፃሐፍትን #በPdfና_በvoice
🎭ወጎች
🇪🇹ሐገራዊ መረጃዎች
👉 join @yeneta27
👉F.comment @yenefikr & @abaynesh_bot
አድሚኖች👇
@fiyuy

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-06-05 22:46:14 #ይቅርታ_ልበልሽ

አጣሁ ብዙ ነገር ስለይሽ የዛኔ
አሁን ነው የታወቀኝ ሲበዛ ሀዘኔ
እንባዬ ይወርዳል ከደጅሽ ለመቆም
ይቅር ልበልና ልውደቅ ከፍቅር አለም

ከእጄ እያለሽ ጥዬ ብቆጥር እንደ መዳብ
ዛሬ ከኔ ባትሆኝ ቆጨኝ ከሰው ሆነሽ ማሰብ
ይቅርታ ልበልሽ ውሃ ሆኜ ላፅዳሽ
ቆጭቶኛል ዛሬ ስትርቂኝ ላላይሽ

መልካም ሴት ሲፈጠር አንደኛ ብትሆኝም
በኔ ስህተት ድሮ ክብርሽን ብታጪም
አሁን ማሪኝ ፍቅር ይቅርታ ልበልሽ
ይታጠብ ጥፋቴ በይቅር ባይ ልብሽ

ሰው ሲመስለው ስራው ትክክል ነኝ ይላል
እኔም መስሎኝ እንጂ የሰራሁት ስራ ቅያሜን አጭሯል
ቢገባኝም ረፍዶ አልቀረሁም ደጅሽ
ማሪኝ አጨክኚ ተንበርክኬ ከእግርሽ ዛሬም ልለምኘሽ

ዝም አትበይ ተቆጪ ደረቴንም ምቺ
ጥፋቴ ቢሰረዝ ይቅርታዬ ባንቺ
ስደት ወቷል ልቤ አንድ ነገር አሞት
ይቅርታሽን ሽቶ ለመዳን ከፀፀት

ወዴ......
ይቅር አትይኝም በቃ እኮ አመመኝ
ጥፋቴ ገብቶኛል እንታረቅ በይኝ
ናፈቀኝ ጠረንሽ ልረሳው አልቻልኩም
ካንቺ ፍቅር አለም መንጎድ አላቆምኩም

ታሞ ያልዳነ ሰው ሞቱን ይመርጥና
ተስፋ ቆርጦ ሲኖር በሱ ይማርና
ተመስገን ይለዋል አይኑን ያቀናና
እኔም ከታመመው በምን እሻላለው
ከእግሮችሽ በታች ይቅር ልል ወድቃለው
ተነስ እስክትይኝ እጠብቅሻለው
ይቅርታ አርገሺልኝ ላቅፍሽ ቸኩያለው
#ይቅርታ_ልበልሽ ማሪኝ አጥፍቻለው

ሲሳይ አሰፋ (የኔታ)
አዳማ ኢትዮጵያ
25/09/13
7.8K views꧁☆$🇸 🇮 🇸 🇦 🇾 $☆꧂ ꧁☆$🇾 🇪 🇳 🇪 🇹 🇦 27 $☆꧂, 19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-01 23:18:14
መልካም በዓል ይሁንላቹ
7.9K views꧁☆$🇸 🇮 🇸 🇦 🇾 $☆꧂ ꧁☆$🇾 🇪 🇳 🇪 🇹 🇦 27 $☆꧂, 20:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-15 13:22:48
በቅርብ ቀን ይጠብቁ ውድ የፍቅርና ጥበብ ቤተሰብ አባላት #የሐሳቤ_ስዕልንም ማንበብ ጀምሬያለው ስጨርሰው እጀምረዋለው ያኔ ቤታችንን እናደምቀዋለን።በመሐል አንዳንድ ግጥሞቼን ይዤ ብቅ እላለው።በጉጉት እየጠበቃቹ ያላችሁ እንዳላቹ አውቃለው።ለሱ እክሳለው።
8.2K views꧁☆$🇸 🇮 🇸 🇦 🇾 $☆꧂ ꧁☆$🇾 🇪 🇳 🇪 🇹 🇦 27 $☆꧂, 10:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-11 00:33:45
7.5K views꧁☆$🇸 🇮 🇸 🇦 🇾 $☆꧂ ꧁☆$🇾 🇪 🇳 🇪 🇹 🇦 27 $☆꧂, 21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-07 21:54:37
7.5K views꧁☆$🇸 🇮 🇸 🇦 🇾 $☆꧂ ꧁☆$🇾 🇪 🇳 🇪 🇹 🇦 27 $☆꧂, 18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-05 11:34:23
7.4K views꧁☆$🇸 🇮 🇸 🇦 🇾 $☆꧂ ꧁☆$🇾 🇪 🇳 🇪 🇹 🇦 27 $☆꧂, 08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-01 15:42:18 ልክ ነው
"የሰው ልጅ እኔ እንደማስበው ያስባል አትበል
እኔ ብቻ ትክክል ነኝ አትበል አስተውል ሁሉም ሰው በራሱ ሚዛናዊ አስተሳሰብ ልክ ነው ።"
ሁሉም ሰው በራሱ ልክ ነው
@yeneta27
8.5K viewsŎńĩ.........ťÿpĩŋğ, edited  12:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-01 15:39:24 ፍቅሮችዬ
ወዳጄ ሆይ
ጓደኝነት ከደም ትስስር በላይ ሀይል አለው ። በጓደኝነት ውስጥ የነፃነት ገደብ የፍራቻ ወደብ የለም። የመሰለክን ሀሳብ የመግለፅ ስልጣን አለህ። መልካም ጓደኛ መጥፎ ጎንህን ሳይሸሽግ ይነግርሃል በጥሩ ጎንህ ላይም ያበረታታሃል። በጥሩ የጓደኝነት መረብ ላይ ምቀኝነት፣ቅናት፣ሀሜት ብሎ ነገር የለም። አንተ አቅም ባይኖርህና የጓደኛህ ችግር በጥቅም መካፈል ባትችል በሀሳብ ከጎኑ ሆነህ አብሮነትህን ታሳያለህ። በጥሩ ጓደኝነት መስፈርት በገንዘብ መረዳዳት የጥሩነት ጥግ አይደለም ይልቁንስ ጓደኛህ ሰው ቢሸሸው፣አደጋ ቢደርስበት፣በህመም አልጋ ላይ ቢውል ከማንም በፊት አጠገቡ መገኘትህ ነው የጓደኝነት ጥግ
ቸር ዋሉልኝ
7.0K viewsŎńĩ.........ťÿpĩŋğ, 12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-01 15:35:50 ያጠፋህ መስሎዋቸው እኮ ነው ፤ሰድበውክ አንቋሸውክ ፤አትረባም አትደርስም ፤አትችልም ምክንያቱም አታውቅም ብለውክ ወድቀህ ሲያዩ ስቀው ተሳልቀውብክ ፤እንደ ትንኝ ሲረግጡህ ይበልጡን ስትወድቅ ፤እንደሞተ ትተውክ ሲሄዱ .......

የደማው ልብክን ተሸክመክ ተነስ በቀስታም ተራመድ ያንተ ተስፋ በፈጣሪ ነውና በጉዞክ አታመንታ የተገፋከው ስለእውነት ነውና አትሽሽ በስቃይክ ተደሰት ባለማወቃቸው ሳቅባቸው በዝምታክ አሸንፋቸው ባንተ ዝምታ ፈጣሪክ ይናገራልና ..........ግን ሽንፈታቸውን ለመደበቅ አንተን መኮርኮም ይጀምራሉ ።ኮርኩመውክ፣ኮርኩመውክ ፣ኮርኩመውክ ፣ከርክመውክ፣ከርክመውክ፣ከርክመውክ፣ከርክመውክ ትልቅ ሰው ያደርጉሀል
ብቻ ከፈጣሪ ጋራ ሁን
6.7K viewsŎńĩ.........ťÿpĩŋğ, 12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-01 14:45:15
ፀፀቴ

ቀልደኝነቴ በዝቶ ቁምነገሩን እንዳላስተውል አደረገኝ ሳቄ በዛና ሰዎች የሚስቁ እየመሰለኝ ነገሩን ዘለልኩት

እኔ ሳይገባኝ ጥልቅ ሆነህ አፍቅረኸኝ ነበር...... እኔ ሳልረዳህ ብዙ ታመህ ነበር በግልጽ ነግረኸኝ አለመጠርጠሬ እንጭጩ ጭንቅላቴን ጠላሁት..... ሁሌም የሚሆነውን ነበር የምትነግረኝ እኔ ግን ሳይገባኝ ሳቅኩበት

እኔ ስነቃ ግን ሁሉም አለፈ....አንድ ነገር ብቻ ተረዳሁ በልቤ ስፈልግህ ያጣሁክ በጭንቅላቴ የአገኘሁክ ፀፀቴ ነህ።

ኦኒ

@yeneta27
6.7K viewsŎńĩ.........ťÿpĩŋğ, 11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ