Get Mystery Box with random crypto!

#ጽብረቃ ' ወላጆቼ 55 ዓመታትን በትዳር ኖረዋል። አንድ ቀን ጠዋት ላይ እማዬ ለአባ ቁርስ ልት | 💖የኔ ፍቅር 😘

#ጽብረቃ

" ወላጆቼ 55 ዓመታትን በትዳር ኖረዋል። አንድ ቀን ጠዋት ላይ እማዬ ለአባ ቁርስ ልትሰራ ወደ ምድር ቤት እየወረደች ሳለ የልብ ድካም ጣላት። አባዬም እማን አፋፍሶ መኪና ውስጥ አስገባት። መኪናው የቻለችውን ያህል እያከነፈና የትራፊክ ህግን ሳያከብር ወደ ሆስፒታል አደረሳት። ግን ምን ዋጋ አለው..ሆስፒታል ሲደርሱ እማ ለዘላለሙ ተለይታን ነበር

በቀብር ስርዓት ወቅት አባ ዝም ጭጭ ብሎ ትውስታውን ያጣ ይመስል ነበር። የንባ ከረጢቱ ደሮቆበት ዋለ። በዛን ቀን ምሽት ሁሉም ልጆቹ ከሱ ጋር አልተለየንም ነበር። ሀዘን ባጠላበት ስሜት ውስጥ እንዳለን አባቴ አንዱን የሃይማኖት ትምህርት ( theologian) ያጠናውን ወንድሜን 'አሁን እናታችሁ የት ልትሆን ትችላለች?' ሲል ጠየቀው።ወንድሜም ከህይወት በኋላ ስላለው ሁኔታ እየተነተነ በማስረዳት የናታችን ግምታዊ አድራሻ ተናገረ።

አባም በትኩረት ሲያዳምጥ ቆይቶ ድንገት ወደ መካነ መቃብር ውሰዱኝ አለ። "አባ ከምሽቱ 5 ሰዓት ሆኗል መካነ-መቃብር መሄድ አንችልም" ብንለውም "ልጆቼ አትከራከሩኝ፣ የ55ዓመት የትዳር አጋሩን ያጣን ሰው አትከራከሩ "ሲል ልብ በሚሰብር ድምፅ ተናገረ። እኛም መከራከራችንን አቆምን።

ወደ መካነ-መቃብሩ ሄደን የማታ ጥበቃውን አስፈቅደን ወደማየ መቃብር ቀረብን። አባዬ መልካም ምኞቱንና ፀሎቱን ለእማ ካደረሰ በኋላ ወደኛ ወደ ልጆቹ ዞሮ መናገር ጀመረ።

"55 ዐመታት ሆነ...ታውቃላችሁ? ማንም ስለ እውነተኛ ፍቅር ካንዲት ሴት ጋር 55ዓመት ሳይኖር ማውራት የለበትም።"

ትንሽ አቋርጦ ፊቱን ጠራረገና "እሷና እኔ፣ እኛ በብዙ ውጣ ውረዶች ውስጥ አብረን ነበርን....ብዙ ከፍታና ዝቅታን አይተናል....ልጆች ስንባረክ አብረን ተደስተናል፣ ልጅ የማሳደግ ኃላፊነትን አስተምሮ ወግ ማድረስን ደስታ በጋራ አጣጥመናል...ብዙ ህመሞችን በጋራ አስተናግደናል፣ ብዙ ስህተቶችንም ይቅር ተባብለናል። ልጆቼ አሁን ሁሉም አልፏል እኔም ደስ ብሎኛል....ለምን ደስ እንዳለኝ ታውቃላችሁ??

ምክንያቱም እሷ ቀድማኝ ስላለፈች።

እኔን ስትቀብር የሚገጥማትን ሃዘን፣ የብቸኝነት ህመም፣ የ55 ዓመት የትዳር አጋር ማጣት የሚፈጥረውን ባዶነት ሳታይ ቀድማኝ ስላለፈች ደስ ብሎኛል። በጣም ስለማፈቅራት ስቃይ እንዲገጥማት አልፈልግማ.......

አባዬ ተናግሮ ሲጨርስ እኔና ወንድሞቼ ተንሰቅስቀን አለቀስን። የአባዬ ሃዘን ውስጣችን ዘልቆ ገባ።

ከዛም ወደ ቤት ተመለስን....

በዛን ቀን ምሽት የዕውነተኛ ፍቅር ምንነትን ተረዳሁ..እውነተኛ ፍቅር ከሮማንቲዝም የራቀ፣ ወይም ፆታዊ የተራክቦ ርካታ ላይ ያልተጣበቀ...ይልቁንም በጋራ መስራት፣ በጋራ መቆም፣ በጋራ መቻቻልና ይቅር መባባል...ደስታና ሃዘኑን በጋራ ማጣጣም መሆኑን ተገነዘብኩ....

(ያልታወቀ ፀሃፊ ፃፈው፣ እኔ ደግሞ FB ላይ አግኝቼ ወደ አማርኛ መለስኩት። ታሪኩን ትወዱታላችሁ ብዬ ጋበዝኳችሁ)
____
ሠላማችሁ ይብዛልኝ

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir