Get Mystery Box with random crypto!

'ለምንድነው የምትፆመው?' ይሄን ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች አሉ፤ይህን ጥያቄ ክርስትያን ነኝ ከሚል ሰ | የነፍሴ ጥያቄዎች

"ለምንድነው የምትፆመው?"

ይሄን ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች አሉ፤ይህን ጥያቄ ክርስትያን ነኝ ከሚል ሰው መስማት ያሳዝናል።

ለምንድነው ምፆመው? ሞት እየነገሰ ሰው እንዴት ይህን ጥያቄ የመጠየቅን ድፍረት ሊያገኝ ይችላል? ወደ ግራ እና ወደቀኝ ዞር ዞር ብለን እንመልከት እስኪ ምን ይታይሀል? ምንስ ይታይሻል? በሽታ፣ሱሰኝነት፣ኑፋቄ...ወደልጆቻችሁ ክፍል ብትገቡ ምን ታያላቹ? ብትቀርቡዋቸው አብራቹ ብትቀመጡ እና ውስጣቸውን ብትረዱ ያሉበትን ሁኔታ የሚያጨሱትን የሚያዩትን ብትመለከቱ ደምስሮቻቸው ላይ ምን ሰክተው በምን እንደሚጦዙ ጓደኞቻቸው እነማን እንደሆኑ ብታውቁ፤TV ከፍታቹ ብትመለከቱ ራሳችሁን ብታደምጡ የምትሰሙት ጦርነት የምታዩት ሴሰኝነት የምትረግጡት መሬት በደም የራሰ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንደሆነ ይገባቹዋል።

ከዛ ለምን መፆም እንዳለብን ይገለጥላቹዋል ለምን እንደምንፆም ይገባቹዋል። ተስፋ ላለመቁረጥ ስንል እንፆማለን፤በንፋስ የሚሰበር ሸንበቆ ላለመሆን ስንል እንፆማለን።

አለማዊ ለስላሳ ልብስን አንፈልግ!
በቁም ሬሳዎች የተሞሉ ትላልቅ ቤቶችን አንፈልግ!
ሰይጣናዊ ዝሙታዊ ጭፈራዎችን አንፈልግ!
ወደ መጥምቁ ዮሀንስ የንስሀ ጥሪ እንመለስ!
ሊመጣ ያለውን በመላእክት ታጅቦ የሚመጣውን ንጉሱን ለመቀበል እንዘጋጅ!
የምንፆመውም ለዛ ነው!
ከመንግስቱ እንዳንጎድል ነው በንስሀ የምንኖረው!
መስቀሉን እና ስቃዩን እናስብ ለአለም ችግር የኛ ፆም እና ስግደት ፀሎታችን መፍትሄ አለው ለዛም እንፆማለን!

አንድ አባት የመለሱትን መልስ ከራሴ ጋር አዋህጄ ፃፍኩላቹ ፆማችን መፍትሄ አለው!
share join share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch