Get Mystery Box with random crypto!

ግጥም እና ታሪክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yena_tarikoce — ግጥም እና ታሪክ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yena_tarikoce — ግጥም እና ታሪክ
የሰርጥ አድራሻ: @yena_tarikoce
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 655

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-01-09 18:59:56 ​​ ሳፈቅርሽ ኖራለው

የትም ብትሆኚ ከአጠገቤም እሩቅ
አፍቃሪሽ ልቤ ነው መውደዱ የማያልቅ
ብትጠይኝ ብትወጂኝ መውደዴ አይቀንስ
አንቺን ገና ሳይሽ መንፈሴ የሚታደስ
ፍቅር ትሩፋቴ መላ እንነቴ
ያንቺው ነው ብያለው ተረጂልኝ እቴ

የልቤ ምት እንኳን ስላንቺ ሲመቱ
ብታዳምጪልኝ ምን ነበረ እቱ!

የመውደዴን ምላሽ ካንቺ ሳልጠብቀው
ባታፈቅሪኝ እንኳን ሳፈቅርሽ ኖራለው።

my( Letarik)
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
127 viewsLetarik, 15:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 20:55:08 እርምሽን አውጪ

አይታወቅ ብዬ የወንድ ብራንባሩ
ድንግል ነኝ እያልኩኝ ለሀገር ለምድሩ
ያቺም ስትመጣ የመጀመሪያዬ
አንቺም ስትመጪ የመጀመሪያዬ
ለዚችም ለዛችም የመጀመሪያዬ
ምናምን ምናምን ሰው ስወድ አምርሬ
እያልኩኝ መሸንገል መዋሸት አስሬ
ለራሴው ሰለቸኝ ልነግርሽ ነው ዛሬ
በይ እርምሽን አውጪ
                 እንዳይከፋሽ ፍቅሬ
አስራ ስምንተኛዬ ነው
                  ሰው ስወድ አምርሬ።                        

My( Letarik)
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
177 viewsLetarik, 17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 03:15:15 https://youtube.com/shorts/76eihsyENmw?feature=share
Subscrubers pless my best member
38 viewsLij Wonda, 00:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-15 13:28:54 የምናፈቅረውን ሰው በጃችን የማስገባት ጥበብ

ክፍል

. እንክብካቤ አብዛባት፡፡

. ቀልድ አታብዛ ያለበለዝያ እንደ ወንድሟ ነው ምታይህ፡፡ ሁሌም ቁም ነገረኛ ሁኚ ሁን፡፡

. እሳ ከጠራችህ ወይም ከጠራችህ ምንም አይነት ጉዳይ ውስጥ ብትሆንም ሂድ ምክንያቱም ለሷ ትልቅ ቦታ እንዳለህ ማሰብ ትጀምራለች ስለዚህ ሁሉም ነገር መስመሩን ያዘልህ ማለት ነው፡፡

. ፍቅርህን ስገልፅ እባክህ ከፊልም ላይ ያለውን ወይም የሰማህውን የማማለያ ቃላት አትጠቀም ሁሌም አንተ የቃላት ፈጣሪ ሁን እንጂ የተለመዱ ቃላቶች አትጠቀም ምክንያቱም በልቧ ጥርጣሬ ያድራል አውቆ ነው ብላ ታስባለች፡፡

. ከንፈርዎን የምስመው የመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ እባክህ እባክህ ባከባቢው ፍፁም ሰው እንዳይኖር ምክንያቱም ሰው ካለ ታፍራለች ሌላ ጊዜም የምደግመው ስለሚመስላት ካንተ ጋ የምትገናኙበት ቀን ይቀንሳል በዛ ላይ ሰው ካለ ልትገረጣ ትችላለህ ስለዚህ ሰው በሌለበት ቦታ ሳታስበው ሳማት የምር ነው ምልህ እውነት ቤቷ ገብታ ካንተ ውጭ ማንም አይምሮዎ ላይ አይመጣም፡፡ ምን አለ በለኝ በህልሟ ሁሉ ልመጣ ትችላለህ፡፡

. ማታ ላይ ስስማት የተሰማህን ስሜት በሚገርም ቋንቋ(ጅንጀና ቢጤ) ፅፈህ በ Text ልከህ መጨረሻው ሰላም እደሪልኝ ብለህ ላክ፡፡ hahaaha ታድለህ እሄንን ካረክ እውነት እንቅልፍ እስከሚወስዳት ስታስብህ ስትደሰት ነው የምታመሸው፡፡እረ ወላሁላ በቃ ፊልም ላይ እንደሚሆኑት ፍቅረኛሞች የሆነች መስሎዎት ይሰማትና ክላስ(ት.ቤት) ቁጭ ብላ የስኪርብቶዎን ጫፍ ነከስ ነሰስ እያረገች አንተን ማሰብ ልጀምር ሁሉ ትችላለች፡፡ ( henok )

ይቀጥላል...

ይቀጥል የምትሉ እስኪ የ ምልክቱን በመንካት ድጋፋችሁን ስጡን፡፡

JOIN & SHARE
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
1.7K viewsLij Wonda, 10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-14 08:04:00 የምናፈቅረውን ሰው በጃችን የማስገባት ጥበብ
ክፍል

. ሁሌም ያማረ አለባበስ መከተል ማለትም ያሉንን ልብሶች ሁሌም ፅዱ ማረግ(Protocol)

. ሁሌም ጠዎት የሰላምታ Text መላክ፡፡ ከዛ ስናስለምደው ከወራቶች ቡሀላ ማቆም ከዛ ስለንተ ስላንቺ መጨነቅ ጀመረ ጀመረች ማለት ነው፡፡

. ቢያንስ በሳምንት አንድ ጊዜ ወክ ማረግ መናፈሻወችን ማስለመድ፡፡

. ሁሌም ስትገናኝ አንድ አይነት ሰላምታ ማስለመድ አሁንም ከሳምንታት ቡሀላ ስስማት ወይም ስስሚው ለየት ያለ አሳሳም ከዛ እንዳፈቀርካት/ሽው አወቀለሽ አወቀችልህ ማለት ነው፡፡

. ስልክ ማውራት አስፈላጊ ከሆነ ሁሌም ማታ ማታ ማድረግ ምክንያቱም ማታ ላይ ምንም የሚረብሽ ወይም የሚያስጨንቅ ነገር የለም ጉዳይም የለባትም ስለዚህ በምታዎራት ሠአት ሀሳብህን ትረዳለች ስልኩ ከተዘጋ ቡሀላ እናቴ ትሙት ነው ምልህ ስላንተ ማሰብ ትጀምራለች፡፡

. የኛን ቻናል በጥሞና መከታተል ምክንያቱም እናስተምርሀለን እና አንተ ደግሞ በተግባር ታሳያታለህ፡፡ ለጉዎደኛህ ምታስብ ከሆነ በል የፍቅር ግዜን join አስደርግ

ይቀጥላል.... ክፍል

ይቀጥል የምትሉ እስኪ የ ምልክቱን በመንካት ድጋፋችሁን ስጡን፡፡

JOIN & SHARE
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
1.4K viewsLij Wonda, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-14 07:57:08 ... ትመስክር ጨረቃ!

እንዴት እንደምወድሽ ትናገር ጨረቃ
ጠብቀሽ ጠይቂያት ስትወጣ ደምቃ

የሆዴን ሁሉ አንዳችም ሳልደብቅ
አዋያት ነበረ ጠብቂአት በድብቅ

እሷም አታሳፍር ታዳምጠኛለች
ከክዋክብት ጋራ ተገርማ እያየች

ደመናው አይሎ እንዲያው የቀረች ቀን
አይሻልም ምሽቱ ከ ልቤ ሰቀቀን

አሁን አሁንማ........
ክረምቱም ደረሰ ደመናው አየለ
የእኔ ና የእሷም ነገር ከንግዲህ ተለየ

እንዲው ግን ሰሞኑን አንዳች ግር ብሎኛል
ላንቺ ከነበረኝ ፍቅር ግን የሷ በልጥብኛል።

Join Share
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
1.2K viewsLij Wonda, edited  04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 15:31:07 ሳቂታዋ ዝሙት አዳሪ

ክፍል 9

የእናቱ ልጅ
.
.
#የመጨረሻ ክፍል!!
.
.
ወዳሻት ነዳችው፡፡ ከሷ ጋር ሆኜ ለምን ወደ ሞት አትወስደኝም ከመሄድ አልመለስም፡፡ አንድ ግቢ ጋር ስትደርስ ወረደች፡፡ በሩን ከፈተች፡፡ መኪናዋን አስገባች፡፡ መልሳ ግቢውን ዘግታ አጠገቤ መሪዋን ይዛ ተቀመጠች፡፡

"ስማ ከእንግዲህ ግን እንደዚህ እያጎደልከኝ እንድትሄድ
አልፈቅድልህም፡፡ የማትታዘበኝ ከሆነና ሴተኛ አዳሪነቴን ካልተጠየፍከኝ ከዚህም በላይ ብትቀርበኝ ደስ ይለኛል ።" "እሽሽሽሸ እንደዚህ አትናገሪ ፡፡
አንቺ በጣም ምርጧና ልዩ ሴት ነሽ" "ልሳምህ...?" ቀድሜ ከንፈሯ ላይ
ተጣበቅኩባት፡፡ ጎትታ ከመሪው ጋር እየተጋጨች ላዬ ላይ ተቀመጣ ከልብ
ተሳሳምን፡፡ የጡት ማስያዣዋንና ከላይ የለበሰችውን ሽቅብ ጎትታ ትላልቅ
ጡቶቿን አፌ ላይ ደቀነቻቸው፡፡ሳምኳቸው...ጠባኋቸው..ጫን ጫን
አደረግኳቸው፡፡ ሁሉ ነገሯ ፍቅር ነው፡፡እጆቿ አያርፉም፡፡ ከንፈሯ ከንፈሮቼን
አይለቁም፡፡ ሱሪዬ ውስጥ ገብታ በእጇ ጨብጣ ያዘችው፡፡ ሁለታችንም
አቅላችንን ስተን ሌላ ደስ የሚል የሚያቃጥል አለም ውስጥ ገባን፡፡
ሁለመናዋን ሳምኳት፡፡ ንጹህ እና ትኩስ ናት፡፡ የለበሰችው አጭር ቀሚስ
በመታገል ተተረተረ፡፡ የውስጥ ሱሪዋን እስከምታወልቅ ትግስት
አልነበረኝም፡፡ ፓንቷን ወደ ጎን ሰብሰብ አድርጌ ስይዝላት በቀስታ
ተቀመጠችብኝ፡፡ የሚገርም ወሲብ አደረግን፡፡ ሁለታችንም የለየለት
እብደት ውስጥ ገብተን ተዋሰብን፡፡ አንገቴ ላይ ተጠምጥማ ከመኪናው
ኮርኒስ ጋር እየተጋጨች ጋለበችኝ፡፡ እኔም በሚገባ ናጥኳት፡፡ ሁለታችንም
የመጨረሻው የእርካታ ጫፍ ላይ ስንደርስ ተንዘርዝራ በላብ ተጠምቃ
አንገቴ ስር ተሸጎጠች፡፡ እቅፍቅፍ ብለን መርፌና ክር እንደሆንን
ቆየን፡፡ ደግመን ጣፋጭ ወሲብ ሰራን፡፡የምትጠገብ አይደለችም፡፡
ስንጨርስ እንደመጀመሪያው አንገቴ ስር ተሸጎጠች፡፡ ቀና ብላ ልታየኝ
አልደፈረችም፡፡ ፊቷን በሁለት እጆቼ ይዤ ቀና አድርጌ ከንፈሯን በፍቅር
ሳምኳት፡፡ ያስቃል አይደል ግን ቢታኒያም ተሽኮረመመች፡፡ ተመልሳ አንገቴ ስር ተደበቀች፡፡
"ታዉቃለህ
እንደዚህ አንገትህ ስር እንደተሸጎጥኩ ብቀር ብዬ ተመኘሁ፡፡ ከአንገትህ
ከወጣሁ የምትሄድብኝ መሰለኝ፡፡ትተወኛለህ...?" አለችኝ
"ወድጄሻለሁ፡፡ ጠብ
የሚል ነገር የሌለኝ የመንግስት ሰራተኛ ነኝ፡፡ ምናልባት የምሰጥሽ ነገር
አይኖር ይሆናል፡፡ራሴን ግን በፈለግሽው ልክ እንድትወስጂው ልሰጥሽ
እችላለሁ" አጥብቃ እቅፍ አደረገችኝ፡፡በተናገርኩት ደስ ያላት መሰለኝ፡፡
ጡቶቿን መሸፈን ስጀምር "እንቢዬዉ አትሸፍነኝ! አሁን መነሳት አልፈልግም..እንዳትነቅለዉ ዋ! እንዲሁ እንደሆንን መቆየት ነው የምፈልገው"አለችኝ፡፡
እንደዛው ተጣብቀን መኪና ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ወሰብን፡፡
"ወድጄሃለሁ አጠገቤ ትሆናለህ...?አትሄድብኝም...?" ዝም ብላ ትጠይቀኛለች እንጂ እኔም ከሷ
የመሄዱ ጉልበት የለኝም፡፡
"ከፈለግክ ነገ መዘጋጃ ሄደን አገባሀለሁ፡፡እንቆይ ካልክም የፈለገህን ጊዜ እጠብቃለሁ" ሳታቋርጥ ታወራለች... "ስማ ለሳምንታት ሳስብህ ነበር፡፡ ደግመን የምንገናኝ ስላልመሰለኝ ስጸጸት ነበር የሰነበትኩት፡፡ ከንፈርህን እንኳን ሳልስምህ ስትሄድ 'ቢታንያ ምን አይነቷ
ደደብ ነሽ' ብዬ ራሴን ስሰድብ ነበር የሰነበትኩት፡፡ አሁን ግን ውስጤን
አይተሃል፡፡ በድተኸኛል፡፡ ተነስቶ መሄድ የለም!!" በፍቅር እያየችኝ ቀጠለች
"ታሪኬን አውቀሃል፡፡ እንዳንተ ዘርዝሬ ስለራሴ የነገርኩት ሰው ኖሮ
አያዉቅም፡፡ ሰምቶኝም የሚያዉቅ ሰዉ ስላልነበረ ይሆናል ። ገመናዬን አውቀሃል፡፡ሀጥያቴን ተናዝዤልሃለሁ፡፡ እምሴንም
አይተሃል፡፡ ነግሬህ አልነበር ባለ ሁለት አንቴና እንደሆንኩ...? አየኸው...?
ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ"
ሳምምምም አደረግኳት፡፡ "አየሁሽ፡፡ እናም አስር አመት..ሀያ አመት አብረሽኝ የኖርሽ ሚስቴ እንደሆንሽ ነው እየተሰማኝ ያለው፡፡...መረብሽ በአሁኑ ያጠመደው መናጢ ደሀ ነው፡፡ ግን ህይወቱንም ሳይሰስት እንደሚሰጥሽ ቃል እገባለሁ ።"
መልሳ አላወራችም...አልጠየቀችኝምም ከንፈሬን ጎረሰችዉ ። በከንፈሯ አገባችኝ ..በስስት ተቀበልኳት ። ተሳሰርን.. በቶሎ ሳትለቀኝ እየተስለመለመች ሳመችኝ ። በከናፍርቶቿ ሁሉንም አወራችልኝ ። ሁሉ ነገሯን ሰጠችኝ ። ሁሉ ነገሬን ሰጠኋት ።

//ከአራት አመት በኋላ...//

ከዚህ በኋላ የማጫውታችሁ ስለ ሁለት ልጆቼ እናት ቢታንያ ነው፡፡ የባልና ሚስት ገመና ስለማይነገር ከዚህ በኋላ ብልግና
አይኖርም፡፡ በርግጥ ሙቀቱ ልፊያው መዳራቱ ተጠናክሮ ቀጥሎ አልጋ
የምንቀይረው በየአመቱ ነው፡፡ አልጋችን የሚወርድበትን መአት መገመት
ይቻላል፡፡ ብዙ አኗኗራችን ሰክኖ ቀጥሏል፡፡ ጠዋት እንነሳለን ቤተክርስትያን እንሄዳለን ፤ እንፀልያለን ። አሜን አሜን እንላለን፡፡ በፍቅር ተሞልተን አብረን ቁርስ
እንመገባለን፡፡ ወደ ስራ እንሄዳለን ፡፡
የኔ ውብ ሚስት ብቻ አይደለችም፡፡
እናት ፣ ጓደኛ ናት ። እህት ሆነችኝ ፡፡ ሁለት ራሷን የመሳሰሉ ሴት ልጆችን ወልዳ ትርጉም ያልነበረውን ህይወቴን አጣፈጠችልኝ ፡፡ አንደኛዋን ልጃችንን ራቤላ አለቻት፡፡ ሁለተኛዋን ደግሞ ሳራቤል ብላ ሰየመቻት ፡፡
ተመልከቱ ልጆቿን በጠራቻቸው ቁጥር ከአፏ እንዳልርቅ የስማቸው መሰረት አደረገችኝ፡፡ በሁለቱም ልጆቻችን ስም የኔን ስም አድምቃ ጻፈች ፡፡
ጣእም ከሌለው ኑሮ ወደ ብሩክ ህይወት አመጣችኝ ፡፡ ስቆ የማያውቀውን
ሮቤልን ደምስሳ በጽኑ የሚደሰት ሳቂታ ሰው አደረገችኝ፡፡ 'ሃሃሃሃሃሃ' ቤታችን
በሳቅ የተሞላ ነው፡፡ አፈቅራታለሁ፡፡ አሁን በጣም ደስተኛና የራሴ ቤተሰብ
ያለኝ ሰዉ ሆኛለሁ፡፡ እድለኛ ነኝ ብዬም አስባለሁ፡፡ ሊፍት ሰጥታኝ ህይወቴን
የቀየረችው እድለኛ ስለሆንኩ ይመስለኛል፡፡ እንደ ቤተሰብ ቆንጆ ህይወትን እየመራን ነዉ ። የማፈቅራት ሴት እና የምወዳቸዉ ልጆች ከጎኔ ቅርቤ ናቸዉ ። የኔዋ ዉብ ዘመናዊ የሴት ፋሽን ልብሶችን መሸጫ የንግድ ሱቅ ከፍታለች ። ከተለያዩ የአዉሮፓ ሃገራት ፋሽን ልብሶችን እያስመጣች ስኬታማ የንግዱ ሰዉ ሁናልኛለች ። እኔም በዚህቺዉ ሳቂታዋ ሚስቴ አጋዥነት ማስተርሴን ጀምሬ ወደ መጨረሻዉ ተቃርቤያለሁ ። እቺ ሴት የማንዶከድከዉን የማይጣፍጥ ሽሮዬን አይደለም የቀየረችዉ.. ማንደክደክ ለምዶብኝ አሁንም ካለ ሽሮ አይሆንልኝም ። እቺ ሴት ህይወቴን ነዉ በቅፅበታት የለወጠችዉ ። የኔ ቢታኒያ ጭምትነቴን በሳቅ ቀየረችልኝ ። ከእሷ ተጋብቶኝ በወሬዬ መጨረሻ ሁላ ሳቅ አክላለሁ ። "ሃሃሃሃሃሃሃ"
ክብር በማይመጥናቸው ቦታ
ላይ ሆነው በብቸኝነት ለሚማቅቁ ሰዎች!! አንድም ሴት ተቸግራ ዝሙት አዳሪ መሆን የለባትም !!
.
.
.
// ተፈጸመ //
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce

#ዝሙት (ሴተኛ) አዳሪዎችን አናግላቸዉ ...በሩቁ አንመልከታቸዉ .. ከዛ ይልቅ እንሞክር .. ልንረዳቸዉ እንሞክር ..ልናቀርባቸዉ እንሞክር ...እነሱም የማህበረሰባችን አካል ናቸዉ ። አዉጥተን አንወርዉራቸዉ ።.."ጣት ገማ ተብሎ ተቆርጦ አይጣልም" ይባላል ። እነሱም አካላችን ናቸዉ ። እዚህ ህይወት ስለገቡ አንርሳቸዉ ። ከዚህ ህይወት ዉስጥ ለማዉጣት መንገዱን እንጥረግላቸዉ ። ቀላል ነዉ..
1.2K views12:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-02 13:31:51 ሳቂታዋ ዝሙት አዳሪ

ክፍል 8

የእናቱ ልጅ
.
.
#ሊጠናቀቅ 1 ክፍል ብቻ ቀርቶታል!!
.
.
ለአመታት አብራኝ ኖራ የተለየችኝ ያህል ምሬት ተሰማኝ፡፡እያንዳንዷን እርምጃ
ስራመድ ደግሜ የማላገኛት መሆኔ እየታወሰኝ አዘንኩ፡፡ የሆነ ነገሬ እሷ ጋር
ቀርቷል፡፡ ባዶ ሆኛለሁ፡፡ መጠጥ አብዝቼ መጠጣቴ ጠቅሞኝ እንጂ ከአጠገቧ
ለመራቅ ድፍረቱም አይኖረኝም ነበር፡፡ አይ ሰው ሃሃሃሃሃ ሳቅኩኝ፡፡ ከእንግዲህ እኔ
ጋር የቀረው ሳቋ ብቻ ነው ፡፡
አስፓልቱን ጨርሼ ወደ ሰፈሬ የሚያስገባውን ኮብልስቶን ይዤ በጨለማው
እየተደናበርኩ ወደ ፊት ቀጠልኩ፡፡ በቃ አላገኛትም ቲሽ! ተበሳጨሁ፡፡ ለምን
ሰማኀት ..?ለምን በአንዴ ወድጃት ቀረሁ..? ለምን ስልካችንን እንዳንለዋወጥ ህግ
ስታወጣ ተስማማሁ..? ለምን አብራኝ እንድትቆይ ለመጠየቅ ድፍረቱን አጣሁ..?
ለምን ዞሬ ሳላያት አቅፌ ሳልሰናበታት ተለየኋት..?
በድን ሰውነቴን እየጎተትኩ ከፍራሼ ላይ ወጣሁ ፡፡ በማየው ነገር ሁሉ እየታየችኝ
ስቸገር መብራቱን አጠፋሁ፡፡ ሃሃሃሃሃሃ ደሞ በሳቋ መጣች፡፡ 'ኦ ቢታንያ እስከመቼ
ዙሪያየን ከበሽኝ ትቆይ ይሆን...?'
ወደተለማመድኩት ድህነት ተመልሼ በቀን ሶስቴ ሽሮዬን እያንደከደኩ ኪስ
በማያሞቅ ደሞዝ የመንግስት ባሪያ ሆኜ መስራቴን ቀጥያለሁ፡፡ ያቺ አንድ ቀን
በህይወቴ ብቅ ብላ ሌላ አለም ያሳየችኝ ልጅ የለችም፡፡ እሷን ካገኘሁ በኋላ
የምኖረው የመጨረሻው የድህነት አዘግጥ ውስጥ መሆኑ ታየኝ፡፡ እንዴት ከዚህ
አዙሪት መውጣት እንዳለብኝ አላውቅም፡፡ግን የግድ መለወጥ እንደ ሰው መኖር
አለብኝ፡፡

ሳምንት አለፈኝ ግን አልረሳኋትም፡፡ ሳቋ ዘወትር በጆሮዬ ያቃጭላል፡፡ አንዳንድ ሰው
ባጋጣሚ በህይወትህ ይከሰትና ጨለማ የነበረውን ህይወትህን በብርሃን ወገግ
አድርጎት ይሄዳል፡፡ ችግሩ ብቻህን ስትቀር የጨለማው ብርታት ማየሉ ነው፡፡
ሁለት ሳምንት አለፈኝ፡፡ ውስጤ ተስላ ስለቀረች በየደቂቃው አስባታለሁ፡፡ ድምጿ
ቅርብ ፈገግታዋ አጠገቤ ያለ ይመስለኛል..

ሶስተኛው ሳምንትም አለፈ፡፡ በጣም ናፍቃኛለች፡፡ እድሌን መጠቀም አቅቶኝ የገፋኋት
ራሴው ነኝ፡፡ በጣም ከፍቶኛል፡፡ ደግሜ ማግኘት የማልችለውን ነገር አሳይታኝ
ህይወቴ ጣእም የሌለው እንዲሆን አድርጋኛለች፡፡ስለዚህም እረፍት ማድረግና
ወደ ቀደመው አቋሜ መመለስ አለብኝ፡፡የሚያዛልቀኝ የተጋባሁት ድህነቴ ነው፡፡
በወሩ የአንድ ሳምንት እረፍት ሞልቼ ከስራ ወጣሁ፡፡ ሳምንቱን ለማሳለፍ ደብረ
ብርሃን ለመሄድ ነው ያሰብኩት፡፡ አንድ ሁለት ቅያሪ ልብሶች ይዤ ከመስሪያ ቤቴ
ወደ አውቶብስ ተራ ለመሄድ ታክሲ ስጠብቅ
"ኧረ ስለ ሴት ልጅ አምላክ ሃሃሃሃሃሃሃ" የሚል ድምፅ ከጆሮዬ ገባ ።

የተሰማኝን ስሜት በቃላት መግለጽ ይከብዳል፡፡ ራሷ ናት ቢታንያ!! ቦርሳዬን
እያንጀላጀልኩ ስሮጥ መኪናዋ ጋር ደረስኩ፡፡ ከመኪናዋ ወጣች አቀፍኳት!!ወደራሴ አስጠግቼ በሀይል አጥብቄ አቀፍኳት ፡፡
"ከአንተ ማምለጥ አይቻልም፡፡ በጣም ነበርኮ የናፈቅከኝ" አይኖቿ ረጠቡ፡፡
"ለምን ዞረህ እንኳን ሳታየኝ ሄድክ...?የጠላኸኝ የተጸየፍከኝ ነበር የመሰለኝ፡፡
በሽርሙጥናዬ ያፈርክብኝ.. እንደ እብድ የቆጠርከኝ ነበር የመሰለኝ ።"
"ትእዛዝሽን መጣስ ከበደኝ፡፡ ደግመሽ ልታገኝኝ ያልፈለግሽ መሰለኝ እንጂ እኔማ
እየከፋኝ ነበር የሄድኩት ።"
ደረቴን እየቀጠቀጠች አነባች ፡፡አልተከላከልኩም ተደበደብኩላት፡፡ እጆቼን ይዛ እየመራችኝ መኪናዋ ውስጥ ገባን፡፡

"እንዴት አገኘሽኝ ..?" አልኳት
"በቅድሚያ ምሳ የበላንበት ካፌ ነበር የሄድከዉ..በጠዋት ምን ትሰራለህ .. እዛ የምታገኘኝ መስሎህ ነዉ..? ሃሃሃሃሃ "
"ጅል ሆንኩብሻ .. አነሆለልሽኝኮ..ካልተሳሳትኩ ግን አንቺም በዛዉ አከባቢ ነበርሽ...እዛ ምታገኚኝ መስሎሽ ነዉ ..? ሃሃሃሃሃሃ " ሳቋን ሳቅኩላት...
"ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ" የናፈቀኝ ተንከትካች ሳቋ
ተመለሰልኝ ። ነፍሴ ስትረጋጋ ተሰማኝ ። ወዳሻት ነዳችው፡፡ ከሷ ጋር ሆኜ ለምን ወደ ሞት አትወስደኝም ከመሄድ አልመለስም፡፡ አንድ ግቢ ጋር ስትደርስ ወረደች፡፡ በሩን
ከፈተች፡፡ መኪናዋን አስገባች፡፡ መልሳ ግቢውን ዘግታ አጠገቤ መሪዋን ይዛ
ተቀመጠች፡፡

ይቀጥላል....
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
#ሊጠናቀቅ 1 ክፍል ብቻ ይቀረዋል !!
1.1K views10:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-22 13:18:46 ሳቂታዋ ዝሙት አዳሪ

ክፍል 7

የእናቱ ልጅ
.
.
.
"ወንድሜ አጸያፊውን ድህነት መቋቋም አቅቶት ወደ ሱዳን ጥሎኝ ሲሰደድ
ራሴን ጥልቅ ድህነትና ብቸኝነት ውስጥ ሰጥሜ አገኘሁት፡፡ለሶስት ቀናት
ከተኛሁበት ፍራሽ ሳልነሳ ራሴን ትራስ ውስጥ ወሽቄ አለቀስኩ፡፡በሶስተኛው ቀን
ግን ርሃብና ድካሙ ከተኛሁበት አስነሳኝ፡፡በራሴ ቆሜ ህይወትን ልጋፈጣት
ወሰንኩ፡፡እንባየ ሶስት ቀን በማልቀስ አልቋል፡፡በውስጤ የቀረው እልህ ብቻ ነው፡፡
ቁጭት!!መጀመሪያ እህል ቀምሼ ራሴን አበረታሁ፡፡ቀጠልኩና የሸተተ ገላየን
ታጥቤ ጸጉሬን በአንድ ሰርቼ አስተካከልኩት፡፡ራሴን በትንሽየ መስታወት ውስጥ
ተመለከትኳት፡፡ያው ናት
መሸትሸት ሲል እንደነገሩ ለብሼ ጎተራ ኦሜድላ ሆቴል አካባቢ ቆምኩ፡፡ራሴን
ለገበያ ማቅረቤ ነበር፡፡ከወንድ ጋር ተኝቼ አይደለም ከንፈሬን ተስሜ አላቅም እኮ፡፡
ክብረ ንጽህናየ እንዳለ ነበር፡፡ድህነት አስቀያሚ ነው፡፡ሰብእናህን አሳጥቶ
የተሳሳተ መንገድ እንድትሄድ ያደርግሀል፡፡ካለሁበትን ውጥረት ያወጣኛል ብየ
ያሰብኩት የተሳሳተውን መንገድ ነው፡፡ስለዚህም እንደሚታረድ በሬ ራሴን ለእርድ
አቀረብኩ፡፡
አንዴ ገበያው ላይ ውጣ እንጂ ሊቀምስህ የሚያሰፈስፈው ብዙ ነው፡፡እዛው
በቆምኩበት ከህሊናየ ጋር እየታገልኩ ሳለ እድሜው በአርባዎቹ መጀመሪያ
የሚገመት ሰውየ መኪና ውስጥ ሆኖ ጠራኝ፡፡ሳላመነታ መኪናዋ ውስጥ ገባሁ፡፡
መኪናዋ ውስጥ የሚሸተው መልካም መአዛ የአባቴ መኪና ውስጥ ይሸተኝ
የነበረው አይነት ነው፡፡ሳላስበው እንባየ አመለጠኝ፡፡የሆንኩትን ጠየቀኝ፡፡ራሴን
አረጋግቼ ሁሉንም ነገርኩት፡፡አብረን ራት በላን፡፡የሚጠጣ ጠጣን፡፡
3ሰአት ሲሆን አብሬው እንዳድር ወደ አልጋ ይዞኝ ሲሄድ በሚገርም ሁኔታ ድንግል
እንደሆንኩ ነገርኩት፡፡ያልተለመደ ነገር ስለገጠመው ግራ ተጋብቶ አየኝ፡፡አልጋ
ላይ ወጥቼ ተንጋለልኩለት፡፡ቁላው ትልቅ ነው፡፡ወደ ውስጥ ሲከተው የሆነ ትልቅ
አጣና የመሰገብኝ ነበር የመሰለኝ፡፡በደም ተነክሬ ተንቀጠቀጥኩ፡፡የእውነት
ድንግል መሆኔ አስደንቆት ነው መሰለኝ 5ሺ ብር አሰጨብጦኝ ቤቴ አደረሰኝ፡፡ከዛ
በኀላም የተወሰነ ገንዘብና የሚበላ ነገር እየያዘ ለሳምንት ተመላልሶ ጠየቀኝ፡፡
ሳየው ግን እፈራው ነበር፡፡
ቁስሌ ሲድን የነበርኩበትን መኖሪያ ቤት ቀይሬ መኖር ጀመርኩ፡፡ከዛ በኀላ ቀላል
ነበር፡፡አንድ ወር በተከታታይ ሸረሞጥኩ"
የተገነጠለውን የህይወት ገጿን ነግራኝ ስናበቃ ወደ ሰፈሬ ልታደርሰኝ መኪናዋ
ውስጥ ገባን፡፡ከዛ በኀላ ምንም አላወራችም፡፡በጸጥታ ብቻ ትነዳለች፡፡ሰፈሬ
ስደርስ ዳር ይዛ ቆመች፡፡
"አመሰግናለሁ ጥሩ ሰው ነህ፡፡ቆሻሻ ታሪኬን ልቅም አድርገህ ሰምተህ
ተጋርተህኛል፡፡ውለታህን ግን ፈልጋለሁ"
"ምን ልታዘዝሽ?"
"በፍጹም ደግመህ እንዳታገኘኝ፡፡ማለቴ ስልክ እንዳንለዋወጥ ቻው እንዳንባባል
ዝም ብለህ ብቻ ወርደህ ሂድ፡፡ይሄን ታደርግልኛለህ?"
በሩን በዝምታ ከፍቼ ፊቴን ሳላዞር እንዳዘዘችኝ ሳልሰናበታት ቁልቁል ወረድኩ፡፡
"በቃ?ሃሃሃሃሃሃ ያንተን ታሪክ እኮ አልነገርከኝም፡፡"
"መናኛ ደሀ የሚነገር ታሪክ የሌለኝ ምንም ነኝ!!!አመሰግናለሁ ቢታንያ አንቺ
አለምን የምታጣፍጪ ቅመም ነሽ ደህና ሁኚ"
"ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ"ሳቋ ከጆሮየ መራቅ ሲጀምር ዞሬ አየኀት፡፡አይኖቿ ላይ እንባ
ተገድቧል፡፡ሲጢጢጥጥጥ አድርጋ በፍጥነት እየነዳች ከአይኔ ተሰወረች፡፡

ይቀጥላል...
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
1.1K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 20:05:05 ሳቂታዋ ዝሙት አዳሪ

ክፍል 6

የእናቱ ልጅ
.
.
.
ቀኑን ሙላ ያለመሰሰት ሙሉ ወጪየን ችላ የሚጣፍጥ ታሪኳን ስታስኮመኩመኝ
ዋለች፡፡አመሻሹ ላይ ሁለታችንም ሞቅ ብሎን የሷ ምላስ መተሳሰር ሲጀምር
የቀረ ታሪኳን አስለፈለፍኳት፡፡
"ተወልጄ ያደግኩት አዳማ ነው፡፡የናዙየ ልጅ ነኝ፡፡ወላጆቼ ትላልቅ ሆቴሎችና
የኮንስትራክሽን ድርጅት የነበራቸው ኤርትራውያን ነበሩ፡፡የሀብታም ልጅ በመሆኔ
የተማርኩት በወቅቱ ውድ እና ተመራጭ በነበረው አቃቂ አድቬንቲስት አዳሪ
ትምህርት ቤት ነው፡፡
የኢትዮ ኤሪትራ ግጭት ተቀስቅሶ ሁለቱ ሀገሮች ወደ ጦርነት ሲገቡ የኛ ቤት
ጀንበር መጥለቅ ጀመረች፡፡በእርግጥ የሁለቱም ሀገራት ፖለቲከኞች እልህ
መወጫ የሆነው ምስኪኑ ህዝብ ነው፡፡በሁለቱም ሀገራት የነበሩ ህዝቦች
ከኖሩበት ወደ ሀገሮቻቸው እየተባረሩ ሲመለሱ የነበራቸውን ጥሪት እንዲይዙ
ሳይፈቀድላቸው ነበር፡፡
አንድ አርብ ቀን ከትምህርት ቤት ወጥቼ አዳማ ሄድኩ፡፡ግቢያችን ደርሼ ስገባ
ህይወት የነበረው ቤታችን እንደ በረዶ ቀዝቅዞ ጠበቀኝ፡፡በፍርሃት ተውጬ ቤት
ገባሁ፡፡አሳዳጊ ሰራተኛችን ብቻዋን ተቀምጣለች፡፡በአስር ደቂቃ ልዩነት ታላቅ
ወንድሜም ተከትሎኝ ደረሰ፡፡ወላጆቻችንና አንድ እህትና አንድ ወንድማችን
በድንገት ተይዘው ወደ ኤርትራ ድንበር መጣላቸውን አሳዳጊያችን ነገረችን፡፡
አዘንን፡፡ተላቀስን፡፡ቀጥላም ተቀናቃኝ እንዳንሆንባት ይመስላል እኛም እየተፈለግን
እንደሆናነና በፍጥነት ራቅ ያለ ቦታ መደበቅ እንዳለብን አስጠነቀቀችን፡፡ጊዜ
አላጠፋንም፡፡የተወሰኑ ልብሶቻችንን ይዘን ወደ አዲስ አበባ መጣን፡፡ሸገር
ስንደርስ በነበረችን ጥቂት ገንዘብ ቤት ተከራይተን ለመጀመሪያ ጊዜ ከድህነት
ጋር ተዋወቅን፡፡
ኑሮን ለመግፋት ወጣን ወረድን፡፡ወንድሜ ክብሩን ጥሎ ጭቃ አቡኪ እስከመሆን
ደረሰ፡፡ቢጨንቀን አዳማ ሄደን አሳዳጊያችንን የወላጆቻችንን ንብረት ሙሉ
ውክልና የወሰደች እሷ ስለሆነች የተወሰነ ገንዘብ እንድትረዳን ጠየቅናት፡፡
በፖሊስ እንደምታስይዘን ዝታ በጭካኔ አባረረችን፡፡ወደ ሸገር ተመልሰን የሰቆቃ
ህይወታችንን መግፋት ቀጠልን፡፡ወንድሜ ግን የወረደብንን መአት መቋቋም
አቃተውና ጨክኖ ወደ ሱዳን ተሰደደ፡፡
ከአመታት በኀላ ወላጆቻችን በብስጭትና በችግር ተከታትለው ማረፋቸውን
ከኤርትራ የመጣ ሰው አረዳኝ፡፡ኤፍሬም ገብረታቲዎስን ታቀዋለህ?"
ጠየቀችኝ፡፡የማቀው መሆኔን በአወንታ አመለከትኳት፡፡ቀጠለች..
"ለኤርትራ 10ሺ ሜትር የሚሮጠው ኤፍሬም የታናሼ ታናሽ ወንድሜ ነው፡፡
ታቃለህ እኔ ኢትዮጵያዊት ነኝ፡፡ሌላ ሀገር የለኝም፡፡የኔ አለም የኔ መጀመሪያ የኔ
መጨረሻም እዚች ሀገር ላይ ነው የሚሆነው፡፡ኤፍሬም በአለም ሻምፒዮና
ሲያሸንፍ እኔ ሁለተኛ ለወጣው ኢትዮጵያዊ አትሌት ድጋፌን እየሰጠሁ ነበር፡፡
ወንድሜ ሲያሸንፍ በጣም ተበሳጨሁ፡፡ሀገሬን ወዳታለሁ፡፡ቤተሰቦቼን አንዴ
አጥቻቸዋለሁ ሀገሬን ግን ላጣት አልፈልግም"
የእንባ ዘለላዎች አይኖቿ ላይ ተንጠልጥለው ለመንጠባጠብ አሰፍስፈዋል፡፡ምን
አይነት ውብ ሴት ናት?ቀጫጫ ብትሆንም ቋጥኝ ቋጥኝ የሚያካክሉ ችግሮችን
ተቋቁማ ማለፏ የሚያስደንቅ ነው፡፡
ቀጠለች
"ከህይወቴ ገጽ ሆነ ብየ ያልነገርኩህ የተገነጠ አንድ ገጽ አለ፡፡እሱን ብነግርህ
ምናልባት እንዳትጠላኝ ስለምሰጋ ነው የዘለልኩት፡፡መስማት ከፈለግክ ግን
እነግርሃለሁ፡፡መስማት ትፈልጋለህ?"
"ንገሪኝ"
ለደቂቃዎች በፈገግታ አይኖቿን አቦዝዛ ስታይ ቆይታ ቀጠለች....

ይቀጥላል
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
https://t.me/yena_tarikoce
1.2K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ