Get Mystery Box with random crypto!

...ላ አባትህ ነኝ ብለህ ስትመጣ መቀበሌ አንሶህ ልረድህ ትለኛለህ እንዴ!!!' አላለውም ነበር። | የነቢያት ታሪክ እና እስላማዊ ትምህርቶች

...ላ አባትህ ነኝ ብለህ
ስትመጣ መቀበሌ አንሶህ ልረድህ ትለኛለህ እንዴ!!!" አላለውም ነበር።
ነገር ግን በእናቱ መልካም ተርቢያ ያደግው የመልካም ስነምግ ባር ባለቤት
የሆነው ኢስማዒል፦"አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ፈፅም እኔንም ታጋሽ ሆኜ
ታገኘኛለህ" ነበር መልሱ።
አሁን ኢብራሂም ልጁን ሊያርድ ዝግጅቱን ጀምሯል።የኢስማዒልን እጅ ወደኋላ
አድርጎ ካሰረ በኋላ በጀርባው ካስተኛው አይኑን ሲያይ ሆዱ አይችልም'ና
በሆዱ አስተኝቶ ፊቱን ወደ መሬት በመድፋት የጌታውን ትዕዛዝ ተፈፃሚ
ሊያደርግ ቢለዋውን በልጁ ኢስማዒል አንገት ላይ ሲያሳርፍ ከወደ ላይ
በኩል፦"ኢብራሂም ሆይ !!! ህልሙን እውን አድርገሀል እኛም እንደዚህ
መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን" የሚል ድምፅ መጣ።
ኢብራሂምም ቀና ሲል ከሰማይ አንድ መልዐክ ለኢስማዒል ቤዛ ይሆን ዘንድ
ሙኩት ይዞ መጣ'ና፦"ኢስማዒልን ፈትተህ ይሄን እረድ" አለው።
ከዚያም ኢብራሂም ደስታው ወደር አጣ...እየተቻኮለ የልጁን...የአብራኩን
ክፋይ እጆች መፍታት ጀመረ።ከዚያም ከሰማይ የመጣለትን ሙኩት
አረደው።ያን ቀን በማስመልከት ነው እንግዲህ በየዐረፋ በአሉ የእርድ
ስነስርዐት ሙስሊሞች የምንፈፅመው።
ኢብራሂምም ወደ ሀገሩ ተመልሶ ብዙም ሳይቆይ ዳግም ሌላ ትዕዛዝ ከጌታው
በኩል መጣለት፦"ከልጅህ ጋር በመሆን ልጅህ በሚገኝባት ከተማ እኔ
ምመለክበትን ቤት(ካዕባ) ስራ" የሚል ነበር ትዕዛዙ።
ኢብራሂምም ለጌታው ታዛዥ በመሆን ወደ ልጁ ሄዶ ሲያማክረው ልጁም
መርሀባ ይለውና ማቴርያል አሰባስበው ግንባታ ጀመሩ።
ኢብራሂም እላይ ሆኖ ሲመርግ ኢስማዒል ደሞ ከታች ድንጋይ ያቀብለው
ነበር።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ፦"ጌታችን ሆይ! የምንሰራውን ተቀበለን አንተ
ሰሚም አዋቂም ነህ" በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር።
አሁን የታዘዙትን ቤት ሰርተው አጠናቀዋል ኢብራሂምም ከቤቱ ጎን በመቆም፦"
ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም
ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን።
ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ
ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና...
ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡
ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ።
ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለምእመናንም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት
ቀን ማር" በማለት ዱዐ አደረገ።
ይህን ትልቅ ቤትም ገንብተው ካጠናቀቁ በኋላ አላህም ኢብራሂምን፦"ሰዎች
ከየሀገሩ በመምጣት ቤቴን ይጎብኙ ዘንድ ተጣራ" አለው።
ኢብራሂምም፦"ጌታዬ እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝ ድምፄ እኮ አይደርስም"አለው።
አላህም፦"አንተ ተጣራ ማድረስ የኔ ስራ ነው" አለው።
ኢብራሂምም ትልቅ ተራራ ላይ በመውጣት ተጣራ።ያን ግዜ ከየሀገሩ ያሉ
ህዝቦች ጥሪውን በመቀበል መካ መጥተው ሞሉ። ኢብራሂምም የሀጅን
ስነስርዐት ለሁሉም አስተማራቸው።
ከዚያ በኋላ የኢብራሂም ሚስት ሳራ በከንዐን ምድር ሀብሩን በምትባል ቦታ
በ127 አመቷ ዱንያን ተሰናበተች።
ከዚያ በኋላ ኢብራሂም ለሳራ ልጅ ኢስሀቅ ሪፍቃ ቢንት በቱኢል የተባለችን
እንስት አጭቶለት አጋባው።
ከዚያም ኢብራሂምም ለራሱ ቀንጡራ የተባለችን ሴት በማግባት
1፦ዙምራን
2፦የቅሻን
3፦ማዳን
4፦መድየን
5፦ሺያቅ
6፦ሸውህ...የተባሉ ልጆችን ወለዱ።
በመጨረሻም በ200 አመቱ #ኢብራሂም ዱንያን ተሰናበት....ዐለይሂ ሰላቱ
ወሰላም
_____________________________________
የኢብራሂምን ዐ ሰ ትረካ ስንዳስስ የኢስማዒልን እና የኢስሀቅን (ዐሰ) ትንሽ
ነካ ነካ ማድረጋችን ይታወሳል።
ስለዚህ በቀጣይ በአላህ ፍቃድ የሁለቱንም ትረካዎች በማያያዝ የምናቀርብላችሁ
ይሆናል።
ምንጮቻችን፦
ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ / ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
ﺻﺤﻴﺢ ﻣﺴﻠﻢ
ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ

ነብዩሏህ #ኢስማኢል እና #ኢስሀቅ ታሪክ ኢንሽአላህ
ይ......ቀ.....ጥ.....ላ......ል፡፡
ሌሎች የነብያት፣ ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ
እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ
አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።
@yenebiyattaric
@yenebiyattaric