Get Mystery Box with random crypto!

የነቢያት ታሪክ እና እስላማዊ ትምህርቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ yenebiyattaric — የነቢያት ታሪክ እና እስላማዊ ትምህርቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ yenebiyattaric — የነቢያት ታሪክ እና እስላማዊ ትምህርቶች
የሰርጥ አድራሻ: @yenebiyattaric
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.89K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2021-12-27 20:42:41 #ነብዩሏህ_ዩሱፍ(ዐለይሂ_ሰላም) ታሪክ

ክፍል

ያዕቁብ ልጆቹን ሚስቶቹን እና አገልጋዮቹን ይዞ ከንዓን ምድር ላይ ኑሯቸውን
ጀምረዋል።ያዕቁብ ልጆቹን ሁሉ እላፊ በመውደዱ የሚታወቅ አባት ቢሆንም
ለየቲሞቹ #ለዩሱፍ እና #ለቢንያሚን ያለው ቦታ ልዩ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን #ዩሱፍ በሌሊት ተነስቶ ለአባባቱ ያየውን ድንቅ ህልም
እንዲህ ሲል ይነግረዋል፦" አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና
ጨረቃንም (በሕልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው"
አባትየውም፦"ልጄ ሆይ! ሕልምህን ለወንድሞችህ አታውራ፡፡ ላንተ ተንኮልን
ይሰሩብሃልና፡፡ ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና..... እንደዚሁም
(እንዳየኸው) ጌታህ ይመርጥሃል፡፡ ከንግግሮችም ፍች ያስተምርሃል፡፡
ጸጋውንም ከአሁን በፊት በሁለቱ አባቶችህ በኢብራሂምና በኢስሐቅ ላይ
እንዳሟላት በአንተ ላይና በያዕቆብ ዘሮችም ላይ ይሞላታል፡፡ ጌታህ ዐዋቂ
ጥበበኛ ነውና" ብሎ አብስሮት ህልሙንም ለማንም እንዳይናገር
አስጠነቀቀው።
አባትየው ያዕቁብ የዩሱፍን ህልም ከሰሙ በኋላ ለዩስፍ ያላቸው ፍቅር ወደ
አክብሮት እና ለሱ ወደ መተናነስ ያደላም ጀመር።ይህ ግን ለዩሱፍ ለአባቱ
ልጆች የእግር እሳት ሆኖባቸው ቅናት እረፍት ነስቷቸዋል።
ከእለታት አንድ ቀን የዩሱፍ የአባት ልጆች በዩሱፍ እና በአባቱ መካከል ያለውን
ፍቅር እንዴት በአጭሩ ማኮላሸት እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ
ተሰበሰቡ።ብዙ ሀሳቦችን አንስተው በመጨረሻም ዩሱፍን በአንድ ውሀው
ጨዋማ በሆነ ስምጥ ጉድጓድ ውስጥ ሊጨምሩት ወሰኑ።
ማታ ላይ አባታቸው ዘንድ በመሄድም፦" አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ላይ ለምን
አታምነንም እኛም ለእርሱ በእርግጥ አዛኞች ነን።
ነገ ከእኛ ጋር ላከውና ይደሰት፤ ይጫወትም፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን"
በማለት ዩሱፍ ከነሱ ጋር እንዲሄድ አባታቸው ያዕቁብን ተማፀኑት።
ያዕቁብም፦" እኔ እርሱን (ዩሱፍን) ይዛችሁ መሄዳችሁ በእርግጥ ያሳዝነኛል፡፡
እናንተም ከእርሱ ዘንጊዎች ስትሆኑ ተኩላ ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ" በማለት
መለሰላቸው።
ከዚህም ከዚያም ብለው አባታቸውን ካሳመኑት በኋላ የልባቸውን ሊፈፅሙ
ዩሱፍን ወዳጅ መስለው አቅፈው ወሰዱት።ያሰቡበትም ጉድጓድ ውስጥም
እየለመናቸው እጅ እግሩን አሳስረው ቀሚሱን አውልቀው ወረወሩት።
ማታ ሲሆንም የሁዳ ባመጣው ሀሳብ መሰረት ያወለቁትን የዩሱፍን ቀሚስ አንድ
ፍየል አርደው ቀሚሱን በፍየሏ ደም ለወሱት።በመጨረሻም ምሽቱ ሲደምቅ
እንስሳቶቹን እየነዱ መንደር ከደረሱ በኋላ የዩሱፍን በደም የተለወሰ ቀሚስ
ይዘው እዬዬዬ....በማለት እያለቀሱ ሰፈሩን ቀወጡት።
ይህን ሲያይ ያዕቁብ እግሩ ተብረከረከ ተንኮለኛ ልጆቹ በውዱ ልጁ ሴራቸውን
ተግባር ላይ እንዳዋሉ ተረዳ።
እሱም፦"ልጄ ምን ሆነ" ሲላቸው...
እነሱም፦" አባታችን ሆይ! እኛ (ለሩጫና ለውርወራ) ልንሽቀዳደም ሄድን፡፡
ዩሱፍንም ዕቃችን ዘንድ ተውነው፡፡ ወዲያውም ተኩላ በላው፡፡ አንተም
እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም" አሉት (እነዚህ ቀልበ ደረቆች)
አባታቸውም፦" አይደለም፤ ነፍሶቻችሁ (ውሸት) ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡
ስለዚህ መልካም ትዕግስት (ማድረግ አለብኝ) በምትሉትም ነገር ላይ
መታገዣው አላህ ብቻ ነው" ብሎ ጉዳዩ ለአላህ የወው።
ዩሱፍም እዚያ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ወደ ግብፅ የሚሄድ ቅፍለት(ተጓዥ
ነጋዴዎች) በዚያ ጉድጓድ ሲያልፉ ውሀ ለመቅዳት ባልዲያቸውን ወደ ውስጥ
ወርውረው ውሀ ለማውጣት ወደ ላይ ሲጎትቱ ቆንጅዬ ልጅ ባልዲው ላይ
ተንጠልጥሎ ወጣ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ውሀውን ሚቀዳው ሰውዬ ልጅ አገኘሁ እያለ ሲጮኽ የዩሱፍ
ወንድሞች ሰምተው መጡ'ና፦"ከኛ ያመለጠ ባሪያ ነው ከፈለጋችሁ ግዙን
እንጂ በነፃ አትወስዱም" በማለት ወንድማቸውን በርካሽ ዋጋ ለነጋዴዎቹ
ሸጡላቸው።
ነጋዴዎቹ ደግሞ ሸቀጣቸውን ከሚገዙባት ግብፅ ከተማ ሲደርሱ ለግብፅ
አስተዳዳሪ በውድ ዋጋ ሸጡለት።የሀገሪቱ አስተዳዳሪም ዩሱፍን ለሚስቱ
በስጦታ ምልኩ አበርክቶላት ልጅ ስለሌላት እንድ ልጇ አድርጋ እንድታየውም
ነገራት።
ሚስቱም እጅጉን ተደሰተች የልጁ ውበትም ከልጅነቱ ጋር አጓጊነቱም ማረካት።
ግዚያት ነጎዱ ቀን ሌሊትን ክረምት በጋን እየተተካኩ ብዙ አመታት
ተቆጠሩ።ዩሱፍም ወጣትነቱ እና የአዕምሮ ብስለቱ ይልቅ ውበቱን
ጨምሮበታል።የአስተዳዳሪው ሚስት ይህን ስታይ ሁኔታዋ እየተቀያየረ
መምጣት ጀመረ።
ከእለታት አንድ ቀንም ለዝሙት እራሷን አዘጋጅታ ክፍሏ አስጠራችው'ና በሩን
ዘጋጋች።ከዚያም፦"ተዘጋጅቼልሀለሁ ናልኝ" ስትለው
ዩሱፍም፦" በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ
ነውና፤ (አልከዳውም)፡፡ እነሆ! በደለኞች አይድኑም" አላት።
በዚህ አጋጣሚ ዩሱፍ በሩን ከፍቶ ሲወጣ የሴትየዋ ባል፣የከተማይቷ
አስተዳዳሪ፣የራሱ አለቃ....በር ላይ ተገጣጠሙ።ሚስቱ ዩሱፍን ተከትላም
ስትወጣ ባሏን በር ላይ አገኘችው።ለትንሽ ሰዐት በሶስቱም መሀከል ዝምታ
ሰፈነ።በመቀጠልም ምን እየተከሰተ እንደነበር አስተዳዳሪው ሲጠይቃቸው
ሚስትየው ቀደም ብላ፦" በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር
ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም" አለች።
ዩሱፍም ንግግሯ ውሸት እንደሆነ አስተባበለ በዚህ መሀልም አንድ በወራት
ቤት ያለ የዙለይካ የዘመዷ ህፃን ልጅ ሊዳኛቸው አላህ በመሀል አስገባው።
ህፀኑም፦" ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀድዶ እንደሆነ (እሷ)እውነት ተናገረች፡፡
እርሱም ከውሸታሞቹ ነው
ቀሚሱም ከበስተኋላ ተቀድዶ እንደሆነ እሷ ዋሸች፡፡እርሱም ከእውነተኞቹ
ነው"በማለት ፍርዱን ሰጠ።
አስተዳዳሪውም በመገረም ቀሚሱን ሲመለከት የተቀደደው ከኋላ ነው።ወደ
ሚስቱ ዞር በማለት፦" እርሱ (የተናገርሺው) ከተንኮላችሁ ነው (ሴቶች)
ተንኮላችሁ በእርግጥ ብርቱ ነውና" ብሎ ወቀሳት።
ለዩሱፍም ወሬውን እንዳያሰራጭ ነገረው።
ነገር ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ ወሬው በከተማይቱ እጅጉን ተሰራጨ።(ወይ
dire tube የለ...ወይ ethiopian dj የለ...)ግን ብቻ ወሬው ከአጥናፍ
እስካጥናፍ ተሰራጨ።ይንህ የወሬውን መሰራጨት ዙለይካ ስትሰማ አንድ ሴራ
ጠነሰሰች'ና አንድ ትልቅ ዝግጅት በማዘጋጀት የከተማውን የመሳፍንት እና
የከበርቴ ሚስቶችን ባጠቃላይ ጠራች።
ከዚያም በዝግጅቱ ሁሉም ሴት መገኘቱን ስታረጋግጥ ፍራፍሬ እና ቢለዋ
በመስጠት እሷ መብላት ጀምሩ ሳትል ማንም እንዳይበላ አዘዘቻቸው።
በዚህ መሀል አሁን መብላት ትችላላችሁ ብላ ሴቶቹ የያዙትን ፍራፍሬ
መቆራረጥ ሲጀምሩ፦"ዩሱፍ ና ግባ" በማለት ድምጿን ከፍ አድርጋ
ጠራችው።ዩሱፍም ያማረ ልብስ አስለብሳው ነበር'ና ልክ የሌሊት ጨረቃ
መስሎ ወደ ውስጥ ሲገባ ሴቱ ሁሉ አይናቸው በሱ ፈዘዘ'ና ፍራፍሬውን
ረስተው እጆቻቸውን በያዙት ቢለዋ በመሸረካከት፦" አላህም ጥራት ይገባው፡፡
ይህ ሰው አይደለም፡፡ ይህ ያማረ መልአክ እንጅ ሌላ አይደለም" ማለት
ጀመሩ።
እሷም፦"ታዲያ ይህ ያ በርሱ (ፍቅር) የዘለፋችሁኝ ነው፡፡ በእርግጥም ከነፍሱ
አባበልኩት፡፡ እምቢ አለም፡፡ የማዘውንም ነገር ባይሠራ በእርግጥ ይታሰራል፡፡
ከወራዶቹም ይሆናል" አለቻቸው።
ዩሱፍም፦"ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር
ለእኔ የተወደደ ነው፡፡ ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ
እዘነበላለሁ፡፡ ከስህተተኞቹም እሆናለሁ" ሲል አላህን ተማፀነው።
የከተማይቱ አስተዳዳሪም በሚስቱ ሰበብ የጠፋውን ስሙን ለማደስ ሲል
ዩሱፍን እስር ቤት ለመጣል ወሰነ።ዩሱፍም እስር ቤት በገባ ግዜ እሱን
በፊትም የሚያውቁት ሁለት እስረኞች...
.@yenebiyattaric
4.6K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 08:08:16 .....መላዕክቱ እዛው ከተማ ውስጥ ናቸው...ሉጥ እና
ተከታዮቹ ከተማይቱን ልክ ለቀው እንደወጡ ከወደ ከተማይቱ ከፍተኛ
ድምፅ ሰሙ።
ማንም ወደ ከተማዋ እንዳይዞር ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠ ማንም አልዞረም
ነበር።የሉጥ ሚስት ግን ወደኋላ በመዞር፦"ወይኔ ወገኔ,,,,!!!" በማለት
ጮኸች።
ትልቅ የድንጋይ ፍንጣሪ መጣና እራሷን ለሁለት ከፈለላትና የመቅሰፍቱ ሰለባ
ሆነች።አላህም ይህን ዘግናኝ ክስተት ሲተርክ እንዲህ ይላል፦"ትዕዛዛችንም
በመጣ ግዜ (የከተማይቱን) ላይዋን ከታች አደረግን(ገለባበጥናት) ተከታታይም
የሆነ የሸክላ ድንጋይ በርሷ ላይ አዘነብን" (ሱረቱል ሁድ)
እንዴት አድርጎ እንደገለባበጣቻው ታውቃላችሁ...!!!መጀመሪያ ጂብሪል
ክንፉን በከተማይቱ መሬት ውስጥ ዘቅዝቆ አስገባው።ከዚያም ከተማይቱን ከነ
ህንፃዎቿ ነቅሎ ወደ ሰማይ ከፍ ካደረገ በኋላ ገለበጠው'ና መልሶ ወደ ምድር
ተከለው።
ሉጥ ከነ ተከታዮቹ ብዙ ርቀት ከተጓዘ በኋላ ሱዒር የተባለ አከባቢ በመስፈር
ይህ ነው ተብሎ በታሪክ መዛግብት እድሜው ባይሰፍርም እዛው ሱዒር ላይ
ህይወቱ አልፏል። (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም)
________________________________

ነገ በ አላህ ፍቃድ #የነብዩሏህ_ዩሱፍን ዐለይሂ ሰላም ታሪክ ይዤላችሁ
የምቀርብ ይሆናል :: አሏህ ሰላማችሁን ያብዛልኝ....

ኢንሽአላህ
ይ.......ቀ......ጥ.....ላ....ል፡፡


ሌሎች የነብያት፣ ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ
እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ
አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።
.@yenebiyattaric
.@yenebiyattaric
3.5K viewsedited  05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 21:10:33 #ነብዩሏህ_ሉጥ_ (አለይሂ ሰላም)

ክፍል

★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም
ማስተማራቸውን ቀጠሉ። ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና
ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ። ሉጥ (ዐ.ሰ) በአላህ (ሱ.ወ)
እንደሚጠበቁ በመዘንጋት የሰዶም ሕዝቦች ሊያጠቋቸው ሞከሩ።
ውዶች በባለፈው ትምህርታችን ላይ ታስታውሱ እንደሆነ መላእክት ነቢዩላህ
ኢብራሂም ቤት ሄደው ዘይሯዋቸው ከዚያም መላእክት ራሳቸውን ለኢብራሂም
አስተዋወቁ። “እኛ አዋቂ ልጅ እንደምታገኝ ልናበስርህ ከጌታህ ዘንድ የተላክን
መልዕከተኞች ነን።” አሏቸው። «አሁን ከአንተ ቤት ወጥተን ወደ ሉጥ ሕዝቦች
በመሄድ ሉጥን እንረዳዋለን። የሕዝቦቹ መጥፊያ በዚህች ሌሊት ነው።
ቀጠሯቸው ጐህ ሲቀድ ነው። በማለት መላእክቱ የመጡበትን ዓለማ
ለኢብራሂም (ዐ.ሰ) አስረዱ። ኢብራሂም በሁኔታው ተደናግጠው ነገሩ
እንዲዘገይ ለማድረግ ሞከሩ። መላእክቱ ግን የአላህ ትእዛዝ ስለሆነ ሳይዘገይ
የሚፈጸም መሆኑን አስረዷቸው።
መላእክቱ ከነብዩ ኢብራሂም ቤት ወጥተው ወደ ሰዶም መንደር አመሩ። አስር
ሶላት ወቅት ሲሆን ሰዶም መንደር ዳርቻ ደረሱ። እዚያ ቦታ ላይ በደን ውስጥ
የሚፈስ ወንዝ ነበር። ከወንዙ ዳርቻ አንዲት ልጅ ውሃ ለመቅዳት ቆማ አገኟት።
ይህች ልጅ የሉጥ (ዐ.ሰ) ልጅ ነበረች። ሦስቱን ወጣቶች ስታይ ለየት ያለ
ውበት ስለነበራቸው ተደናገጠች። ከሦስተኛው አንደኛው የሉጥ ቤት የት
እንደሆነና እንግዳም ይቀበሉ እንደሆነ ጠየቃት። ልጅቷም የሰዶም ሰዎችን
አስፀያፊ ተግባር ስለምታውቅ «ለአባቴ ነግሬ መልሱን እስከምነግራችሁ ድረስ
እዚሁ ቆዩ። ወደ ሰዶም እንዳትገቡ» ብላ አስጠነቅቃቸው የውሃ እቃዋን ወንዙ
ዳር ተወችና ፈጥና ወደ አባቷ ሉጥ (ዐ.ሰ) ዘንድ በመሄድ ሦስት ወጣቶች
እሳቸውን ፈልገው እንደመጡ ነገረቻቸው።
ሉጥ ይህን መልዕክት ሲሰሙ ተደሰቱ ወይስ አዘኑ? ስለሁኔታው አላህ (ሱ.ወ)
በሁድ ምዕራፍ ውስጥ እንዲህ ይላል፦
ﻭَﻟَﻤَّﺎ ﺟَﺎٓﺀَﺕْ ﺭُﺳُﻠُﻨَﺎ ﻟُﻮﻃًۭﺎ ﺳِﻰٓﺀَ ﺑِﻬِﻤْﻮَﺿَﺎﻕَ ﺑِﻬِﻢْ ﺫَﺭْﻋًۭﺎ ﻭَﻗَﺎﻝَ ﻫَـٰﺬَﺍ ﻳَﻮْﻡٌ ﻋَﺼِﻴﺐٌۭ ﴿٧٧ ﴾
“መልዕክተኞቻችን ሉጥን በመጡት ጊዜ በነሱ (ምክንያት) አዘነ። ልቡም በነሱ
ተጨነቀ። ይህ ብርቱ ቀን ነውም አለ።“ (ሁድ፥ 77)
ሉጥ (ዐ.ሰ) «ዛሬ አስቸጋሪ ቀን ነው። አሉና ፈጥነው ወደ እንግዶቹ ሄዱ።
እንግዶቹን ሲያዩ ለሰዶም ሰዎች መጥፎ ተግባር እንዳይጋለጡ በመፍራት
ይበልጥ አዘኑ።
ሉጥ እንግዶቹን ከየት እንደመጡ ጠየቋቸው። መልስ ሰጧቸው። ወደ የት
እንደሚሄዱ ሲጠይቋቸው ግን መልስ አልሰጧቸውም ነበር። ይልቁንም
በእንግድነት እንዲቀበሏቸው ጠየቋቸው።
ሉጥ (ዐ.ሰ) እንግዶቹን ለማስተናገድ ስስት አልነበረባቸውም። ነገር ግን
መላእክት መሆናቸውን ስላላወቁ የመንደሩ ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን
እንዳይፈጽሙባቸው ፈርተው ነበር ያዘኑት። ከዚያም ፊት ለፊት እየመሩ
እንግዶቻቸውን አስከትለው ወደ ሰዶም መንደር ገቡ። በመንገድ ላይ እያሉ
ሉጥ (ዐ.ሰ) ቆም አሉና «ከዚህ አገር ሰዎች አስጠንቅቃችኋለሁ። በመሬት ላይ
እንደነዚህ ሰዎች ቆሻሻ ሰው የለም» አሏቸው። መላእክቱ ሉጥ በሰጧቸው
ማስጠንቀቂያ ላይ ምንም አስተያየት ሳይሰጡ ዝም ብለው መንገዳቸውን
ቀጠሉ።
ሉጥ (ዐ.ሰ) ለእንግዶቹ ይህን ያሏቸው ከሰዶማዊያን ዓይን እንዲርቁ ፈልገው
ነበር። እንግዶቹ ግን ምንም ሳይናገሩ ፀጥ ብለው ቆዩ። በዚህን ጊዜ ሉጥ
(ዐ.ሰ) ወደ ሰዶም መንደር በሌሊት ተደብቀው እንዲገቡ ጠየቋቸው።
እንግዶቹ ይህን ተቀብለው ማንም ሳያያቸው ከሉጥ ጋር በመሆን በሌሊት ወደ
ከተማዋ ገቡ። ሉጥ (ዐ.ሰ) እንግዶቹ ሌሊት ገብተው ጠዋት ጐህ ሲቀድ
ማንም ሳያያቸው ይወጣሉ በሚል አስበው ነበር።
ሉጥ (ዐ.ሰ) አሁን ካሁን መጥፎዎቹ ሰዎች እነዚህን እንግዶች እንዳያይዋቸው
እየተጨነቁ ከሦስቱ እንግዶቻቸው ጋር እንደምንም ወደ ቤታቸው ገቡ።
ከመንደሩ ሰዎች ማንም አላያቸውም ነበር። ነገር ግን በቤት ውስጥ
የነበረችው ከሓዲዋ ሚስታቸው እንግዶቹን እንዳየች ተደብቃና ድምጽዋን
አጥፍታ ከቤት ወጣች።
★ የሉጥ (ዐ.ሰ) ሚስት በፍጥነት ወደ ሰዶማዊያኑ በመሄድ በሉጥ ቤት
ከሰዶም ያልሆኑ እንግዶች እንዳሉ ነገረቻቸው። ብልሹዎቹ ሰዎች ይህን ሲሰሙ
ተደስተው እየተጠራሩ ወጡ። ከዚያም በአንድ ላይ ተሰብስበው ወደ ሉጥ ቤት
አመሩ። ሉጥ (ዐ.ሰ) ማን እንደነገራቸው ሲያስቡ፡ ሚስታቸው ቤት ውስጥ
አለመኖሯን አወቁ። ሐዘናቸው በጣም ጠና።
ከየአቅጣጫው የተሰበሰቡት ሰዶማዊያን የሉጥን ቤት ከበቡ። ቀጥሎም በሩን
መቆርቆር ጀመሩ። ሉጥ (ዐ.ሰ) ምን እንደምፈልጉ ጠየቋቸው። በፊታቸው ላይ
መጥፎ ነገር ይነበብ ነበር። ሉጥ (ዐ.ሰ) ተንኮለኞችን ለመመለስ ቢሞክሩም
አልቻሉም። ከዚያም፦
ﻭَﺟَﺎٓﺀَﻩُۥ ﻗَﻮْﻣُﻪُۥ ﻳُﻬْﺮَﻋُﻮﻥَ ﺇِﻟَﻴْﻪِ ﻭَﻣِﻦ ﻗَﺒْﻞُ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ۟ﻳَﻌْﻤَﻞَﻥﻭُ ﭐﻟﺴَّﻴِّـَٔﺎﺕِ ۚ ﻗَﺎﻝَ ﻳَـٰﻘَﻮْﻡِ ﻫَـٰٓﺆُﻟَﺎٓﺀِ ﺑَﻨَﺎﺗِﻰ ﻫُﻦَّ
ﺃَﻃْﻬَﺮُ ﻟَﻜُﻢْ ۖ ﻓَﭑﺗَّﻘُﻮﺍ۟ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﻭَﻟَﺎ ﺗُﺨْﺰُﻭﻥِ ﻓِﻰ ﺿَﻴْﻔِﻰٓ ۖﺃَﻟَﻴْﺲَ ﻣِﻨﻜُﻢْ ﺭَﺟُﻞٌۭ ﺭَّﺷِﻴﺪٌۭ ﴿٧٨ ﴾
“ሕዝቦቼ ሆይ! እኝህ ሴቶች ልጆቼ ናቸው። እነሱ ለእናንተ ይልቅ በጣም የጸዱ
ናቸው። (አግቧቸው)። አላህንም ፍሩ። በእንግዶቼም አታሳፍሩኝ። ከናንተ
ውስጥ ቅን ሰው የለምን?” (ሁድ፥ 78)
በማለት አናገሯቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) ሰዎቹ ሐራምን ትተው ወደ ሐላል እንዲዞሩ
መንገድ ቢያሳዩዋቸውም አሻፈረኝ በማለት መጥፎ የመሥራት ፍላጎታቸውን
ለማሳካት መሞከራቸውን ቀጠሉ። በዚህን ጊዜ ሉጥ (ዐ.ሰ) በራቸውን ዘጉ።
ሰዎቹም በሩን በኃይል ነቀነቁት። ሉጥ (ዐ.ሰ) በሁኔታው ተስፋ ቆረጡ።
ﻗَﺎﻝَ ﻟَﻮْ ﺃَﻥَّ ﻟِﻰ ﺑِﻜُﻢْ ﻗُﻮَّﺓً ﺃَﻭْ ﺀَﺍﻭِﻯٓ ﺇِﻟَﻰٰ ﺭُﻛْﻦٍۢ ﺷَﺪِﻳﺪٍۢ ﴿٨٠ ﴾
“ በናንተ ላይ ለኔ ኃይል በኖረኝ ወይም ወደ ብርቱ ወገን ቢጠጋ ኖሮ
(የሚሠራውን በሠራሁ ነበር)።” (ሁድ፥ 80)
አሏቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) የተንኮለኞቹን ክፋት ለመከላከል በቂ ኃይል በነበረኝ
ብለው ተመኙ ።
በዚህን ጊዜ መልአኩ ጅብሪል ቆመና፦ይህን የሉጥን ሁኔታ እና እንግልት
የተመለከቱት በወጣቶች የተመሰሉት መላዕክት ሉጥን ጠሩት'ና ሁሉንም ነገር
ግልፅ አደረጉለት። መላዕክት መሆናቸውንም አክለው ነገሩት።
1፦ጂብሪል
2፦ሚካኢል
3፦ኢስራፊል....ነበሩ።
በመጨረሻም ይህችን ከተማ ሊያጠፏት እንደሆነ እና ሉጥ ቤተሰቦቹን እና
ተከታዮቹን ሁሉ ሰብስቦ ሱብሂ ሰዐት ከተማይቱን ለቅቆ እንዲወጣ አዘዙት።
በዚህ ሁኔታ ሉጥ እንግዶቹን እያወራ ሳለ ህዝቡ በሩን ሊገነጥል ተቃረበ ያን
ግዜ ጂብሪልም አላህን አስፈቀደ'ና አንድ ግዜ በሩን ከፍቶ በመውጣት በክንፉ
ፊት ፊታቸውን ክፉኛ መታቸው አይኖቻቸውም እዛው መፍሰስ ጀመሩ።
ጠዋት ሲነጋ ሉጥን እንደሚገድሉት እየዛቱ ሁሉም ከበሩ እየተተራመሱ
ሄዱ።ከዚያም
ሉጥ መላዕክቱን፦"መቼ ነው እነዚህን ህዝቦች ምታጠፉት" አላቸው።
እነሱም፦"ሱብሂ ላይ ነው" አሉት።
ሉጥም፦"አሁኑኑ ብታጠፏቸውስ" ሲላቸው...
መላዕክቱም፦"እንዴ ሱብሂ ቅርብ አይደል ወይ!!!" አሉት።
በነጋታው ሉጥ ተከታዮቹን፣ቤተሰቦቹን እና አመፀኛዋን ሚስቱን ይዞ ከመቅሰፍቱ
ሽሽት ከከተማይቱ መውጣት ጀመረ። ሲወጣም ለተከታዮቹ በከተማይቱ
የሚወርደውን መቅሰፍት ማንም ዞሮ ማየት እንደሌለበት አስጠንቅቆ ተናገረ።
አሁም ጉዞ ጀምረዋል...
5.4K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-15 20:34:53 #ነብዩሏህ_ሉጥ_(ዐ.ሰ)

ክፍል

★ የሉጥ ሕዝቦች ነብያቸውን በማስተባበል በምድር ላይም ብልሹነትን
አነገሱ፥ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፦
ﻭَﻟُﻮﻃًﺎ ﺇِﺫْ ﻗَﺎﻟَﻠِﻘَﻮْﻣِﻪِۦٓ ﺃَﺗَﺄْﺗُﻮﻥَ ﭐﻟْﻔَـٰﺤِﺸَﺔَ ﻭَﺃَﻧﺘُﻢْ ﺗُﺒْﺼِﺮُﻭﻥَ ﴿٥٤﴾ ﺃَﺋِﻨَّﻜُﻢْ ﻟَﺘَﺄْﺗُﻮﻥَ ﭐﻟﺮِّﺟَﺎﻝَ ﺷَﻬْﻮَﺓًۭ ﻣِّﻦ
ﺩُﻭﻥِ ﭐﻟﻨِّﺴَﺎٓﺀِ ۚ ﺑَﻠْﺄَﻧﺘُﻢْ ﻗَﻮْﻡٌۭ ﺗَﺠْﻬَﻠُﻮﻥَ ﴿٥٥ ﴾
#“ሉጥንም_ለሕዞቦቹ_ባለ_ጊዜ_(አስተውስ)_እናንተ_የምታዩ_ስትኾኑ_ጸያፍን_ነገር_ትሠራላችሁን። #እናንተ_ከሴቶች_አልፋችሁ_ወንዶችን_ለመከጀደል_ትመጣላችሁን_በውነቱ_እናንተ_የምትሳሳቱ_ሕዝቦች_ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

እነዚህ ሕዝቦች በምሥራቃዊ ዮርዳኖስ ይኖሩ ነበር። ይህ ቦታ በሙት ባህር
አቅራቢያ ይገኛል። በአካባቢው አምስት መንደሮች ነበሩ። እነሱም;- “ሰዱም፣
ዑመራ” “አደመህ” “ሱወይም” “ባሊ’ዕ” ናቸው። ሉጥ (ዐ.ሰ) በዋናው
መንደር ሰዱም ይኖሩ ነበር። መጥፎና ርካሽ ተግባራትን ትፈፅም የነበረችውም
መንደር እሷ ነች።
የሰዱም ነዋሪዎች እርኩሶችና መጥፎ ከመሥራት የማይፈሩ ነበሩ። አስፀያፊ
ተግባራቸውን በግልጽ የሚፈጽሙበት መሰብሰቢያ ቦታ ነበራቸው። መንገደኛን
ይዘርፋሉ። ከሌላ አካባቢ ነጋዴዎች ከመጡ ተሰብስበው ዕቃቸውን ይቀማሉ።
የሉጥ ሕዝቦች ነፍሳቸውንም በእጅጉ የሚበድሉ እጅግ ቆሻሾች ነበር።
ካቆሻሻነታቸው የተነሳ በፆታ ግንኙነት ከሴት ይልቅ ወንድ ከወንድ ጋር መገናኘት
ይመርጡ ነበር።
እነዚህ ሰዎች መጥፎ ተግባራቸው ወሰን ያለፈ ስለሆነ ይህ አስፀያፊ ተግባር
ወደ ሌሎችም አካባቢዎች እንዳይዛመት እነሱን በማስተካከል ወይም
በማጥፋት ይህን መጥፎ ተግባራቸውን ማስወገድ የግድ ነበር። ምክንያቱም
ሲባል ነው።
# የሉጥ_ጥሪ
★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝቦቻቸው የሚሠሩትን አስፀያፊ ነገር ሲያዩ የወገኖቻቸው
በዚህ ሁኔታ መገኘት አሳሰባቸው። ሥነ-ምግባራቸው እንዲስተካከል
በማሰብም ምክር መለገስ ጀመሩ። የሉጥ ጥሪ ሥነ-ምግባራቸው በጅጉ
ለተበላሹና ቀልባቸው ለደረቀ ሰዎች የሚደረግ በመልካም ተግባር ማዘዝና
ከመጥፎ መከልከል ነበር። እነዚህ ሰዎች ምንም ሐያእ /ሐፍረት/ የሌላቸውና
አስጸያፊ ወንጀልን በጠራራ ፀሐይ የሚፈፅሙ ነበሩ። ከዚህም በላይ ሴት
በማግባት አላህ የፈቀደላቸውን ግንኙነት መፈጸም ትተው ከወንዶች ጋር
በመገናኘት ማንም አድርጎት የማያውቀውን አስጸያፊ ተግባር ይፈፅሙ ነበር።
ስለዚህም አላህ (ሱ.ወ) ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደ እነዚህ ሕዝቦች ሄደው ከቆሻሻ
ተግባራቸው እንዲፀዱ ጥሪ እንዲያደርጉላቸው ላካቸው።
ሉጥ (ዐ.ሰ) የነበዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የወንድም ልጅ ሲሆኑ በኢራቅ ባቢል
ነበር የተወለዱት። ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ ተውሂድ ጥሪ ሲያደርጉ
አምነው ከሳቸው ጋር ወደ ሻም አካባቢ ስደት በመሄድ በምሥራቅ ዮርዳኖስ
በሚገኘው ሱዲም ሸለቆ አካባቢ ሰፈሩ። በአካባቢው ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት
የምትፈጽስም ሰዱም የምትባል መንደር ነበረች። አላህ (ሱ.ወ) ነቢዩላህ
ሉጥን ወደ ሰዶምና አካባቢዋ ሕዝቦች፣ አላህን ብቻ እንዲያመልኩና ከመጥፎ
ተግባራቸው እንዲርቁ ለማስተማርና ወንድ ለወንድ ግንኙነት መፈጸማቸውን
ትተው አላህ የፈቀደላቸውን ሴቶቻቸውን በማግባት ግንኙነት እንዲፈፅሙ
እንዲያዟቸው አላህ ሉጥን ላካቸው። ይህ ዓይነቱ ወንጀል ከሰዶም ሕዝቦች
በፊት ማንም ያልሠራው አስጸያፊ ወንጀል ነበር
ነቢዩላህ ሉጥ (ዐ.ሰ)
ﺇِﺫْ ﻗَﺎﻝَ ﻟَﻬُﻢْ ﺃَﺧُﻮﻫُﻤْﻠُﻮﻁٌ ﺃَﻟَﺎ ﺗَﺘَّﻘُﻮﻥَ ﴿١٦١﴾ ﺇِﻧِّﻰ ﻟَﻜُﻢْ ﺭَﺳُﻮﻝٌ ﺃَﻣِﻴﻦٌۭ ﴿١٦٢﴾ ﻓَﭑﺗَّﻘُﻮﺍ۟ ﭐﻟﻠَّﻪَ
ﻭَﺃَﻃِﻴﻌُﻮﻥِ﴿١٦٣﴾
#“አትጠነቀቁምን? #እኔ_ለናንተ_ታማኝ_መልዕክተኛ_ነኝ።_አላህንም_ፍሩ።_ታዘዙኝም” (አሽ-ሹዐራእ፥ 161-163)
አሏቸው።
እንዲሁም ሉጥ እያዘኑላቸው ለዘብ ባለ ቃል!
ﻭَﻣَﺎٓ ﺃَﺳْـَٔﻠُﻜُﻢْ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻣِﻦْ ﺃَﺟْﺮٍ ۖ ﺇِﻥْ ﺃَﺟْﺮِﻯَ ﺇِﻟَّﺎ ﻋَﻠَﻰٰ ﺭَﺏِّ ﭐﻟْﻌَـٰﻠَﻤِﻴﻦَ﴿١٦٤ ﴾
#“በርሱም_ላይ_ምንም_ዋጋ_አልለምናችሁም። #ዋጋዬ_በዓለማት_ጌታ_ላይ_እንጅ_በሌላ_አይደለም።” (አሽ-ሹዐራእ፥ 164) በማለት አስገነዘቧቸው።

በዚህ ቃላቸው ውስጥ ሉጥ (ዐ.ሰ) ከነሱ ዓለማዊ ጥቅም እንደማይሹና
ብቸኛው ፍላጐታቸው የነሱ መስተካከልና አላህን ብቻ ማምለካቸው እንደሆነ
አስረዷቸው።
በመቀጠልም ሉጥ (ዐ.ሰ) ወደነዚህ ሰዎች አስፀያፊ ተግባር በመዞር
የሚከተለውን ተናገሯቸው።

ﻭَﻟُﻮﻃًﺎ ﺇِﺫْ ﻗَﺎﻝَ ﻟِﻘَﻮْﻣِﻪِۦٓ ﺃَﺗَﺄْﺗُﻮﻥَ ﭐﻟْﻔَـٰﺤِﺸَﺔَﻭَﺃَﻧﺘُﻢْ ﺗُﺒْﺼِﺮُﻭﻥَ ﴿٥٤﴾ ﺃَﺋِﻨَّﻜُﻢْ ﻟَﺘَﺄْﺗُﻮﻥَ ﭐﻟﺮِّﺟَﺎﻝَ ﺷَﻬْﻮَﺓًۭ ﻣِّﻦ
ﺩُﻭﻥِ ﭐﻟﻨِّﺴَﺎٓﺀِ ۚ ﺑَﻠْﺄَﻧﺘُﻢْ ﻗَﻮْﻡٌۭ ﺗَﺠْﻬَﻠُﻮﻥَ ﴿٥٥ ﴾ ۞
#“ሉጥንም_ለሕዝቦቹ_ባለ_ጊዜ_(አስተውስ)_እናንተ_የሚታዩ_ስትኾኑ_ጸያፍን_ነገር_ትሠራላችሁን። #እናንተ_ከሴቶች_ወንዶችን_ለመከጀል_ትመጣላችሁን_በውነት_እናንተ_የምትሳሳቱ_ሕዝቦች_ናችሁ። (አን-ነምል፥ 54-55)

የሰዶም ሰዎች አስፀያፊ ተግባራቸውን በግልጽና በስብሰባ ቦታዎች ሁሉ
ሳይቀር መፈጸማቸው ሉጥን በጣም አሳዘነ። #ሉጥ (ዐ.ሰ) ከዚህ አስፀያፊ
ተግባር ቢከለክሏቸውም «አንተ ሴቶችን አስተናግድ ወንዶችን ተውልን።»
በማለት አስፀያፊ መልስ ሰጧቸው።
ይህ ሁሉ ቢሆንም ነቢዩላህ #ሉጥ (ዐ.ሰ) ተስፋ ባለመቁረጥ የተለያዩ
ማስረጃዎችን በመጥቀስ ጥሪያቸ እውነት መሆኑን ሊያሳምኗቸው ሞከሩ።
ነገር ግን ድካማቸው በከንቱ ነበር። ቀናት ወራትን ወራት ዓመታትን እየተኩ
ዘመኑ ሄደ። #ሉጥም ዳዕዋቸውን ቀጠሉ። ነገር ግን ከቤተሰባቸው ውጭ
አንድም ሰው አላመነላቸውም ነበር። ከቤተሰባቸውም ውስጥ ሚስታቸው
አላመነችም ነበር። ከከሓዲያን ጐን ተሰለፈች። ይህም ሁኔታ #ሉጥ (ዐ.ሰ)
ከቤታቸው ውጭ ከሓዲያንን፣ በቤት ውስጥ ደግሞ ከሓዲት ሚስታቸውን
መታገል አስገደዷቸው። ስለሆነም በጣም ድካም ይሰማቸው ነበር። ቢሆኑም
ግን ትዕግስት እያደረጉ ያለ መሰላቸት ወደ አላህ ጥሪ ማድረጋቸውን ቀጠሉ።
ሕዝባቸው ግን ማመናቸው ቀርቶ በዳዕዋቸው በማላገጥ #“ከእውነተኞቹ_እንደሆንክ_የአላህን_ቅጣት_አምጣብን።” (አል-ዐንከቡት፥ 29)

ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም
ማስተማራቸውን ቀጠሉ። ከሓዲያኑ የሰዶም ሕዝቦች ሉጥ ላይ ማፌዛቸውንና
ማስቸገራቸውን አጠናክረው ቀጠሉ። ሉጥ (ዐ.ሰ) በአላህ (ሱ.ወ)
እንደሚጠበቁ በመዘንጋት የሰዶም ሕዝቦች ሊያጠቋቸው ሞከሩ።
ሉጥንና ቤተሰባቸውን በመናቅም።
#ﻭَﻣَﺎ ﻛَﺎﻥَ ﺟَﻮَﺍﺏَ ﻗَﻮْﻣِﻪِۦٓ ﺇِﻟَّﺎٓ ﺃَﻥ ﻗَﺎﻟُﻮٓﺍ۟ ﺃَﺧْﺮِﺟُﻮﻫُﻤﻢِّﻥ ﻗَﺮْﻳَﺘِﻜُﻢْ ۖ ﺇِﻧَّﻬُﻢْ ﺃُﻧَﺎﺱٌۭ ﻳَﺘَﻄَﻬَّﺮُﻭﻥَ ﴿٨٢ ﴾
#“ሉጥንና_ተከታዮቹን_ከከተማችሁ_አውጧቸው። አሉ። #እነሱ፡_የሚጥራሩ_ሰዎች_ናቸውና።” (አል-አዕራፍ፥ 82)
አሉ። የሰዶም ሕዝቦች ቆሻሾች ስለነበሩ ነቢያቸው ሉጥ «ከመጥፎ ነገር
ተመለሱ። በተመሳሳይ ፆታ መካከል ግብረ ሥጋ ግንኙነት አትፈጽሙ።» ብለው ሲመክሯቸው በሉጥና ተከታዮቻቸው ንፁህነት በመቀለድ “እነሱ ንፁሃን ናቸው”
ሲሉ አሾፉባቸው።
★ ሉጥ (ዐ.ሰ) ሕዝባቸው ቢቀልዱባቸውም ታግሰውና ችለው አሁንም ማስተማራቸውን ቀጠሉ።.....

ክፍል ኢንሽአላህ
ይ.....ቀ......ጥ.......ላ.......ል
5.1K views17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-03 21:21:56 ..ሁሉ ኬት አምጥተህ ነው?"
አለው።
ያዕቁብም፦"እነዚህ አላህ የሰጠኝ ስጦታዎቼ ናቸው" አለው።
ይህን ግዜ የያዕቁብ ልጆች እና ሚስቶች ተራ በተራ እየመጡ ዒስን ከዘየሩ
በኋላ ያዕቁብ በአገልጋዮቹ አማካኝነት ለዒስ የላከውን ስጦታ ዒስ መቀበል
እንቢ አለ።
ያዕቁብም ለምኖት እንዲቀበል አደረገው'ና አብረው በረሀውን እያቆራረጡ
አባታቸው ወደሚገኝበት የፊለስጢን ምድር መትመም ጀመሩ።
በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ያኔ....ያዕቁብ አጎቱ ጋ ሲሄድ ተኝቶ ህልም ያየበትን ቦታ
ደረሱና እዛ ቦታ ያዕቁብ በ200 በግ ያንን ቦታ ከአንድ ገበሬ ገዛው'ና አንድ
ትልቅ የአምልኮ ቦታ ሰራ(ቁድስ) ከዚያ በኋላ ነው በሱለይማን ዘመን
ሱለይማን ያደሰው።
በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ነበር አንድ ደስታ እና ትልቅ ሀዘን በያዕቁብ ቤተሰብ
የተከሰተው።ነፍሰ ጡር የነበረችው ትንሿ ራሂል ምጥ አስቸገራት...ብዙ
ከተጨነቀች በኋላ ቢንያሚን የተባለ ልጅ ተገላግላ ለራሷም ዱንያን
ተገላገለቻት።
ያዕቁብም ባለቤቱን መንገድ ላይ ቀብሮ ሀዘኑን ታቅፎ ወደ አባቱ ጉዞ
ቀጠለ።ከአባቱም ተገናኝቶ በከንዓን ምድር ሀብሩን በምትባል(ኢብራሂም
ይኖር በነበረበት) አካባቢ መኖር ጀመረ።
ኢስሀቅም እርጅና ተጫጭኖትም ስለነበር ጌታው የፃፈለትን 180 አመት
ካጠናቀቀ በኋላ ነፍሱን ለጌታው አስረከበ።
አሁን የያዕቁብን እዚህች ጋ ያዝ እናድርጋት'ና አንድ ግዜ ብቻ ወደኋላ
ልመልሳችሁ።ምክንያቱም የያዕቁብን አጠናቅቀን ሉጥ ጋ እንመጣለን ብንል
የያዕቁብን ትርካ ተከትሎ ነው ዩሱፍ የሚቀጥለው ለዛ አንዴ ቀኝ ኋላ ዙሩ....።
ኢንሻ አላህ በአሏህ ፍቃድ ነገ የሉጥን (ዐ.ሰ) ምንቀጥል ይሆናል

#የነብዩሏህ_ሉጥ(ዐ,ሰ)_ታሪክ
ኢንሽአላህ
ይ......ቀ.......ጥ.......ላ.......ል፡፡


ሌሎች የነብያት ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ
እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ቻናላችንን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።
@yenebiyattaric
@yenebiyattaric
3.9K views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-04 21:25:15 #የነብዩሏህ_ያዕቆብ(ዐ,ሰ) ታሪክ

ያዕቁብ ሙሽሪትን ተመለከታት ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት
ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት።
ያዕቁብ በጣም ተናደደ በጠዋት አጎቱ ጋ በመሄድ፦"አንተ ቃል ኪዳንን
አፍርሰሀል።እኔ የተዋዋልኩት ልጅህን ራሂልን ሀኖ ሳለ እንዴት ለያን
ትሞሽርልኛለህ" በማለት ወቀሰው።
የያዕቁብ አጎትም ላባን ብልጣ ብልጥ ነገር ነበር'ና፦"ይህማ በኛ ባህል ነውር
ነው...እንዴት ታላቅ እያለች ታናሽ ትዳራለች!!! በል ራሂልን ምትፈልግ እንደሆን
ለ7 አመት በጎችን አግድልኝ" አለው።
ያዕቁብም ራሂልን በጣም ወዷት ስለነበር 7 አመታትን ለመጠበቅ
ተገደደ።የማይደርስ የለም'ና ይህም ቀን ደረሰ።ያዕቁብም ለ14 አመት
የጠበቃትን ራሂልን በእጁ አስገባት።
(በነገራችን ላይ ሁለት እህትማማቾችን በአንድ ግዜ ማግባት በነሱ ህግ/ሸሪዓ
ክልክል አልነበረም።ከዚያ በኋላ ነው ተውራት ሲወርድ ይህ ህግ የተሻረው።)
ከዚያ ያዕቁብ ሁለት እህትማማቾችን አግብቶ ሳለ አጎቱ ላባን ለሁለት ለልጆቹ
ሁለት አገልጋዮችን በስጦታ መልኩ ጀባ አላቸው።
ለያ ለምትባለዋ፦ዘልፋ የምትባል አገልጋይ ሲሰጣት
ራሂል ለምትባለዋም፦በልሃ የምትባል አገልጋይ ሰጣት።
አላህም ለያ የምትባለዋን(ፉንጋዋን) 4 ወንድ ልጆችን በመስጠት
ካሳት።ልጆቿም
1፦ረውቢል
2፦ሸምዑን
3፦ላዊ
4፦የሁዳ...ናቸው።
ትንሿ ረሂል ምንም እንኳም ቆንጅዬ ብትሆንም ልጅ መውለድ ግን
አትችልም።በታላቅ እህቷ መውለድ በጣም ቅናት ይይዛት'ና እራሷ ዘንድ
የምትገኘውን በልሀ የተባለችውን አገልጋይ ለገዛ ባለቤቷ ዳረችው'ና
አገልጋይዋም ከያዕቁብ
5፦ዳን
6፦ኒፍታሊ...የተባሉ ልጆችን ወለደች።
ያን ግዜ ለያ ከእህቷ ረሂል እልህ ተያያዘች'ና እሷም ዘልፋ የምትባል
አገልጋይዋን ለያዕቁብ ዳረችለት'ና ያዕቁብም ከዘልፋ
7፦ጃድ
8፦ዐሺር...የተባሉ ልጆችን ወለደችለት። ኧረ የሌላ ይደላል ያዕቁብ ዐ ሰ
በመሀል ተመቻቸው እኮ...ሱብሀን አላህ የአላህ ተርቲብ
ከዚያም ለያ(ታላቋ) አምስተኛ አረገዘች'ና
9፦ያሳካር...የተባለ ልጅ ወልዳ ብዙም ሳትቆይ
10፦ዛብሎን... የተባለ ልጅ ደገመች።አሁንም አላረፈችም
11፦ዲና... የምትባል ሴት ልጅ ለያዕቁብ አሳቀፈችው።ያ ማለት ለያ
ከያዕቁብ 7 ልጆችን ወለደች ማለት ነው።
ይህን ስታይ መቋቋም ያቃታት ራሂል አላህን ልጅ እንዲሰጣት መማፀን
ጀመረች።አላህም በሩን ያንኳኳውን በከንቱ ማይመልስ ጌታ ነው'ና ዱዓዋን
ተቀብሎ
12፦ዩሱፍ (ዐሰ) የሚባል ውብ እና ገራሚ የሆነ ልጅ ጀባ አላት።
ይህ ሁሉ የሚሆነው በአጎቱ ሀገር በሀራን ምድር ላይ ነው።አሁን ያዕቁብ
የትውልድ ሀገሩን ፊለስጢንን ለቅቆ የሀራንን ምድር ከረገጠ 20 አመታትን
አስቆጥሯል።
ያዕቁብም አጎቱ ዘንድ በመሄድ፦"አጎቴ አሁን ፍቀድልኝ'ና ሚስት ልጆቼን
ሰብስቤ ቤተሰቦቼ ጋር ልሂድ" ይለዋል።
አጎቱ ላባንም፦"ያዕቁብ እኔ ባንተ ሰበብ ብዙ ንብረቴ በረካ ሆኖልኛል።ስለዚህ
የፈለግከውን ያህል ንብረት ጠይቀኝ" አለው።
ላባን በጣም ለቁጥር ሚያዳግት የእንስሳት መዐት ስለነበረው
ያዕቁብም፦"በዚህ አመት የሚወለዱትን ሁሉ ባጎች ስጠኝ።
ከተቀረው እንስሳቶችህ መልካቸው ጥቁር በነጭ የሚወልዱትንም ስጠኝ።
ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችንም ስጠኝ" አለው።
አጎቱ ላባንም፦"እሺ" አለው።
ያዕቁብም ይህን ሀላፊነት ልጆቹ እንዲወጡ አዘዘ።በመጀመርያ ያዕቁብ እርጉዝ
የሆኑ እንስሳቶችን ከሌሎቹ እንስሳት የሶስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት
አራራቃቸው።
ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችን እንደዚያው አራራቃቸው።ይህን ካደረገ
በኋላ እርጉዞቹም ወለዱ ያዕቁብም ድርሻውን ለይቶ በአላህ ትዕዛዝ ለጉዞ
ተዘጋጀ።
አሁን ያዕቁብ የብዙ ሺህ በጎች...እንስሳቶች...እና የብዙ አገልጋዮች ባለቤት
ሆኗል።ወደ ፊለስጢን ጉዞ ሲዝጀምሩ ራሂል የተባለችዋ የያዕቁብ ሚስት
የአባቷን ጣኦት ደብቃ ይዛ ወጣች።
ያዕቁብ ልጆቹን፣ሚስቶቹን፣አገልጋዮቹን፣እንስሳቶቹን...ሁሉ ሰብስቦ በረሀውን
እያቋረጠ ብዙ ተጎዞ የሀራንን ምድር ካጋመሰ በኋላ አጎቱ ላባን እና የሀራን
ከተማ ነዋሪዎች ተከትለውት ደረሱበት።
ልክ እንዳገኙት አጎቱ ላባን በወቀሳ መልኩ፦"ያዕቁብ ለምን ሳትነግረኝ ትተህ
ትሄዳለህ!!! ምነው በደስታ ተሰነባብተን ከአከባቢው ህዝብ ጋር ጨፍረን
ብንሸኛቹስ" በማለት አንድ ጣኦት ይዘው እንደመጡም አክሎ ጠየቀው።
ያዕቁብ ዐ ሰ ምንም አይነት ከጣኦት ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ለአጎቱ ሲል
የሚስቶቹን እቃ ሀሉ ፈተሸለት ምንም አላገኘም።
ራሂል ግን ጣኦቱን ይዛው ስለነበር ለፍተሻ ፍቃደኛ አልሆነችም ነበር አሞኛል
አልነሳም አለች።ያን ግዜ ያ ጣኦት ምናልባት ጀልዓድ በተባለ ዳገት ላይ
ይኖራል በሚል ግምት ላባን ልጆቹን እና የእህቱን ልጅ ያዕቁብን ተሰናብቷቸው
ተመለሰ።
ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ሊገባ ጥቂት ሲቀራው መላዕክት እየወረዱ እንኳን
ደህና መጣህ እያሉት ያልፉ ነበር።
አሁን ያዕቁብ ሳዒር የምትባል ቦታ ላይ ደርሷል ግን ሀገሩ ሊገባ የወንድሙን
በቀል ፈርቷል።እዛው ሆኖ እንደማለማመጥ አይነት ነገር ፅፎ ደብዳቤ
ለወንድሙ ላከለት።
በነጋታው ሌላ የዛቻ ደብዳቤ የያዘች ወረቀት ዒስ(የያዕቁብ ወንድም) 400
እግረኛ ጦር አሰልፎ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዳ መልዕክት ከወደ ፊለስጢን
በኩል ለያዕቁብ መጣችለት።
ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው
ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።
ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው
ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ።
ከዚያም ወንድሙን ሊያስደስት በርከት ያለ ስጦታም አዘጋጀለት...
200 ሴት ፍየሎችን እና 20 ወንድ ፍየሎች
200 ሴት በጎችን እና 20 ወንድ በጎች
30 (ኮርማ)በሬዎችን እና 40 ላሞች
20 ሴት ግመሎችን እና 10 ወንድ ግመሎች
እና አራቱንም የስጦታ አይነቶችን ለያይቶ ሊልክ በአራት ቡድን የተደራጀ
አገልጋዮችን አዘጋጀ እና ቀድሞ አንዱን ቡድን ለከ።
የመጀመርያው ቡድን ስጦታን ይዞ ሄዶ ትንሽ ራቅ ሲል ሁለተኛውን ይልካል
ሁለተኛውም ትንሽ ራቅ ሲል ሶስተኛውን ይልካል....እንዲ እንዲ እያለ
አራቱንም የስጦታ አይነት ከነ አገልጋዮቻቸው ጨምሮ፦"ማንም የማን ነው
ብሎ ከጠየቃችሁ ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው በሉ" ብሎ ላካቸው።
ይህንንም ሊያደርግ የቻለው ወንድሙ ዒስ ስጦታዎች በተከታታይ ሲመጡለት
ደስታው የላቀ ይሆናል በሚል ነው።
ከዚያም የመጀመሪያውን ስጦታ የያዘው የአገልጋልይ ቡድን ዒስ እና ወታደሮቹ
ያሉበትን ቦታ ሲደርሱ
ዒስ፦"ይህ የማን ነው?" ብሎ ጠየቀ።
አገልጋዮቹም፦" ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው" አሉት።
እሱን ተቀበላቸውና ሁሉም የስጦታ ነጂ ቡድኖች ስጦታዎቻቸውን ተራ በተራ
እየነዱ አስረከቡት።
ያዕቁብም ሚስቶቹን ልጆቹን እና የተቀሩ አገልጋዮቹን አስከትሎ በሌሊት ወደ
ወንድሙ ጉዞ ጀመረ።(በነገራችን ላይ በዚህች የሌሊት ጉዞ ነበር ክርስቲያን
ወገኖች ያዕቁብ እና እግዚአብሄር ተደባድበው ያዕቁብ አሸነፈው የሚሉት።)
ሌሊቱን ተጉዞ ፀሀይ ጀንበሯን አምልጣ መውጣት ስትጀምር ለ20 አመታት
ያህል የተለያዩ ወንድማሞች አይን ለአይን ተገጣጠሙ።
ዒስ 400 ጦረኛዎችን አሰልፏል።ያዕቁብም ወንድሙን ሲያየው 7 ግዜ
አጎበደደለት(ይህ በዘመናቸው ሀራም አልነበረም የዘመናቸውም ሰላምታ
ነበር።በቀጣይ ክፍላችን ለዩሱፍ ሲሰግዱ እንዳስሳለን"
ዒስ ዱዓውን ከአባቱ የዘረፈውን ወንድሙን ሲያይ ሄዶ ተጠምጥሞበት
ወንድሙን እየሳመ ያለቅስ ጀመር።በዚህ አጋጣሚ ከአጠገቡ ያሉትን ሴቶችን
ልጆችን እና አገልጋዮችን ሲመለከት፦"ይሄም..
@yenebiyattaric
4.4K views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-04 21:18:02 ....ምር ያዕቁብ ሙሽሪት
ን ተመለከታት።ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት ራሂል ሳትሆን
ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት።
ያዕቁብ በጣም ተናደደ.......


#የነብዩሏህ_ያዕቁብ_ታሪክ
ኢንሻአላህ
...ይ
........ቀ
.............ጥ
..................ላ
.......................ል፡፡
@yenebiyattaric
@yenebiyattaric
3.5K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-23 21:21:45 #ኢብራሂም ነብዩሏህ_ዒስማኢል እና #ነብዩሏህ_ዒስሃቅ

አሁን ዒስማኢል (ዐሰ) ጎርምሷል፣ለሁሉ ነገር ብቁ የሆነ ወጣትም ሆኗል።ውሀ
ፍለጋ መጥተው እዛው ኑሮዋቸውን ያደረጉት የጁርሀም ብሄረሰቦችም
ኢስማዒልን እጅጉን ይወዱታልም።
ቋንቋቸውንም አስለምደውት ባህላቸውንም አላብሰውታል።ለአቅመ አዳም
መድረሱን በተመለከቱም ግዜ ከራሳቸው ዘር የሆነችን እንስትም ዳሩለት።
ኢስማዒል (ዐ ሰ) ትዳር እንደያዘ እናትየው ሀጀር ብዙም ሳትቆይ ነበር
ለፈጣሪዋ ነፍሷን ያስረከበችው።ኢስማዒልም ያለ አባት ያሳደገችው እናቱ
ስትለየው እጅጉን ቢያዝንም ምላሹ ግን ዱዓ ብቻ ነበር።
ምንም እንኳን የኢስማዒል አባት ኢብራሂም (ዐ ሰ) በዛ ግዜ ትልቅ ሽማግሌ
ቢሆኑም የአብራካቸውን ክፋይ ለመጎብኘት ከፊለስጢን ምድር መካ ድረስ
በየግዜው ይመላለሱ ነበር።ነገር ግን አሁን ትንሽ ሰንበትበት ብለዋል መካ
ከመጡ...
ልክ መካ እንደደረሱ ልጃቸው ቤት ሲገቡ የልጃቸውን ሚስት
ያገኟታል።ኢስማዒል የት እንዳለም ሲጠይቋት ለአደን ከከተማ እንደራቀ
ነገረቻቸው።
እሳቸውም ቀጠል አድርገው ፦"ልጄ ኑሯቸሁ እንዴት ነው?" ብለው ሲጠይቋት
እሷም፦"ኑሮዋችን በጣም ዝቅተኛ ነው..."በማለት ብዙ ስሞታ አቀረበች።
እሳቸውም፦"በይ ልጄ እኔ መሄዴ ነው።ኢስማዒል ሲመጣ ሰላምታዬን
አድርሺልኝ።በመቀጠልም የበሩን መዝጊያ እንዲቀይርም ንገሪው" ብለዋት
ትተው ሄዱ።
ኢስማዒልም ከአደን ሲመለስ ሚስቱ፦"አንድ ሽማግሌ ሰውዬ መጥቶ
ነበር።ሰላም በይልኝ ብሎ የበርህንም መዝግያ እንድትቀይር አዞሀል" ስትለው
አባቱ መሆኑን አውቆ የበር መዝጊያ ደሞ ሚስቱን እንደሆነ በመረዳት ሚስቱን
ፈታት።
ኢስማዒልም ሌላ አዲስ ሚስት አገባ።ከእለታት አንድ ቀንም የልጃቸው ናፍቆት
አላስቀምጥ ያላቸው ኢብራሂም ከ ፊለስጢን ምድር ልጃቸውን ሊያዩ ሲከንፉ
መጡ።
ቤት ሲደርሱ ሌላ ሴት ተመለከቱ'ና፦"ልጄ ኢስማዒል የት ነው" ብለው
ሲጠይቋት
እሷም፦"ለአደን ራቅ ወዳለ ቦያ ሄዷል ኑ ግቡ"አለቻቸው።
እሳቸውም፦" ኑሮዋችሁስ እንዴት ነው?" ሲሏት
እሷም፦"በጣም ጥሩ ነው ሁሌ ድሎት ሁሌ ምቾት ነው" ብላ መለሰችላቸው።
እሳቸውም፦" በይ ልጄ እኔ መሄዴ ነው።ኢስማዒል ሲመጣ ሰላምታዬን
አድርሺልኝ።በመቀጠልም የበሩን መዝጊያ ጠበቅ አድርጎ እንዲይዝ ንገሪልኝ"
ብለዋት ሄዱ።
ኢስማዒልም ከአደን ሲመለስ ሚስቱ፦"አንድ ሽማግሌ ሰውዬ መጥቶ
ነበር።ሰላም በይልኝ ብሎ የበርህንም መዝግያ ጠበቅ አድርገህ እንድትይዝ
አዞሀል" አለችው።
ኢስማዒልም አባቱ ይህችኛዋን ሚስቱን እንደወደዱለት ተረድቶ ይልቅ
ያከብራትም ጀመር።
ለዚያ አካባቢ እና በዙሪያዋ ላሉ ነገዶች፣ለአማሊቃዎች፣ለጁርሀሞች እና
ለየመኖች በነቢይነት ሲያገለግል የነበረው ኢስማዒል (ዐ ሰ) ቀደምት አባቶቹ
የቀመሱትን የሞት ፅዋ መቅመሻው ግዜ ሲደርስ ነስማ የተባለችውን ሴት
ልጁን የወንድሙ የኢስሀቅ ልጅ የሆነው ዒስ እንዲያገባት ተናዝዞ በተወለደ
በ173 አመቱ የሙታንን መንደር ተቀላቀለ።...{ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም}
አሁን እግረ መንገዳችን የኢስሀቅን ህይወት ጎራ ብለን እንመልከት...
ለኢስሀቅ አባቱ ኢብራሂም (ዐሰ) በህይወት ሳለ በ40 አመቱ ነበር ረፍቃ ቢንት
በትዋዪል ከተባለች እንስት ትዳር ያስያዘው።
ምንም እንኳን ረፍቃ መውለድ የማትችል መሃን ብትሆንም በባለቤቷ ያላሰለሰ
ዱዓ ሁለት መንታ ልጆችን ለመታደል በቅታለች።
አንደኛው፦ዒስ ሲሆን
ሁለተኛው፦ያዕቁብ (ዐሰ) ይባላል።
ዒስ የሮም ህዝቦች ቅድመ አያት ሲሆን፤ ያዕቁብ ደሞ የእስራኢላውያን ቅድመ
አያት ነው። የሁለቱም አባት ሁለቱንም ልጆቹን በጣም ቢወዳቸውም ከያዕቁብ
ይልቅ ለዒሱ ግን ለየት ያለ ቦታ ነበረው።
እናታቸው ረፍቃ ግን ያዕቁብ ታናሽ ስለሆነ ይበልጥ እሱን ነበር የምትወደው።
ኢስሀቅ ከእርጅና የተነሳ አይናቸው ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል።
ከእለታት አንድ ቀን ኢስሀቅ (ዐሰ) ስጋ ያምራቸውና የሚወዱትን ልጃቸውን
ዒስን አደን አድኖ ስጋ እንዲያመጣለቸው እናም ከባድ ዱዓም
እንደሚያደርጉለት ነግረውት እሱም ለአደን ሄደ።
ይህን በድብቅ ስትሰማ የነበረችውም የልጆቹ እናት ረፍቃ ለያዕቁብ ነግራው
ከፍየሎቹ ወፍራሙን ሙኩት እንዲያርድ ካደረገች በኋላ የወንድሙን ዒስን
ልብስ አልብሳው እራሱን(ዒስን) አስመስላ የሰራውን ስጋ ለአባቱ እንዲያቀርብ
አደረገች።
ያዕቁብም ያዘጋጀውን ምግብ ይዞ አባቱ ዘንድ ሲያቀርብ
አባቱ፦"ማን ነህ አንተ?" አሉት።
ያዕቁብም፦"ልጅዎት ነኝ"አለ።
አባቱም(ኢስሀቅ)፦"ድምፅህ የያዕቁብ ነው፤ልብስህ ግን የዒስ ነው" በማለት
የቀረበላቸውን ምግብ በሉት።
ምግቡን በልተው እንደጠገቡም ምግቡን ላቀረበው አላህ ክብሩን ከፍ
እንዲያደግለት፣ የበላይ ዘርም እንዲያደርገው፣ልጆቹንም ሪዝቁንም አላህ
እንዲያበረክትለት ዱዓ አደረጉ።
ልክ ዱዓውን እንዳጠናቀቁ ያዕቁብ አሚን ብሎ የአባቱን ክፍል ለቆ
ወጣ።ያዕቁብም ሲወጣ ዒስ በታዘዘው መልኩ ያደነውን ስጋ ጠባብሶ ለአባቶ
አመጣ'ና አቀረበ። አባቱ ግን ቅድሙኑ ጠግበዋል።
ዒስ ምግቡን ሲያቀርብላቸው፦"ልጄ ይህ ምንድነው?" አሉት።
ዒስ'ም፦"አምጣልኝ ያሉት ስጋ ነዋ" አላቸው።
አባትየውም፦"አሁን አምጥተህልኝ በልቼ ዱዓ አላደረግኩልም እንዴ!!!"ሲሉት
ወንድሙ ያዕቁብ እንደቀደመው እና ዱዓውንም ሸውዶ እንደተቀበለ በመረዳት
ሀይለኛ እልህ ያዘው።
ዒስ አባታቸው ኢስሀቅ ከሞተ ያዕቁብን እንደሚገድለውም ይዝትበት
ጀመር።ያን ግዜ አባት ለልጃቸው ዒስ ማስተዛዘኛ ይሆም ዘንድ፦"አላህ
ዝርያዎችህን ጠንካሮች ያድርጋቸው፣ፍራፍሬዎችን እና ሪዝቆቹንም አላህ ሰፋ
አድርጎ ይስጥህ" በማለት ዱዓ አደረጉለት።
ነገር ግን እናት ልጇ ያዕቁብ ላይ ሚዛተው ዛቻ እረፍት ነስቷት ስለነበር የዒስ
ቁጣ እስኪበርድለት ድረስ ያዕቁብን ሀራን በሚባል አካባቢ ወደሚገኘው
ወንድሟ (ላባን) ላከችው።
ያዕቁብም ስንቁን ይዞ ወደ አጎቱ ላባን እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ መሸበት እና
አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ፏ ያለ እንቅልፍ ተኛ።
እዛው በተኛበትም በህልሙ ወደ ሰማይ መወጣጫ ይመለከታል።በዚያ
መወጣጫ መላዕክት ይወጣሉ...ይወርዳሉ።በዚያ መሀከል አላህም፦"እኔ
አንተን እባርክሀለሁ።ዝሪያዎችህንም አበዛልሀለሁ...ምድርንም ላንተ እና
ለዝርያዎችህ አደርጋታለሁ" አለው። በህልሙ ማለት ነው....
ልክ ይሄን እንዳየ ከእንቅልፉ ነቃ። ባየው ነገርም በጣሙን ተደሰተ'ና፦"ጌታዬ
አሁን ከምሄድበት በሰላም ከመለስከኝ እዚህ ቦታ ላይ ላንተ አምልኮ እሚሆን
ቤት እገነባለሁ።ከሚኖረኝም ሀብት አንድ አስረኛውን ባንተ መንገድ አውላለሁ"
በማለት እዛ ቦታ ላይ የሆነ ምልክት አድርጎ ስለት ገብቶ ጎዞውን ቀጠለ።
ብዙ ተጉዞ የሀራንን ምድር ደረሰ'ና ከአጎቱም ተገናኘ።ለአጎቱ ሁለት ሴት ልጆች
ነበሩት አንዷ (ለያ) ስትባል ታናሿ ደሞ (ራሂል) ትባላለች።
ምነው ለያ ራሂል...ስል የዩሱፍ ፊልም ትዝ አላችሁ ሀ....!!! ቆይ ዩሱፍንም
ደርሰነዋል ትንሽ ነው የቀረን።
ትንሸኛዋ ራሂል ቆንጅዬ ነገር ስትሆም ትልቋ ግን እስከዚህም ነገር
ነበረ።ከዚያም ያዕቁብ ትንሸኛዋ ራሂል በልቡ መግባቷን ሲያውቅ አጎቱን ላባንን
እንዲድረው ጠየቀው።
አጎቱም፦"7 አመት በጎችን ካገድክልኝ እድርሀለሁ" በማለት ቃል ገባለት'ና
ያዕቁብም ቆንጂዬዋን ራሂልን ለማግኘት ለ7 ተከታታይ አመታት እረኛ ሆኖ
አሳለፈ።
የማይደርስ የለም'ና ሰባቱ አመት ተጠናቅቆ የቀጠሮው ቀን ብቅ አለ።ላባንም
ድል ያለ ድግስ ደግሶ ዘመድ አዝማድ ከጠራ በኋላ ኒክህ እስሮ ሙሽሪትንም
ለያዕቁብ አስረከበው።
በማግስቱ ጠዋት ላይ ጨለማው በብርሀን መገፈፍ ሲጀ..
@yenebiyattaric
3.9K views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-11 20:56:45 ...ላ አባትህ ነኝ ብለህ
ስትመጣ መቀበሌ አንሶህ ልረድህ ትለኛለህ እንዴ!!!" አላለውም ነበር።
ነገር ግን በእናቱ መልካም ተርቢያ ያደግው የመልካም ስነምግ ባር ባለቤት
የሆነው ኢስማዒል፦"አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ፈፅም እኔንም ታጋሽ ሆኜ
ታገኘኛለህ" ነበር መልሱ።
አሁን ኢብራሂም ልጁን ሊያርድ ዝግጅቱን ጀምሯል።የኢስማዒልን እጅ ወደኋላ
አድርጎ ካሰረ በኋላ በጀርባው ካስተኛው አይኑን ሲያይ ሆዱ አይችልም'ና
በሆዱ አስተኝቶ ፊቱን ወደ መሬት በመድፋት የጌታውን ትዕዛዝ ተፈፃሚ
ሊያደርግ ቢለዋውን በልጁ ኢስማዒል አንገት ላይ ሲያሳርፍ ከወደ ላይ
በኩል፦"ኢብራሂም ሆይ !!! ህልሙን እውን አድርገሀል እኛም እንደዚህ
መልካም ሰሪዎችን እንመነዳለን" የሚል ድምፅ መጣ።
ኢብራሂምም ቀና ሲል ከሰማይ አንድ መልዐክ ለኢስማዒል ቤዛ ይሆን ዘንድ
ሙኩት ይዞ መጣ'ና፦"ኢስማዒልን ፈትተህ ይሄን እረድ" አለው።
ከዚያም ኢብራሂም ደስታው ወደር አጣ...እየተቻኮለ የልጁን...የአብራኩን
ክፋይ እጆች መፍታት ጀመረ።ከዚያም ከሰማይ የመጣለትን ሙኩት
አረደው።ያን ቀን በማስመልከት ነው እንግዲህ በየዐረፋ በአሉ የእርድ
ስነስርዐት ሙስሊሞች የምንፈፅመው።
ኢብራሂምም ወደ ሀገሩ ተመልሶ ብዙም ሳይቆይ ዳግም ሌላ ትዕዛዝ ከጌታው
በኩል መጣለት፦"ከልጅህ ጋር በመሆን ልጅህ በሚገኝባት ከተማ እኔ
ምመለክበትን ቤት(ካዕባ) ስራ" የሚል ነበር ትዕዛዙ።
ኢብራሂምም ለጌታው ታዛዥ በመሆን ወደ ልጁ ሄዶ ሲያማክረው ልጁም
መርሀባ ይለውና ማቴርያል አሰባስበው ግንባታ ጀመሩ።
ኢብራሂም እላይ ሆኖ ሲመርግ ኢስማዒል ደሞ ከታች ድንጋይ ያቀብለው
ነበር።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ፦"ጌታችን ሆይ! የምንሰራውን ተቀበለን አንተ
ሰሚም አዋቂም ነህ" በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር።
አሁን የታዘዙትን ቤት ሰርተው አጠናቀዋል ኢብራሂምም ከቤቱ ጎን በመቆም፦"
ጌታዬ ሆይ! ይህንን አገር (መካን) ጸጥተኛ አድርገው፡፡ እኔንም ልጆቼንም
ጣዖታትን ከመገዛት አርቀን።
ለእዚያ ከሽምግልና በኋላ ኢስማዒልን ኢስሐቅንም ለእኔ ለሰጠኝ አላህ
ምሰጋና ይገባው፡፡ ጌታዬ ልመናን በእርግጥ ሰሚ ነውና...
ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡
ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ።
ጌታችን ሆይ! ለእኔም ለወላጆቼም ለምእመናንም ሁሉ ምርመራ በሚደረግበት
ቀን ማር" በማለት ዱዐ አደረገ።
ይህን ትልቅ ቤትም ገንብተው ካጠናቀቁ በኋላ አላህም ኢብራሂምን፦"ሰዎች
ከየሀገሩ በመምጣት ቤቴን ይጎብኙ ዘንድ ተጣራ" አለው።
ኢብራሂምም፦"ጌታዬ እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝ ድምፄ እኮ አይደርስም"አለው።
አላህም፦"አንተ ተጣራ ማድረስ የኔ ስራ ነው" አለው።
ኢብራሂምም ትልቅ ተራራ ላይ በመውጣት ተጣራ።ያን ግዜ ከየሀገሩ ያሉ
ህዝቦች ጥሪውን በመቀበል መካ መጥተው ሞሉ። ኢብራሂምም የሀጅን
ስነስርዐት ለሁሉም አስተማራቸው።
ከዚያ በኋላ የኢብራሂም ሚስት ሳራ በከንዐን ምድር ሀብሩን በምትባል ቦታ
በ127 አመቷ ዱንያን ተሰናበተች።
ከዚያ በኋላ ኢብራሂም ለሳራ ልጅ ኢስሀቅ ሪፍቃ ቢንት በቱኢል የተባለችን
እንስት አጭቶለት አጋባው።
ከዚያም ኢብራሂምም ለራሱ ቀንጡራ የተባለችን ሴት በማግባት
1፦ዙምራን
2፦የቅሻን
3፦ማዳን
4፦መድየን
5፦ሺያቅ
6፦ሸውህ...የተባሉ ልጆችን ወለዱ።
በመጨረሻም በ200 አመቱ #ኢብራሂም ዱንያን ተሰናበት....ዐለይሂ ሰላቱ
ወሰላም
_____________________________________
የኢብራሂምን ዐ ሰ ትረካ ስንዳስስ የኢስማዒልን እና የኢስሀቅን (ዐሰ) ትንሽ
ነካ ነካ ማድረጋችን ይታወሳል።
ስለዚህ በቀጣይ በአላህ ፍቃድ የሁለቱንም ትረካዎች በማያያዝ የምናቀርብላችሁ
ይሆናል።
ምንጮቻችን፦
ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ / ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
ﺻﺤﻴﺢ ﻣﺴﻠﻢ
ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺒﺨﺎﺭﻱ

ነብዩሏህ #ኢስማኢል እና #ኢስሀቅ ታሪክ ኢንሽአላህ
ይ......ቀ.....ጥ.....ላ......ል፡፡
ሌሎች የነብያት፣ ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ
እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ
አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።
@yenebiyattaric
@yenebiyattaric
4.0K views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-11 20:36:01 #ነብዩሏህ_ኢብራሂም_እና_እስማዒል

ክፍል

እንደምትደሰት በሚገባ ካስረዳችው በኋላ ኢብራሂም ሃጀር የተባለችውን
አገልጋያቸውን አገባ።
ከእለታት አንድ ቀን ኢብራሂም ከሳራ ጋ በሚኖሩበት ድንኳን አጠገብ ሶስት
ወጣቶች ኢብራሂም እና ሳራ ቁጭ ባሉበት መጡ'ና ሰላም አሉት።እሱም
ሰላምታቸውን መለሰላቸው'ና ወሬ ሳያበዛ አንድ ሙኩት አርዶ ጠባብሶ
አቀረበላቸው። አቦ ወላሂ ይመቸው እንግዳን በወሬ ከማድረቅ በፊት ምግብ
ሲቀርብ ነው ሙድ ያለው..
ኢብራሂም ምግቡን ካቀረበ በኋላ እጃቸውን ቢያይ ቢያይ ምንም ወደ ምግቡ
አይዘረጉም።ይህን ግዜ ኢብራሂም በልቡ ፍራቻ አደረ።
ሊዘርፉኝ የመጡ ሌቦች ናቸው!!!?
ወይስ ሊገድሉኝ..!!?
ወይስ ሚስቴን ሊተናኩሉ ነው..!!? እያለ ይጨነቅ ጀመር።
ኢብራሂምም፦"ምን ፈልጋችሁ ነው እነ ማን ናችሁ?" ብሎ ጠየቃቸው።
ወጣቶቹም፦"እኛ ከሰማይ የመጣን መላዕክቶች ስንሆን ላንተ ልጅ
እንደምትወልድ ልናበስርህ እና የሉጥን ህዝቦች ልናጠፋ ነው የመጣነው"
ሲሉት
ኢብራሂም ሚያላግጡበት መስሎት በመገረም፦"ይህ እንዴት ይሆናል? እኔ እኮ
የጃጀው ሽማሌ ነኝ" አላቸው።
እነሱም፦"ይህ የጌታህ ትዕዛዝ ነው እሱ ባሻው ነገር ላይ ቻይ ነው" ብለው
መለሱለት።
ይሁን ሁሉ ንግግራቸውን ስትሰማ የነበረችው ሳራ ከት ብላ ሳቀች።
መላዕቱም ወደ ሳራ ዞሩ'ና፦"አንችም ኢስሀቅ የተባለን ነቢይ ትወልጃለሽ"
አሏት።
ሳራም በጣም በመገረም አፏን ይዛ፦"ይህ ግን እንዴት ይታሰባል ኢብራሂም
እኮ የጃጀ ሽማግሌ ሲሆን እኔም መሀን ነኝ" ስትላቸው።
መላዕክቱም ምንም እንኳን ሳራ መሀን ብትሆን እና ኢብራሂምም ሽማግሌ
ቢሆንም አላህ ልጅ በቅርቡ እንደሚሰጣቻው እና ያ ልጅም ወደፊት ነቢይ
እንደሚሆንም አክለው አረጋገጡላቸው።
እና መላዕቱም ጉዞ ወደ ሰዶማውያን ጀመሩ።(በነገራችን ላይ ሉጥ
ከኢብራሂም ከተለያየ በኋላ ሰዶም ወደተባለ ሀገር በመሄድ ዳዕዋ ማድረግ
ጀምሯል።ይህን ደሞ ነገ ምንዳስሰው ይሆናል።)
አሁን ነፍሰ ጡሯ የኢብራሂም ሁለተኛ ሚስት ወንድ ልጅን ተገላግላለች።ይህን
ግዜ በሳራ የቅናት መንፈስ ያድርባትና ኢብራሂምን የተወለደለትን አዲሱን ልጅ
እና አዲሲቷን ሚስቱን ራቅ ወዳለ በረሀ ጥሏቸው እንዲመጣ አዘዘችው።
ኢብራሂምም ሚስቱን ሀጀርን እና ልጁን ኢስማዒልን ይዞ ጉዞ ወደ በረሀ
ጀመረ።ብዙ ከተጓዙ በኋላም በዐረብያ ምድር ምንም ውሀም ይሁን አረንጓዴ
ነገር ከሌለበት አንድ ተራ ደረሱ።
የያዘውንም ስንቅ አስቀምጦላቻው ኢብራሂም ወደ መጣበት ሲመለስ ሚስቱ
ሀጀር፦'በዚህ በረሀ ትተኸን እየሄድክ ነው? ወይስ አላህ አዞሀል?" አለችው
እሱም፦"አዎ" ብሏት ጉዞ ቀጠለ።
ትንሽ ሄድ አለ'ና፦"ጌታችን ሆይ! እኔ አዝመራ በሌለው ሸለቆ ውስጥ
በተከበረው ቤት አጠገብ ከዘሮቼ አስቀመጥኩ፡፡ ጌታችን ሆይ! ሶላትን
ያቋቁሙ ዘንድ (አስቀመጥኳቸው)፡፡ ከሰዎችም ልቦችን ወደእነሱ የሚናፍቁ
አድርግ፡፡ ያመሰግኑህም ዘንድ ከፍሬዎች ስጣቸው፡፡" ብሎ ዱዓ አደረገ'ና
ወደመጣበት ለመመለስ ጉዞ ጀመረ።
ብዙ ተጉዞ ሚስቱ ሳራ ወዳለችበት አካባቢም ሲደርስ ሚስቱ ወንድ ልጅ ታቅፋ
አገኛት በጣምም ተደሰተ።
ያችኛዋ ሚስቱ ምንም እንኳን አየሩ ለመቋቋም በሚያዳግት መልኩ ሞቃታማ
ቢሆንም የያዘችውም ውሀ ቢያልቅም በህይወት ግን ከልጇ ጋር እስካሁን
አለች። ውሀ ጥም አንገብግቧታል... ምንም የቀመሰችው ነገር ባለመኖሩ ልጇ
ከጡቷ ምንም ሊያገኝ አልቻለም።
ህፃኑ ኢስማዒል ረሀቡን መቋቋም አቅቶት በጣም እያመረረ ማልቀስ
ጀምሯል...ሀጀርም ምን ማድረግ እንዳለባት ግራ ገብቷት ትተክዛለች።
አየሩ በጣም ሞቀታማ ነው፣ፀሀይዋ ሙሉ ብርታቷን በዛ ምድር ምታሳርፍ ነው
ሚመስለው...መሬቱ ግሏል...ነገር ግን ምንም አማራጭ የላትምና ውሀ
ፍለጋ ልጇን አስቀምጣ በበረሀው ለመሯሯጥ ወሰነች።
ከብዙ ፍለጋ በኋላ ውሀ ልታገኝ ባለመቻሏ ያለ ውሀ ህፃኗ ጋር መመለስ
አልፈለገችም'ና ከአንዱ ተራራ ወደ አንዱ ስትሸጋገር ሰፋ እና መርዋ በተባሉ
ሁለት ተራራዎች ዘንድ ደረሰች በመሀከላቸው ትልቅ ሸለቆ አለ።
ከዚያ ሀጀር ውሀ ይኖራል ብላ እየሮጠች ወደ ሰፋ ተራራ ወጣች ምንም
የለም።
አሁንም ወደ ሸለቆው ወርዳ ወደ መርዋ ተራራ እየሮጠች ወጣች ነገር ግን
አይደለም ውሀ ይቅርና እርጥበት እንኳን የለም።
በዚህ ሁኔታ ከሰፋ ተራራ ወደ መርዋ ተራራ ለ7 ግዜ ውሀ ፍለጋ በሩጫ
ተመላለሰች።
አሁን ሀጀር ድካሟን መቋቋም ባማትችለው ሁኔታ ላይ ደርሳለች፣ጉሮሮዋ
ደርቋል፣ ዳግም ውሀ ፍለጋ ተራራዎችን መውጣት ተሳናት።
ከዚህ በላይ ከቆየች ልጇ እንዳይሞትባት ስለሰጋች ልጇን ወዳስቀመጠችበት
ድንኳን አቀናች።ልክ ህፃኑ ጋር ስትደርስ ህፃኑ እያለቀሰ ሲፈራገጥ በእግሩ
መሬቱን ሲደበድብ ከመሬቱ ውሀ ሲወጣ ተመለከተች።
ደስታዋ ወደር አጣ ውሀውን ጠጥታ ልጇን አጥብታ ለጌታው ምስጋናዋን
አደረሰች።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለች መንገደኛ ነጋዴዎች በውሀ ጥም ተቃጥለው
ያንን በረሀ ሲያቋርጡ ይህን ምንጭ ይመለከቱ'ና ሀጀርን አንድ ግዜ ከፍለዋት
ሊጠጡ ለመኗት።
እሷም ከውሀው ፈቅዳላቸው በአፀፋው ተምር ተቀበለቻቸው.....እነሱም
ጠጥተው አለፉ
እንዲህ እንዲህ እያለ በውሀ ችግር የሚታወቀው የዐረብያ ምድር በሀጀር
ምንጭ ወሬው ተጥለቀለቀ የተለያዩ የዐረብ ነገዶችም ከሀጀር አቅራቢያ
እየሰፈሩ ግንባታዎችን መገንባት ጀመሩ።
ከረጅም ግዜ በኋላም ኢብራሂም ልጁን ኢስማዒልን እና ሚስቱን ሀጀርን ከምን
እንደደረሱ ለማጣራት ያስቀመጣቸው ቦታ ሲመጣ ቦታውን ሊያውቅ
አልቻለም።
ምክንያቱም ያኔ ሲመጣ አከባቢው ምንም አይነት ነፍስ ያለው ነገር
የማይኖርበት ምድረ በዳ ነበር።አሁን ግን ቤቶች ተገንብተዋል...የብዙ ተጓዥ
ነጋዴዎችም ማረፊያ ከተማ ሆኗል።
ይህን ሲያይ መንገድ ተሳስቼ ይሁን እያለ ያሰላስል ጀመር።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ
የአከባቢውን ሰው ሀጀር ስለምትባል ሴት ሲጠይቁት ከነ ቤቷ ጠቆሙት።
ኢብራሂምም ቤቷ ሲሄድ በጥሩ ሁኔታ ላይ ከልጇ ጋር ተመለከታት...እንባ
ተናነቀው...ሁለቱንም ለረጅም ሰዐት አቀፏቸው ያለቅስም ጀመር።
ከዚያ በዚህ ሁኔታ ከተገናኙ በኋላ ኢብራሂም ወደ መጣበት ተመለሰ።ምንም
እንኳን የልጁ ኢስማዒል እና የሚስቱ ፍቅር እንደ አዲስ በውስጡ ማንሰራራት
ቢጀምርም በመሀከላቸው ካለው ርቀት አንፃር በፈለገ ሰዐት እየመጣ
ሊዘይራቸው ምቹ አልነበረም'ና ሁሌ በአመት አመት ሊያያቸው መምጣት
ጀምሯል።
ከእለታት አንድ ቀን ኢብራሂም ተኝቶ ሳለ በህልሙ፦"ኢብራሂም ሆይ! አላህ
ልጅን ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ ሰማ'ና ደንግጦ ተነሳ።
ከዚያም፦"ጌታዬ ኢስማዒልን እንዳርደው ምትፈልግ እንደሆን ታዛዥህ ነኝ"
ብሎ ተመልሶ ተኛ።
አሁንም እንቅልፍ ትንሽ ሸለብ እንዳደረገው፦"ኢብራሂም ሆይ! አላህ ልጅህ
ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ በህልሙ ተሰማው። አሁንም
ደንግጦ ተነሳ'ና ረክዐተይን ሰግዶ አላህ ትዕዛዙን ግልፅ እንዲያደርግለት ዱዓ
አድርጎ ተመልሶ ተኛ።
አሁንም ልክ እንደተኛ ለሶተኛ ግዜ፦" ኢብራሂም ሆይ! አላህ ልጅህ
ኢስማዒልን እንድታርደው አዞሀል" የሚል ድምፅ ሲሰማ ኢብራሂም ለጌታው
ታዛዥ ሆኖ ከተኛበት ተነሳ።የጌታው ትዕዛዝ ምንም እንኳን ለህሊና ሚከብድ
ቢሆንም ኢብራሂም ሊፈፅም ወሰነ።
ኢብራሂምም ትዕዛዙን ሊፈፅም ጉዞ ኢስማዒል እና ሀጀር ወደሚገኙባት ቅድስት
ከተማ መካ ሄደ።ልክ እንደደረስ ኢስማዒልን ብቻውን ሊያናግረው ወጣ
አድርጎ፦"ልጄ አንተን እንዳርድህ ጌታዬ አዞኛል ምን ትላለህ!?" አለው።
ኢስማዒል፦"ዞር በል ከዚህ..
ስንት አመት ጥለኸኝ የትም የትም ብዬ ካደግኩ በኋ...
3.3K views17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ