Get Mystery Box with random crypto!

حيات سحبا የምርጦች ትውልድ ታሪክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yemrtoche_twlede — حيات سحبا የምርጦች ትውልድ ታሪክ ح
የቴሌግራም ቻናል አርማ yemrtoche_twlede — حيات سحبا የምርጦች ትውልድ ታሪክ
የሰርጥ አድራሻ: @yemrtoche_twlede
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 131
የሰርጥ መግለጫ

«ያ አላህ! ባልሰራበት እንኳ ወደ በጎ ነገር
ያመላከተ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ፡፡»
.
.
.
.
.
ማሳሰቢያ:- Leave Channel ከማለቶ በፊት
ያለተመቾት ነገር ካለ ያሳውቁን
@yemrtoche_twledebot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-09 08:42:32

57 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 22:30:10 ከአሏህ መልካም ነገር እንጂ አታስብ

ለአንድ የአረብ ዘላን: አንተኮ ሟች ነህ አሉት…
አርሱም አለ: ከዚያስ ወዴት እሄዳለሁ?
ወደ አሏህ አሉት
እርሱም: ኸይርን ከአሏህ እንጂ አግኝተን አናውቅ… ታዲያ ከርሱ ጋር መገናኘትን እንፈራለን እንዴ!

ከአሏህ መልካምን ማሰብ ምነኛ ያማረ ነው!!

ከሰለፎች አንዱ ተጠየቀ: ዱዓው ተቀባይነት ያለውን ሰው ታውቃለህን?

እርሱም አላቸው: አላውቅም። ግን ዱዓን የሚቀበለውን አውቃለሁ!

ከአሏህ መልካምን ማሰብ ምነኛ ያማረ ነው!!

አንዱ ኢብኑ ዐባስን ጠየቃቸው: ለቂያም ለት ማን ነው ሰውን የሚመረምረው?
ኢብን ዐባስ: አሏህ ብለው መለሱለት።
ሰውየውም አለ: በከዕባ ጌታ እምላለሁ ዳንን!!

ከአሏህ መልካምን ማሰብ ምነኛ ያማረ ነው!!

አንድ ወጣት ሞትን ሲያጣጥር እናቱ አለቀሰች…

ወጣቱ: አማዬ የኔን ስራ አንቺ የምትመረምሪው ቢሆን እንዴት ታደርጊ ነበር?
እናት: አዝንልክ ነበር።
ወጣቱም አላት: አሏህ ካንቺ የበለጠ ለኔ አዛኝ ነው!!

ከአሏህ መልካምን ማሰብ ምነኛ ያማረ ነው!
111 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 22:21:33 ~ ጉዞው የቀልብ መሆኑን እወቅ

ውድድሩ የሚለካው በመልካም ስራ ብዛት ብቻ አይደለም ይልቁንም ዋነኛው መለኪያ የቀልብ ልስላሴና ተቅዋ እንዲሁም ከወንጀል ፅዱ መሆን ነው። የዱኒያ ጉዞ በአካል የሚደረግ ሲሆን የአኬራው ግን ~ ቀ ል ብ ነው።

አንድ ሰው ወደ ዛሂዱ ኡበይ ዐሊ አድ ደቂቅ ምክር ፍለጋ ገሠገሠ "እርስዎ ጋር ለመድረስ ረጅም ርቀት መምጣቴ ነው። አላቸው። እርሳቸውም...

ጉዳዩ ረጅም ርቀት በማቋረጥ አይደለም። በእያንዳዱ እርምጃህ ከነፍስህ መራቅህን እርግጠኛ ሁን ፤ ያኔ ወደፈለከው ግብ ትደርሳለህ። ሲሉ የቀልብን ከፍተኛ ሚና ጠቆሙት።

መቶ ነፍስ ስላጠፋው ሰው ኢማም አር ራፊዒይ ያሉትን ተመልከት።..

ይህ ሰው ወደ አላህ የተጓዘው በቀልቡ በመሆኑ አንዷ እርምጃ ይልቁንም አንዷ ስንዝር ርቀት ከፍተኛ ዋጋ ተሰጣት። እዲህ አይነት ቀልብ ሳይኖረው ዓለምን በእግሩ ቢያካልል እንኳ በስጋው ውስጥ ከተቀበረው አጥንቱ የተሻለ ስብዕና አይኖረውም። ምስራቅ ውስጥም ይሁን ምዕራብ ስጋው መቃብሩ ነው። ከመሬት ጋር የሚያመሳስላቸው አንድ እውነታ አለ፤ ያም ያ ሰው ሙት መሆኑና እርሷ ደግሞ መቃብሩ መሆኗ ነው።


የቀልብ ጉዞ ከአካል ጉዞ ይበልጥ ወሳኝ ነው፤ ስንት አለ በአካሉ የአላህ ቤት የደረሰ ነገር ግን ከአላህ የተቆረጠ!

ስንት አለ እቤቱ ፍራሽ ላይ ተቀምጦ ሰማየ ሰመያትን ያዳረሰ!
85 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 22:18:44 ••❥ አንድ ሰማይ ሺህ ከዋክብት ፤ አንድ ህይወት ሺህ ፈተና።

••❥ከዋክብት የጨለመን ሰማይ በብርሃን
ያፈካሉ።

••❥ ፈተናና ችግር ትእግስት ያስተምራሉ።

••❥ ከፈተና ቡኃላ የምታገኘው ውጤት ህይወትህን በደስታ ሐሴት ይሞላታል።
77 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-08 07:31:30 ቀልባችሁ የራበው እንደሆነ ቁርኣንን መግቡት፣
የጠማው እንደሆነም ሐዲሥን አጠጠጡት፣
የደረቅ እንደሆነም በዚክር አርጥቡት፣
የከፋው እንደሆነም በዱዓ አጽናኑት።
ከጥንት እስከ ዛሬ የማውቀው ነገር ቢኖር ....
አላህ ወደሱ የተጠጋን ያስጠጋዋል፣
ከሱ የለመነን ይሰጠዋል፣
በሱ የተመካን ያግዘዋል።
አላህ ያለው ሰው ስለምን ያዝናል!
ተወኩላችንን የምናጠነክርበት በዱዓ፣ በካህፍ፣ በሰለዋት የደመቀ ጁመዓ ይሁንልን


اللهم صلِّ وسلِّم وبارك على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين.
86 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 21:28:58 .የጀነት ሰዎች ቁጭት...

የሚገርም ርዕስ ነው። ስኬት ላይ ያሉ የጀነት ሰዎች ሊቆጩ ይችላሉ። የሚፈልጉትን አግኝተው የተመኙት ጋር ደርሰው የለም እንዴ?

የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) ያሉትን እንይ...

የጀነት ሰዎች በምንም ነገር ላይ አይቆጭም። የተላቀና አሸናፊ የሆነውን አላህ ሳያስታውሱ (ዚክር ሳያደርጉ) ያሳለፏት ሰዓት ላይ ቢሆን እንጂ።
(ጦብራኒና በይሀቂ)

እናንተ የጀነት ሰዎች ሆይ! እንዴት ትደነቃላችሁ ?! በዱኒያ ህይወታችሁ አላህ ላይ በማመፃችሁ። አይደለም የተቆጫችሁት። ይልቁንስ እርሱን ሳታስታውሱባት ባለፈች ሰዓት ምክኒያት ነው የተፀፀታችሁት። በአንፃሩ ከናንተ ውጭ ያለው በዱኒያ ውስጥ ስላጣው ጣዕም ይፀፀት ይሆናል። ከስሜት ዳንኪራ የተራራቀ በመሆኑ ይቆጫል። በሁለቱ ጎራዎች መካከል ያለው ልዩነት ሰፊ ነው?!

አል አውዛዒ ተማሪዎቻቸውን ሰብስበው ከላይ የተጠቀሰውን ሃዲስ ሲያብራሩ እንዲህ ነበር ያሉት...

የቂያም ቀን እያንዳንዷ በዱኒያ ውስጥ ያሳለፉት ሰአት በባሪያው ፊት ትቀርባለች። ቀን በቀን ሰዐት በሰዓት። አላህን ያላስታወሰባት (ዚክር ያላድ0ረገባት) አንዲት ሰዓት ባለፈች ቁጥር በቁጭት ትንፋሹ ቁርጥ ይላል። ሰዓት ሰዓትን ቀን ቀንና ሌሊት ሌሊትን ተከታትሎ አላህን ያላስታወሰበት ጊዜ ሲመለከት ምንድን ነው የሚውጠው?

ምንጫችን....
ፍኖተ ጀነት በኡዝታዝ በድሩ ሁሴን የተተረጓመው

@yemrtoche_twlede
150 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-11 22:11:45 ነበር ። የሀያላኑን ጎራ ተቀላቀሉ ሲላቸው እርሱን ሰጣቸው ።


የኑክሌር ስሪቱን የመሩት የያኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ዙልፋቃር አሊቡቶ በቁጭት እንደዚህ ብለው ነበር
" የክርስትና ሃይማኖት ስልጣኔ የኑኬሌር ቴክኖሎጂ አለው ፤ የሂንዱ ስልጣኔም ኑክሌር አለው ፤ የክንፊሼስ ስልጣኔም የኑክሌር ባለቤት ነው ። የአይሁድ ስልጣኔም ኑክሌር ታጥቋል አሁን የኑክሌር ቴክኖሎጂ የሌለው እስልምና ብቻ ነው ስለዚህ ይህን ቴክኖሎጂ እኛ ሙስሊሞችም ሊኖረን ይገባል " !!

ይህንን የዙልፊቃርን የቁጭት ንግግር የመለሰው ጀግና አብዱልቃድር ኻን ይባላል ። እርሱ የፓኪስታን አልበርት አንስታይን ነበር !!!

#yemrtoche_twlede
157 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-11 22:11:45 #አብዱልቃድር_ኻን_የፓኪስታን_የኑክሌር_አባት_የሰሜን_ኮሪያ_ባለውለታ

ሙሉ ስሙ አብዱልቃድር አብዱልገፉር ኻን ይባላል ። ከአባቱ ከአብዱል ገፉርና ከእናቱ ከዙለይካ እ.ኤ.አ በ 1936 በዛሬዋ ህንድ ተወለደ ። ያኔ እርሱ ሲወለድ ባንግላድሽ ፣ ፓኪስታንና ህንድ አንድ ሃገር ሆነው በእንግሊዝ አገዛዝ ስር የነበሩበት ነበር ።

በ 1947 እንግሊዝ ከህንድ ክፍለአህጉር ለቃ ስትወጣ ትገዛቸው የነበሩት ህዝቦች በሀይማኖት ጦርነት ይተላለቁ ጀመር ። የአሁኗ ህንድ በሂንዱ ሃይማኖታዊ ብሔርተኝነት ስትመሰረት ፓኪስታንና ባንግላዴሽ ደግሞ በኢስላማዊ ብሔርተኝነት አንድ ሃገር ሆነው ተገነጠሉ ። የአሁኗ ፓኪስታን ምእራብ ፓኪስታን ትባል የነበረ ሲሆን ባንግላዴሽ ደግሞ ምስራቅ ፓኪስታን ተብላ አንድ ሃገር ነበሩ ። ምንም እንኳ ባንግላዴሽ ሗላ ላይ ከፓኪስታን ብትገነጠልም ።

የአብዱልድር ኻን ቤተሰቦች የሚገኙት በህንድ ግዛት ውስጥ ቢሆንም ጥብቅ የእስልምና አማኞች በመሆናቸው ከሚደርስባቸው ሃይማኖታዊ ጥቃት ለመሸሽና ወደ ኢስላማዊቷ ፓኪስታን ለመጠቃለል ወደ ፓኪስታን ተመሙ ። አብዱልቃድርም ህንድ ውስጥ የጀመረውን ትምህርት ትቶ ወደ ፓኪስታኗ ካራቺ ከተማ በመምጣት ትምህርቱን ቀጠለ ። በዚያም በካራቺ ዩኒቨርስቲ በፊዚክስ የመጀመሪያ ድግሪውን ያዘ ።

በዚያው በካራቺ እያለ አንድ ህይወቱን የሚቀር ነገር ተከሰተ ። አብዱልቃድር ኻን የምእራብ ጀርመንን ስኮላርሽፕ በማግኘት ወደ አውሮፓ አቀና ። ያኔ ጀርመን ለሁለት የተከፈለች ሲሆን ምእራብ ጀርመን እና ምስራቅ ጀርመን በመባል ትጠራም ነበር ። አብዱልቃድር ትምህርቱን በጀርመን እየተከታተለ ሳለ ከኔዘርላንድ ሌላ የትምህርት እድል አግኝቶ ወደ አምስተርዳም አቀና ። የአብዱልቃድር ብቻ ሳይሆን የፓኪስታንም ታሪክ የተለወጠው በዚህ በኔዘርላንድ ቆይታው ነው ።

በትምህርቱ ስኬታማ በስራውም ታማኝ የነበረው አብዱልቃድር ኻን በብረት ምህንድስናና በሌሎችም ሳይንሳዊ ምርምሮች ከፍተኛ እመርታ በማሳየቱ የእንግሊዝ ጀርመንና ኔዘርላንድ የጋራ የኑክሌር መመራመሪያ ማእከል የሆነው URENCO የተሰኘው ተቋም በኑክሌር ተመራማሪነት ቀጠረው ። በዚህም ከፍተኛ የኑክሌር እውቀቶችን ማካበት ቻለ ። በስራው የተቋሙን እምነት በትልቁ ማግኘት የቻለው ፓኪስታናዊው ሳይንቲስት ታላላቅ ሚስጥራዊ የኑክሌር ረቂቆችን ዶክመንቶችን እንዲተረጉም ሃላፊነት ተሰጠው ። በዚህ ጊዜ ያገኛቸውን እውቀቶች በሀገሩ ቋንቋ እየከተበ ለሀገሩ ውለታ ለመዋል ያዘጋጃቸው ጀመር ።

አብዱልቃድር ኻን ሀገሩን አብዝቶ የሚወድ ለእምነቱም ቀናኢ የነበረ ሰው በመሆኑ በነዚያ የአውሮፓ ታላላቅ ጊዜያቶቹ ለአንድት ቅፅበት እንኳ ሀገሩን አይዘነጋም ነበር ። እናም ተገቢውን የኑክሌር ሚስጢር ከሸከፈ እና ረቂቆቹን አዘጋጅቶ ከጨረሰ በሗላ ለሀገሩ መንግስት የኑክሌር ቦንብ ለመስራት የሚያስችለው ቀመር እንዳለውና ለዚህም ሁሉን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን በደብዳቤ አሳወቀ ። ይሁን እንጅ ፓኪስታን አብዱልቃድርን በአንድ ጊዜ ልታምነው አልቻለችም ። እናም አስፈላጊው መጣራት ከተደረገበት በሗላ ከዙልፊቃር አሊቡቶ ጋር ተገናኝቶ ተነጋገረ ። አሊቡቶ አብዱልቃድርን ያን ያክል ተስፋ ባይጥሉበም "ጥሩ ነው " በማለት ሀሳቡን ተቀበሉት ።

የምንጊዜም ጠላቷ ህንድ " የቡድሃ ፈገግታ " በተሰኘው የድል ብስራቷ የኑክሌር ባለቤት መሆኗን ያረጋገጠች ሆና ሳለ ፓኪስታንን እንቅልፍ ሊወስዳት ቀርቶ ሊያንጎላጃት አይችልምና ዙልፊቃር አሊቡቶ የሀገሪቱን ሳዬንቲስቶች በአስቸኳይ የኑክሌር መሳሪያን እንዲሰሩ ቀጭን ትእዛዝ የሰጡበት ጊዜና ሳይንቲስቶቹ በሚስጥር ጥድፊያ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው አብዱልቃድር ኻን ከሰማይ እንደወረደ መላኢካ ከድንገት ዱብ ያለው ።

ግና ቀድመው የነበሩት የፓኪስታን ሳይንቲስቶች በቅናት ይሁን በአጉል ኢጎ ከአብዱልቃድር ጋር መስማማት ተሳናቸው ። እርሱ የነርሱን ስራ የኑክሌር ባለቤት እንደማያደርግ ሲነግራቸው ጭራሽ መካረሩ ጦፎ የፓኪስታን ኑክሌር ሳይንቲስቶች ለሁለት ተሰነጠቁ ። ይህ ያስደነገጠው የፓኪስታን መንግስት በአብዱልቃድር ኻን ስር የሚመራ ተቋም አደራጀ ። አብዱልቃድር ኻንም ይዞ የመጣቸውን የማይገኙ የኑክሌር ሚስጥሮች ስራ ላይ አዋላቸው ።

ከብዙ ጥረትና ልፋት በሗላ እጅግ በረቀቀ ሚስጥር የኑክሌር ቁሳቁስችን ከአውሮፓና አሜሪካ ጭምር በጥብቅ ሚስጥር እየለቀሙ ወስደው ከሰሩ በሗላ ፓኪስታን ለአለም የኑክሌር ባለቤትነቷን አሳየች ። በዚህ ጊዜ ከእስራኤል እስከ ህንድ በድንጋጤ ቢዋጡም በቁጣ ቢንተከተኩም ነገሩ ያለቀለት ነበርና ምንም ማምጣት አልቻሉም ነበር ። ሳይንቲስቱ ዶክተር አብዱልቃድር ኻን የኑክሌር ቦንቡን ባበሰረበት ወቅት " የታጠቅነው የኑክሌር ቦንብ ህንድን ብቻ ሳይሆን እስራኤልንም ማውደም የሚችል ነው " በማለት ነበር እስራኤልን ኩም ያደረጋት ። እናም እስራኤል በኢራንና ኢራቅ እንደፈፀመቺው አይነት ጥቃትና ትንኮሳ በፓኪስታን ላይ ለማድረግ ከቶም አልደፈረችም !

አብዱልቃድር ኻን ፓኪስታንን ያስታጠቃት ኑክሌር ብቻ አይደለም ይልቁንስ ረጅም ርቀት ሊመዘገዘጉ የሚችሉ ሚሳኤሎች ባለቤት ትሆንም ዘንዳ ያስቻላት የማይተካ ልጇ ነው ። ፓኪስታን አብዱልቃድር ኻንን የመሰለ ከሺህ አመታት አንድ ጊዜ የሚፈጠር ልጅ ባይኖራት ኖሮ ዛሬ እኔደ ኢራን ኑክሌር ለመታጠቅ 30 አመታት የሚፈጅባት ሀገር ትሆን ነበር ።

የምእራባዊያን ጠላቱ አብዱልቃድር ኻን የኑክሌር ባለቤት ያደረገው ሀገሩን ፓኪስታንን ብቻ አይደለም ! ይልቁንስ የኪሞቹን ሀገር ኮሚኒስቷን ሰሜን ኮሪያን ጭምር እንጅ ። እነዚያን አብዱልቃድር እንጅ ሌላው የሌለውን የኑክሌር ቀመሮች ለሰሜን ኮሪያ ባይሰጣት ኖሮ ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ የምትፈራት የኑክሌር ባለቤት ሀገር ላትሆንም ትችል ነበር ። አብዱልቃድር ለሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ቴክኖሎጂን ለማስተላለፍ ከ 13 ጊዜ በላይ እንደተመላለሰ ምንጮች አረጋግጠዋል ። ይህም በፓኪስታን መንግስት በተሰጠው ትእዛዝ ነበር ። ፓኪስታን ለሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ቴክኖሎጂን ስታስተላልፍ ሰሜን ኮሪያ በአፀፋው የሚሳኤል ቴክኖልጂዎችን ለፓኪስታን ታስተላልፍ ነበር ።

አብዱልቃድር ኻን ከሰሜን ኮሪያ በተጨማሪ ለኢራን እና ሊቢያ የኑክሌር ቴክኖሎጂዎችን እንዳስተላለፈ ይነገራል።

ይህን የደረሰችበት አሜሪካም በፓኪስታን ላይ ልምጯን መዘዘች ። ፓኪስታንም ከአሜሪካና አጋሮቿ በትር ለማምለጥ ስትል ይህንን ያደረገው ካለ እውቅናዋ አብዱልቃድር መሆኑን ለነ አሜሪካ ገለፀች ። እናም አብዱልቃድር ታሰረ ። ፓኪስታን ከነአሜሪካ ማእቀብ ለማምለጥ ስትል የቁርጥ ቀን ልጇን ፊዳ አቀረበቺው ። ልጇም አላሳፈራትም ። " እኔ ሀገሬን ለማዳን እንኳን መታሰርና የህይወት መስዋእትነትም እከፍላለሁ " በማለት ሃላፊነቱን ወስዶ የቁም እስረኛ ሆነ ። ሁሉም የፓኪስታን ቁማር ነበርና በሗላ ላይ ነፃነቱ በፍርድቤት ተረጋግጦለት ከእስር ነፃ ሆነ ።

አብዱልቃድር ኻን እንደዚህ ይላል
" እኔ ፓኪስታንን ሁለት ጊዜ አድኛታለሁ አንደኛው የኑክሌር ቦንብ ባለቤት አድርጌ የማትደፈር ሀገር ሳደርጋት አድኛታለሁ ሁለተኛው ደግሞ የኑክሌር ቴክኖሎጂን ለነ ኮሪያ አሳልፈሻል ተብሎ ከፍተኛ ማእቀብ ሊጣልባት ሲል ራሴ ሃላፊነቱን ወስጄ አድኛታለሁ " በማለት ገልጿል።

አብዱልቃድር ኻን በፓኪስታን ውስጥ ያልተሸለመው አይነት ሽልማት የለም ። ታላላቆቹ የፓኪስታን ዩኒቨርሲቲዎች ሁሉም በሽልማትና ዶክትሬት አንቆጥቁጠውታል ። በእርሱ ስም ያልተሰየመ ግዳና እና ተቋም የለም ። እርሱ ፓኪስታኖች ፈጣሪ የሰጣቸው በረከት
157 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-21 19:53:47 አቡሁረይራ ባስተላለፋት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል

ሁለት ንግግሮች አሉ
ለምላስ እጅግ የቀለሉ
ሚዛን የሚደፋና
አላህ ዘንድ እጅግ የተወደዱ
እነሱም፦
ሱብሀን አላህ ወቢሀምዲሂ سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ
ሱብሀን አላሁል አዚም سُبْحَانَ اللهِ العظيمِ ናቸው

(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

አቡ ሙሰል አሽአርይ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል።

ጌታውን የሚያወሳና የማያወሳ ሰው ምሳሌው በህይወት እንዳለና እንደሞተ ሰው ነው።

(ቡኻሪ ዘግቦታል)

ምላሳችን በሌላ ነገር ከመጠመዱ በፊት በዚክር እንጥመደው

- «سُبْحَانَ اللهِ»
- «الحَمْدُ للهِ»
- «لَا إلَهَ إلَّا اللهُ»
- «اللهُ أكْبَرُ»
- «سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ»
- «سُبْحَانَ اللهِ العَظِيمِ»
- «لَا حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إلَّا بِاللهِ»
- «أسْتَغْفِرُ اللهَ وَأتُوبُ إلَيْهِ»
- «لَا إلَهَ إلَّا أَنْتَ سُبْحَانَكَ إنِّي كُنْتُ مِنَ الظَّالِمِينَ»


@yemrtoche_twlede
132 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-12 21:10:28 ዶ/ር አብዱረህማን አስ-ሱመይጥ እንዲህ ይላሉ:-
"በአፍሪካ የሰብአዊ እርዳታና የዳዕዋ እንቅስቃሴ ላይ በነበርንበት ሰዓት አንዲት
አፍሪካዊት እናት ወደ አንድ ዶክተር ጋር ቀርባ አምርራ እያለቀስች
ስትለማመጠው ተመለከትኩ።ዶክተሩ የህፃናትን የህክምና ጉዳይ የሚከታተል
ነበር።
ሁኔታው በጣም ስሜቴን ስለነካኝ ዶክተሩን ስለምታለቅስበት ምክኒያት
ጠየቅኩት።ዶክተሩም:-
"በአንቀልባ ላይ የሚገኘው ጨቅላ ልጇ በሞት አፋፍ ላይ ነው የሚገኘው።እኛ
ጉዳያቸውን ከምንከታተላቸው ህፃናት ጋር አንድ ላይ ጉዳዩን እንድናይላት ነው
የምትፈልገው።ነገር ግን ለእሱ የምናፈሰው ገንዘብ ጥቅም አልባ ነው።ጥቂት
ቀናትን እንጂ መኖር የማይችል ልጅ ነው።ለህክምናው የምናወጣውን ገንዘብ
ለሌላ ልጅ ብናወጣው ይሻላል" አለኝ።
እኔም ወደ እናትየው ተመለከትኩ።ዶክተሩን በእምባ ተሞልታ የምትልማመጥበት
ሁኔታ ልቤን ነካው።
ለተርጓሚውም በየቀኑ ምን ያክል ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት እንዲጠይቃት
ነገርኩት።እሷም ገንዘቡን ነገረችው።ገንዘቡ በጣም ጥቂት ነበር።በሀገራችን
ለለስላለሳ መጠጥ ለምናወጣው ያክል ነው!
ለዶክተሩም:-"ችግር የለውም የሷን ገንዘብ ለኔ ተውልኝ።ሙሉ ገንዘቡን እኔ
ችለዋለሁ።"አልኩት።
እናትየው በደስታ እጄን ልትስም ፈለገች።እኔም ነገሩ ቀላል እንደሆነ አበስሪያት
ከለከልኳት።
ከህክምናው በተጨማሪም ለልጇ የሚያስፈልገውን የአመት ወጪ
ሰጠኋት።ድንገት ካለቀባትም በስፍራው የስራ አጋሬ ወደነበረው ሰው
እየጠቆምኳት ከሱ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ማግኘት እንደምትችል ነገርኳት።
በእውነቱ ያረኩት የእናትን ልብ የማረጋጋትና ልቧን የመጠገን እንጂ የልጁን
ህይወት ይመልሳል ከሚል ሃሳብ አልነበረም።በተለይ እናት ኢስላምን ከተቀበለች
አዲስ በመሆኗ በሷ ላይ ፈተናን ከመፍራትም የተነሳ ነበር ለመርዳት
ያሰብኩት።በመሆኑም ከክስተቱ በኃላ ጉዳዩን አስታውሼውም አላውቅም ነበር።
በዚህ ሁኔታ ወራት አልፈው አመታት ነጎዱ።ነገሩ ከተከሰተ ከ12 አመታት በኃላ
በምሰራበት ድርጅት ውስጥ ሳለሁ ከድርጅቱ ሰራተኞች አንዱ፤ አንዲት
አፍሪካዊት እናት አጥብቃ እንደምትፈልገኝና ከዚህ በፊትም ብዙ ጊዜ ፈልጋኝ
እንደተመላለሰች ነገረኝ።ወደ ቢሮው እንድትገባም ነገርኩት።
አንዲት እናት ከቆንጆ ህፃን ልጅ ጋር ወደ ቢሮዬ ገቡ።
"ይህ ልጄ አብዱረህማን ይባላል።ቁርአንን በሙሉ ሃፍዟል።በርካታ ሃዲሶችንም
በቃሉ አጥንቷል።ከናንተ ጋር የኢስላም ተጣሪ መሆን ይፈልጋል።" አለችኝ።
እኔም በጣም የልጁ ህፃን መሆንና የእናትን ስሜት ስለመተከት ተገርሜ:-"ለምን
ከኛ ጋር እንዲሰራ ፈለግሽ?" ስል ጠየኳት።
ስለ ጉዳዩ ምንም የተረዳሁት ነገር አልነበረም።ወደ ልጁም ተመለከትኩ።እሱም
በዐረብኛ እኔን ማናገር ጀመረ:-
"ኢስላምና እዝነቱ ባይኖር በህይወት ኖሬ ፊት ለፊትህ አልቆምም ነበር።እናቴ
ካንተ ጋር የነበራትን ታሪክ በሙሉ ነግራኛለች።ተስፋ በቆረጠችበት ሰዓት
የህፃንነቴን ቀለብና የህክምና ወጪ በሙሉ እንደቻልክለኝ ነግራኛለች።አሁን ላይ
እኔ አድጊያለሁ።አረቢኛን መናገር እችላለሁ።የሀገሬንም ቋንቋ እናገራለሁ።ካንተ
ስር ሆኜ ወደ ኢስላም መጣራት እፈልጋለሁ።ከናንተ ምግብን እንጂ ምንም
አልፈልግም።ከፈለክ ቁርአን ልቅራልህ።ስማኝ.." አለኝና የተወሰኑ አናቅፅቶችን
በውብ ድምፅ አነበበልኝ።አይኖቹ ጥያቄውን እንድቀበለው የሚጠይቁ ይመስል
ነበር።
የዚህኔ የልጁ ታሪክ ትዝ አለኝ።ለእናትየውም:-
"ይህ ልጅ ዶክተሮቹ የህክምና ወጪውን አናባክንም አንቀበለውም ያሉት ነው
እንዴ?" ስል ጠየቅኳት።
እናትም:"አዎን" ብላ መለሰችልኝ።
ልጁም ከእናት ቀበል አድርጎ:-"እናቴ ለዚህ ነው ካንተ ጋር ሆኜ እንድሰራ
የፈለገችው።ስሜንም አብዱራህማን ብላ ያወጣችለኝ ከዚያ በኃላ ነበር።" አለኝ።
በሁኔታው እራሴን መቆጣጠር እስኪያቅተኝ ድረስ ተደሰትኩ።ለአሏህም የምስጋና
ሱጁድ አደረኩ።የአንድ ለስላሳ መጠጥ ዋጋ በአላህ ፍቃድ እንዴት ተስፋ
የቆረጠች ነፍስን ህያው እንደምታደርግ በማሰብ ተደነቅኩ።
በኃላም ይህ ህፃን በአፍሪካ ላደረግነው የዳዕዋ እንቅስቃሴ የጀርባ አጥንታችን
ሆኖ ከኛ ጋር አሳለፈ።
ጥቂት ምፅዋት የሰው ደስታን መፍጠር፤ህይወትንም መቀየር ትችላለች
.............................
ዶ/ር አብዱረህማን በአፍሪካ የዳዕዋ እንቅስቃሴያቸው ከ11 ሚሊየን በላይ
ሰው የኢስላምን ሂዳያ እንዲያገኝ ሰበብ ሆነዋል።
Ibrahim Taj Ali
118 views˙·٠•● Abuki ●•٠·˙, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ